Alem endat aderech አለም እንዴት አደረች

Alem endat aderech አለም እንዴት አደረች New news

ወሳኝ መረጃ ለ ኤክስፖርተሮች አሊባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ አንጋፋው አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም የሆነው አሊ ባባ እ...
23/02/2025

ወሳኝ መረጃ ለ ኤክስፖርተሮች
አሊባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ አንጋፋው አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም የሆነው አሊ ባባ እንደገለፀው ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአሊ ኤክስፕረስ የበርካታ አገራትን ገንዘብ ጥቅም ላይ ያውላል፡፡

ከእነዚህ አገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኬንያና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል፡፡ የክፍያ መፈፀሚያ ገንዘቦችን ማስፋፋት ያስፈለገው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች በስፋት ተደራሽ ለመሆን በማሰብ እንደሆነ የጠቀሰው አሊ ባባ በተጨማሪም በአለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና የውጭ ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማስቀረት እንደሆነ አስረድቷል፡፡

የአፍሪካ አገራትን ገንዘብ በግብይቱ ውስጥ ጥቅም ላይ ማዋሉ በአለም አቀፍ የክፍያ ስርአት የተነሳ ለአፍሪካዊያን ትልቅ ማነቆ የሆነውን ችግር ለመቅረፍ ማቀዱንም አስታውቋል፡፡ በዚህም አዳዲስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎችን እንደሚያገኝ ተስፋ ሰንቋል፡፡

ለዚህ እንዲረዳው በተጠቀሱት አገራት ከሚገኙ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ጥምረት መፍጠሩን የገለፀው አሊ ባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ማለትም የካቲት 17 ጀምሮ ብርን ጨምሮ የተለያዩ ገንዘቦችን በግብይት ስርአቱ ውስጥ እንደሚያካትት አስታውቋል፡፡
Via # zehabeshanews

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን መንግሥት አስታወቀኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ያስታወቀው  መንግሥት፣ “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገር ውስጥ ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመታየቱ ...
19/02/2025

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን መንግሥት አስታወቀ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ያስታወቀው መንግሥት፣ “ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገር ውስጥ ምርት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመታየቱ ኢትዮጵያ ከውጪ በሚገባ የስንዴ ምርት ላይ ጥገኛ መሆኗ ቀርቷል" ሲል ተናግሯል።

ትላንት የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት በምግብ ራስን መቻልን አስመልክቶ ባወጣው ዝርዝር መረጃ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማርካት በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጪ የውጭ ሀገር የስንዴ ምርት ታስገባ ነበር።

መግለጫው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022/23 የምርት ዘመን ኢትዮጵያ 15 ነጥብ 1 ሚሊየን ቶን ስንዴ እንዳመረተች ጠቁሞ የስንዴ ምርቱ መጠን በቀጠለው ዓመት ወደ 23 ሚሊየን ቶን ማደጉን አውስቷል።

አያይዞም ሀገሪቱ በስንዴ ምርት እራሷን መቻሏ ስንዴ ከውጭ መግባቱ ይቆማል ማለት ግን እንዳልሆነ ያሳሰበው መግለጫው በሀገሪቱ ውስጥ የሚሠሩ የሰብአዊ ርዳታ ተቋማት አሁንም ከሀገር ውስጥ ገበያ ስንዴ ከመግዛት ይልቅ ከውጭ ሀገራት ማስገባትን ሊመርጡ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

አገሪቱ በስንዴ ምርት ራሷን እንድትችል ካስቻሉ ርምጃዎች መካከል፣ የመስኖ ስንዴ ልማት መጀመሩ፣ የግብርና ማሺነሪዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መፈቀዱና የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ መሻሻሉ ይገኙበታል ተብሏል።

የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም
.8

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ100 በላይ ሰራተኞቹ በአንድ ጊዜ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ደመወዝ ይከፈላቸው እንደነበር ደርሼባቸዋለሁ አለ  ‼️በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1...
19/02/2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ100 በላይ ሰራተኞቹ በአንድ ጊዜ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ደመወዝ ይከፈላቸው እንደነበር ደርሼባቸዋለሁ አለ ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች “በሁለት እና በሶስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው” ደመወዝ ሲከፈላቸው እንደነበር የከተማይቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ። የከተማ አስተዳደሩ እነዚህን ሰራተኞች “ተጠያቂ ማድረጉንም” ከንቲባዋ ገልጸዋል።

