
07/06/2025
በተለያዩ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑና ወደ መምህርነት ሙያ መግባት ለሚፈልጉ ምሩቃን አዲስ የአሠራር ስርዓት ገቢራዊ ሊሆን ነው።
እነዚህ ባለሙያዎች ተጨማሪ ስልጠና ወስደው መምህር መሆን የሚችሉበት የሰልጠና ማዕቀፍ ማዘጋጀቱን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ይህም በሀገሪቱ የሚታየውን የመምህራን እጥረት ለመቅረፍ እንደሚያስችል በሚኒስቴሩ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
በዚህም መምህር ሆነው መስራት ለሚፈልጉ ምሩቃን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ተጨማሪ የመምህርነት ሙያ፣ የማስተማር ዘዴ፣ የትምህርት ቴክኖሎጂ እና የጋራ ኮርሶችን ስልጠና እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል።
በተለያዩ የትምህርት መስኮች የተመረቁ ባለሙያዎች፥ ተጨማሪ የማስተማር ሙያ ስልጠና ቢሰጣቸው ወደ ሙያው የመግባት ፍላጎት እንዳላቸው በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ለማረጋገጥ መቻሉን በሚኒስቴሩ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዴስክ ኃላፊ አሰገድ ምሬሳ ገልፀዋል።
አዲሱን የስልጠና ማዕቀፍ ወደ ሥራ ለማስገባት ከአሰልጣኝ የትምህርት ተቋማት፣ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የምክክር መድረክ እየተካሔደ ይገኛል።
አዲስ የተዘጋጀው አማራጭ የመምህራን ማሰልጠኛ ማዕቀፍ ከቀጣይ ዓመት ጀሞሮ ገቢራዊ ይሆናል ተብሏል።
ፌስቡክ፡- https://m.facebook.com/ethiopia24
ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiopia_24