አዳነች ይህንን የገለጹት፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ረቡዕ የካቲት 12፤ 2017 እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ነው።

ከንቲባዋ በዚሁ ሪፖርታቸው፤ የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ስርዓት ተግባራዊ በማድረጉ፤ በስሩ ምን ያህል ሰራተኞች እንዳሉት ለማወቅ እንደቻለ ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ 168 ሺህ ያህል ሰራተኞቹን ፋይል “ስካን አድርጎ” ወደ ስርዓቱ እንዲገባ ካደረገ በኋላ በተደረገው ማጣራት፤ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች “ያለአግባብ በሁለት እና በሶስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው” ደመወዝ እንደሚከፈላቸው እንደተደረሰበት አብራርተዋል።
© Ethiopia Insider

ሰላም እንዴት ናችሁ ሰሞኑን የተከሰቱ ለ ሊፍት (አሳንሰር) አደጋዎች እንዴት ሊክሰቱ ይችላሉ በምን ምክንያት ሊከሰት ይችላል 1 ወቅቱን የጠበቀ የጥገና ጊዜ ባለመኖሩ ማለትም ሊፍት በባህሪው ...
19/02/2025

ሰላም እንዴት ናችሁ ሰሞኑን የተከሰቱ ለ ሊፍት (አሳንሰር) አደጋዎች እንዴት ሊክሰቱ ይችላሉ በምን ምክንያት ሊከሰት ይችላል
1 ወቅቱን የጠበቀ የጥገና ጊዜ ባለመኖሩ ማለትም ሊፍት በባህሪው ተንቀሳቃሽ ነገር ነው የሚክቀሳቀስ ነገር ደሞ ብዙ ነገሮች ሊላሉ ይችላሉ እነሱን ነገሮች ቢያንስ በወር 2 ጊዜ በ ባለሞያዎች ቼክ ማስደረግ
2 ሁለተኛ እና ዋናው ምክንያት ደሞ ካቦ ወይም ገመዱ በሚበላበት ጊዜ በአፋጣኝ መቀየር አንዳድ ባለ ሃብት ወጪ ላለማውጣት በጎደለ ካቦ ወይም በተበላሸ ገመድ አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል ይህም ከባድ አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ምን የሚለውን የማህሙድ ሙዚቃ ነበር የመረጡት? በዛሬው የማህሙድ የሽኝት ኮንሰርት ላይ ይህን ዘፈን የሚዘፍን ይኖር ይሆን?ፎቶ: ከሚሊኒየም አዳራሽ:: ከቀናት በፊይ በቤተ...
12/01/2025

የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ምን የሚለውን የማህሙድ ሙዚቃ ነበር የመረጡት? በዛሬው የማህሙድ የሽኝት ኮንሰርት ላይ ይህን ዘፈን የሚዘፍን ይኖር ይሆን?
ፎቶ: ከሚሊኒየም አዳራሽ:: ከቀናት በፊይ በቤተ መንግስቱ ዕድሳት ምርቃት ላይ ያልተገኙት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በማህሙድ የሙዚቃ ስንብት ኮንሰርት ላይ ተገኝተዋል::

በተአምር የተፈረች ነፍስ !" ከዚህ ትልቅ አደጋ መትረፌን ማመን አቅቶኛል" - ከቦናዉ የመኪና አደጋ የተረፈችው የኔነሽ ለገሠበሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ተከስቶ የ71 ሰዎችን ሕይ...
01/01/2025

በተአምር የተፈረች ነፍስ !

" ከዚህ ትልቅ አደጋ መትረፌን ማመን አቅቶኛል" - ከቦናዉ የመኪና አደጋ የተረፈችው የኔነሽ ለገሠ

በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ተከስቶ የ71 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈዉ የመኪና አደጋ የተረፉት 4 ሰዎች ብቻ ናቸው።

ከእነዚህ ዉስጥ ሁለቱ ገና መኪናዉ ወደ ገደል ሳይገባ ዘለዉ በመውረዳቸው መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ሁለት ሴቶች ደግሞ ተሽከርካሪዉ ወንዝ ዉስጥ ከገባ በኋላ በከፍተኛ ጉዳት በሕይወት ተርፈዉ ከቦና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተሻለ ህክምና ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላዝድ ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸዉን የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን መረጃ ያሳያል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ቤተሰብ አባል ከዚህ አስከፊ አደጋ የተረፉትን ሁለት ሴቶች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለመጠየቅ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላዝድ ሪፈራል ሆስፒታል አቅንቷል።

ከአደጋው የተረፉት ሁለቱ ሴቶች ስማቸው የነኔሽ ለገሠ እና ከበቡሽ ሃይሌ ይባላሉ።

ከበቡሽ ኃይሌ በአደጋዉ ምክንያት ቀዶ ህክምና ተደርጎላት በመተንፈሻ ማሽን እርዳታ ዉስጥ ትገኛለች።

የኔነሽ ገለሠ ደግሞ በድንጋጤና ከፍተኛ ሕመም ዉስጥ ብትሆንም ማዉራት እና የተፈጠረውን አደጋ በመጠኑም ቢሆን ማስታወስና ከአስታማሚዎቿ ጋርም መግባባት ትችላለች።

ከአደጋው ስለተረፉት ሁለት ሴቶች በምን አይነት የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማብራሪያ ከሆስፒታሉ የጠየቅን ቢሆንም ሆስፒታሉ ከአደጋው ጋር በተያያዘ " ከፖሊስ በስተቀር መረጃ ለመስጠት እንቸገራለን " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

በወቅቱ የኔነሽ ለገሰን ሲያስታምሙ ያገኘናቸው አቶ ደበበን አሁን ስላለችበት የጤና ሁኔታ ጠይቀናቸዋል።

አቶ ደበበ እንደነገሩን የኔነሽ ስለ አደጋዉ ዝርዝር ጉዳዩ እንዳልተነገራትና በዚህ ዘግናኝ አደጋ ምክንያት አንድ እህቷን እና ሁለት ወንድሞቿን ማጣቷን ነግረውናል።

በሆስፒታሉ በተገኘን ጊዜም የኔነሽ ነቃ ብላ እያወራች ነበር።

አማርኛ ቋንቋን በሚገባ መናገር ባትችልም በሲዳምኛ ቋንቋ ስለ አደጋው ስታስረዳ ማዳመጥ ችለናል።

" አደጋዉ የተከሰተዉ የአጎቴ ልጅ ሚስት ሊያገባ ስለነበር ቤተ-ዘመድ ተሰባስቦ ሙሽራዋን ለመዉሰድ ወደ ወራንቻ ቀበሌ እየሄድን በነበርንበት ወቅት ነዉ" ብላለች።

" እኔ መሃል ነበርኩ፤ ሁላችን በደስታ በዝማሬ ላይ ነበርን ወደ ዋናዉ መስመር ወጥተን ጋላና ወንዝ ስንደርስ በድንገት መኪናዉ ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ መግባት ሲጀምር በጩኸት ብዛት.... " ንግግሯን መጨረሽ አልቻለችም።

ይኽን በምታወራበት ወቅት እምባ በሁለቱም ዐይኖቿ ይወርድ ነበር።

ከተወሰነ መረጋጋት በኋላ የኔነሽ ስለ አሰቃቂው አደጋ የምታስታውሰውን ማስረዳት ቀጠለች ፤ " አላዉቅም እኔ ዛሬ ነዉ ሀዋሳ መሆኔን እንኳን የተነገረኝ! ሌላዉን አላዉቅም ፤ አጎቴ አብረዉኝ ስለነበሩ አጠቃላይ ስለ ሰርገኛዉ ደጋግሜ ስጠይቀዉ 'እነሱ ቦና ናቸዉ! አንቺ ስለተጎዳሽ ነዉ እዚህ የመጣሽዉ' ይለኛል " በማለት አስታማሚዋ የነበሩት አቶ ከበደ እንደነገሩን ይኽንን መሪር ሀዘን አለመስማቷን አረጋግጣልናለች።

ይህንን በተናገረችበት ቅጽበት አጠገቧ የነበሩት ሁሉ ዝምታን መረጡ ሁሉም እንደተፈራራ ዝም ተባባለ በዚህ ጊዜ አንድ ጥያቄ ቀረበላት "ከቦታዉ አደገኝነት አንፃር በመትረፍሽ ምን ተሰማሽ ? " የሚል።

የኔነሽ ከነበረችበት ትካዜ በመጠኑም ነቃ ብላ " ከቦታዉ አደገኛነትና ከነበረዉ ሁኔታ አንፃር ከዚህ ትልቅ አደጋ መትረፌን ማመን አቅቶኛል " ስትል በመደነቅ ስሜት ገልጻልናለች።

እኛም ፈጣሪ ፈጽሞ እንዲምራትና ብርታቱን እንዲሰጣት ገልጸንላት ተለያየን።

የየኔነሽ አጎትና አደጋዉን ያደረሰው መኪና ባለቤት የሆኑትን አቶ ሀይሌ ሀሮንም አግኝተን ስለ አደጋዉ፣ ስለ መኪናዉ ሁኔታና ስለ ሹፌሩ ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር።

አቶ ሀይሌ ፥ " መኪናዉ አዲስ ነበር። ሹፌሩ ደግሞ የገዛ ወንድሜ ሲሆን ሙሽራዉም የወንድሜ ልጅ ነዉ። መኪናዉ በአባቢዉ ልምድ ከቡና ሳይት ሰራተኞችን የማመላለስ ስራ ይሰራ ስለነበርና አብዛኞቹ የቤተሰቦቻችን አባላት የቡና ስራ ስለሚሰሩ በዕለቱ ሰርገኞችን ጭኖ ወደ ወራንቻ እየሄደ ነበር አደጋዉ የተከሰተዉ " ሲሉ ነግረውናል።

አክለውም ፤ " ከቤተሰቦቻችን ብቻ ከ30 በላይ ሰዎች በአደጋዉ የሞቱ ሲሆን ከዛ ዉስጥ ግማሽ ያህሉ የወንድማማች ልጆች ናቸዉ. . . የቀን ክፉ አንገት አስደፋን ከፍተኛ የልብ ስብራት ነዉ ያጋጠመን ጌታ ብርታቱን ይስጠን " ሲሉ በሀዘን ውስጥ ሆነው አውርተውናል።

በአደጋው ምክንያት ሕይወታቸው ያጡ 71 ሥርዓተ ተቀብራቸዉ የተፈፀመ ሲሆን የሟቾችን ቤተሰብ ለማገዝ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱንና የገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ እየተሰባሰበ እንደሚገኝም ተረድተናል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ እየተዘዋወረ ያለው  “ሃምስተር ኮምባት” ምንድነው ? “ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካቶች ዘንድ እየተ...
27/06/2024

ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ እየተዘዋወረ ያለው “ሃምስተር ኮምባት” ምንድነው ?

“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካቶች ዘንድ እየተዘወተረ የመጣ በቴሌግም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ተጫዋቾቹ በየቀኑ ስክሪናቸውን በጣታቸው መታ መታ (ታፕ ታፕ) ሲያደርጉ ክሪፕቶ ሳንቲሞችን የሚያገኙበት ነው።
“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ በበርካቶች እየተዘወተረ የመጣ ጨዋታም ሆኗል።

በቴሌግራም ላይ የተመሰረተው ሃምስተር ኮምባት በአለም አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ተጫዋቾችን በማፍራት ከፍተኛ ተወዳጅነትን አግኝቷል።

ሃመስትር ኮምባት በቴልግራም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ኤር ድሮፕ ሊሆኑ የሚችሉ ሳንቲሞችን (ኮይን) ተጫዋቾችን የሚሸልም የቴሌግራም ጨዋታ ነው። እንዲሁም ሰዎች በቴሌግራም ለይ ጓኞቻውን እየጋበዙ በርከት ያለ የክሪፕቶ ሳንቲሞችን ለመሰብሰብ በጋራ የሚጫወቱት ጨዋታ እንደሆነም ይነገራል።

ሃመስትር ኮምባት በቴልግራም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ኤር ድሮፕ ሊሆኑ የሚችሉ ሳንቲሞችን (ኮይን) ተጫዋቾችን የሚሸልም የቴሌግራም ጨዋታ ነው። እንዲሁም ሰዎች በቴሌግራም ለይ ጓኞቻውን እየጋበዙ በርከት ያለ የክሪፕቶ ሳንቲሞችን ለመሰብሰብ በጋራ የሚጫወቱት ጨዋታ እንደሆነም ይነገራል።

ምናልባት ጨዋታ ብቻ ስለሆነ ዋናው ጥቅሙ ምንድነው? የሚል ጥያቄ ሊያስከትል ይችላል፤ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ ጨዋታ ቢሆንም፣ በሃመስተር ኮምባት የሰበሰብናቸው ሳንቲች (ኮይኖች) ኤርድሮፕ የመሆን ዝግጅት እንዳለ ነው የሚነገረው።

ይህ ማለትም በዚህ ጨዋታ ሳንቲሞችን (ኮይን) የሰበሰቡ ተጫዋቾች በቲ.ጂ.ኢ (ቶከን ጄኔሬሽን ኢቨንት) ወቅት ለኤር ድሮፕ ብቁ የመሆን እንደል አላቸው። ሳንቲሞቹ አስተዳዳሪዎች ያዋጣል ብለው ያመኑትን ማንኛውንም ተመን በመጠቀም ወደ ቶከን ይቀየራሉ፤ ስለዚህ “ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) መጫወት ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ነው የተባለው።

ሃምስተር ኮምባት ህጋዊ ወይስ ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው?

“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) በክሪፕቶ ገንዘብ ተፈጥሮ ምክንያት ህጋዊ ወይም ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ምንም መንገድ የለም። ነገር ግን ሃምስተር ኮምባት ጠቃሚ ነገር ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ ምልክቶች አሉ የተባለ ሲሆን፤ ከእነዚህም አንዱ ማሳያዎ እንደ “BingX” ካሉ ልውውጦች ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት መፍጠሩ ነው።

ይህ ማለት ወደፊት በ”BingX” ልውውጥ ላይ የሃምተርን ተመዝግቦ ልናይ እንችላል፤ ነገርግን አሁን ማድረግ ያለብን ማመን እና ጨዋታውን መጫወት ብቻ ነው። ተለዋዋጭ በሆነው እና ተገማች ባልሆነው በክሪፕቶ ዓለም ውስጥ ማድረግ የምንችለው እንድ ነገር ወይ አምኖ መጫወት አሊያም መተው ብቻ ነው።

መረጃው የ አል አይን ኒውስ ነው

ሳዑዲ ዓረቢያ ለኢትዮጵያዉያን ሰራተኞቿ የምትከፍለዉን ወርሃዊ ደሞዝ እንዲቀንስ ወሰነች👉 የደሞዝ ቅናሹ የሌሎች አምስት ሀገራት ዜጎችንም ይመለከታልሳዑዲ ዓረቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአራት ሀገራ...
17/01/2024

ሳዑዲ ዓረቢያ ለኢትዮጵያዉያን ሰራተኞቿ የምትከፍለዉን ወርሃዊ ደሞዝ እንዲቀንስ ወሰነች

👉 የደሞዝ ቅናሹ የሌሎች አምስት ሀገራት ዜጎችንም ይመለከታል

ሳዑዲ ዓረቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአራት ሀገራት ዜጎች የሆኑ ስደኛ ሰራተኞችን ደሞዝ መቀነሷን አስታዉቃለች። የሀገሪቱ ሰዉ ሃብት እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ዩጋንዳ ፣ ባንግላዴሽ ፣ ፊሊፒንስ እና ሲሪላንካ ዜጎች ሰራተኞችን ደሞዝ እንዲቀንስ አዉጃለች።

በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ አቅንተዉ ለሚሰሩ ሰራተኞች ከዚህ ቀደም ሲከፈላቸዉ ከነበረዉ 6 ሺህ 900 የሳዑዲ ሪያል ወደ 5 ሺህ 900 መቀነሷን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከሀገሪቱ ሰዉ ሃብት እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል። ሳዑዲ ባስተላለፈችዉ ዉሳኔ መሰረት ከሆነ ኢትዮጵያዊያን ዜጋ ሰራተኞች ከዚህ ቀደም ሲከፈላቸዉ ከነበረዉ የ 1ሺህ ሪያል ቅናሽ እንዲደረግባቸዉ ሆኗል።

በተጨማሪን ሰራተኞችን ወደ ሳዑዲ እንዲያዘዋዉሩ ፈቃድ የተሰጣቸዉም ተቋማት ከተጠቀሱት ሀገራት በሚያመጧቸዉ ሰራተኞች ቁጥር ላይ ገደብ እንዲያደርጉ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።

የደሞዝ ቅነሳዉም የቅጥር ወጩዎችን ለመቆጣጠር የሚደረገዉ ጥረት አካል ናቸዉ የተባለ ሲሆን ፍትሃዊ ያለዉን ክፍያ እንዲኖር ያደርጋል የሚል እምነት እንዳለዉም ጠቅሷል።

በሳዑዲ የሴራሊዮን እና ቡሩንዲ ሀገር ሰራተኞች 7 ሺህ 500 የሳዑዲ ሪያል የሚከፈላቸዉ ሲሆን የታይላንድ ዜጋ የሆኑ ሰራተኞች በአንጻሩ 10 ሺህ ሪያል በማግኘት በሀገሪቱ ከፍተኛ ተከፋይ ናቸዉ።

ዳጉ_ጆርናል

ሀይሌ ስለ ጉዳዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግሯልናፒ የሚባለው ግለሰብ ሐዋሳ ላይ የፈጠረው ነገር እጅግ ከበዳ ነው እኛም በCCTV የተቀረፀውን ቪዲዮውን እንለቀዋለን::የSecurity ማናጀሩን ናፒ ...
17/01/2024

ሀይሌ ስለ ጉዳዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግሯል

ናፒ የሚባለው ግለሰብ ሐዋሳ ላይ የፈጠረው ነገር እጅግ ከበዳ ነው እኛም በCCTV የተቀረፀውን ቪዲዮውን እንለቀዋለን::

የSecurity ማናጀሩን ናፒ የሚባለው ግለሰብ በቦክስ ሆዱ ላይ መቶታል የሰራተኛዎቼን ትእግስት አለማድነቅ አያቻልም:: እኔ ራሱ ማን እንደሆነ አላውቀውም ነበር ወታደር ሲጎነትል ቪዲዮ አሳይተውኝ ነበር እሱም ትክክል አይደለም::

አመጣጡ የኛን ስም አጥፍቶ ዘወር ለማለት ነበር ወደ ሀገሩ ሲሄድ ብዙ ስም ሊያጠፋ ሰለሚችል
ሲረብሽ ና ሰራተኞችን ሲማታ የተቀረፀውን ቪዲዮ እኛም ለህዝቡ እንለቀዋለን:: ኢትዮጵያውያን Prank ነው እያሉ ዝም ብለው ባይስቁለት ደስ ይለኛል::

እኛ እንግዳ ተቀባይ ህዝቦች ነን እንደዚህ አይነት ሰው ግን ስማችን ማጥፋት የለበትም ስማችን ለማጥፋት የሄደበት መንገድ ትክክል አይደለም ጉዳዩን ወደ ክስ ወስደነዋል ብሏል::

ሀይሌም በእንግሊዘኛ ለናፒ መልእክት ያስተላለፈም ሲሆን ስማ ናፒ
I know You don't want peace; you want problems.
However, we need peace, not problems.
ብሏል::😎

Via Seifu

ተወዳጁ የEBS የመዝናኛ ክፍል ባልደረባ አስፋው መሸሻ አረፈ!ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በሚዲያው ዘርፍ ረጅም ግዜ ኢትዮጵያንን በራዲዮ እያዝናና ቁምነገር በማስተማር ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን ከ...
14/01/2024

ተወዳጁ የEBS የመዝናኛ ክፍል ባልደረባ አስፋው መሸሻ አረፈ!

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በሚዲያው ዘርፍ ረጅም ግዜ ኢትዮጵያንን በራዲዮ እያዝናና ቁምነገር በማስተማር ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን ከሀገር ውጭ ከወጣም በኃላ ኑሮ በአሜሪካ የተሰኜ አስተማሪ ፕሮግራም ለኢትዮጵያን ሲያቀርብ የነበረ ተወዳጅ ጋዜጠኛ ነበር

ከውጭ ሀገር ተመልሶም በEbs የእሁድ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ ዝግጅቶችን በማቅረብ እጅግ ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻለ የጋዜጠነትን ስነ ምግባር በአግባቡ የተላበሰ በሳል ጋዜጠኛ ነበር!

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ በዛሬው እለት ማረፏ ተስምቷል!
ለመላ ቤተሰቦቹ እና ወዳጅ መጽናናትን ይመኛል።

ስህተት እስካልሰራህ ድረስ በአላማህ ፀንተህ ቁም! 🌼🙏🏾
10/09/2023

ስህተት እስካልሰራህ ድረስ በአላማህ ፀንተህ ቁም! 🌼🙏🏾

ልጅ ሚካኤልም በመጨረሻስህተት እስካልሰራህ ድረስ በአላማህ ፀንተህ ቁም! እንዳትፈራ እልፍ ሆኖ ቢመጣ የሳተ ወጀብ ብቻህን ቅር እንጂ አብረህ አትወጀብ! እኔ የወጣሁበት ማህበረሰብና አካባቢ እ...
10/09/2023

ልጅ ሚካኤልም በመጨረሻ
ስህተት እስካልሰራህ ድረስ በአላማህ ፀንተህ ቁም! እንዳትፈራ እልፍ ሆኖ ቢመጣ የሳተ ወጀብ ብቻህን ቅር እንጂ አብረህ አትወጀብ! እኔ የወጣሁበት ማህበረሰብና አካባቢ እንኳን ትልልቅ የነብስና የስጋ አባቶችን ይቅርና እኩያ ወንድሞችን እንኳን አለማክበር ሰፈሩ ፈፅሞ አይፈቅድም! አዲስ አበባም ላይ ካሉ የትኛውም ቦታዎች ቢሆን ብዙ ደብራትም ያሉት እኛ አካባቢ ላይ ይመስለኛል ሆኖም በዛ ውስጥ እንዳለፈና እንዳደገ ሰው የትኛውንም ስህተት ብሰራ ብዙ ሰርቼም አቃለሁ ግን ታላላቆቼን ተሻግሬ አላቅም! ለዛም ነው የአካባቢዬና በኛ ሰፈር ዙሪያ ያሉ እንዲሁም ከተማ ላይ ያሉ አሪፍ አሪፍ ሰው አክባሪና ሀይማኖታቸውን አክባሪ ልጆች ለጠየቁኝ ጥያቄ እነሱጋ ያለውን ተናግረው እኔጋ ያለውን አስረድቼ ከብዙዎቹጋ የተግባባነው! እንደው ቢሆን ጥሩ ነበር ግን ሁሉም ደጅ አይሰጣም እንጂ!! ሆኖም በዚ ሁሉ መንገድ አብራችሁኝ ለነበራችሁ አብሮ አደጎቼ የ 06 ኮሪያ ሰፈር ጤና ቡድን ልጆች የ 09 የጃል ሜዳ ልጆች እንዲሁም በሁሉም አካባቢ በውስጥ መስመርም በአካልም ያገኛችሁኝ ወዳጆች እጅግ አድርጌ እያመሰገንኩ አሁንም ወደፊትም ቢሆን እያወኩና እናንተንም እኔንም ከሀቅ ውጪ እሚያሳዝንና እሚያሳጣ ድርጊት አረጋለሁ ብዬ አላምንም:: አብራችሁኝ ስለነበራችሁ በድጋሚ እያመሰገንኩ በሀገርም ከሀገርም ውጪ ላላችሁ ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ ጏደኞችና ኢትዮጵያውያን በሙሉ መጪው ዐመት የፍቅርና የመተሳሰብ ከሁሉ በላይ ደሞ የሠላም እንዲሆንልን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!! መልካም ቀን መልካም አዲስ አመት 🌼🌼🌼🙏🏾

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alem endat aderech አለም እንዴት አደረች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Alem endat aderech አለም እንዴት አደረች:

Share

Category