Hãbţĩŝh G.Gĩŕmã

Hãbţĩŝh G.Gĩŕmã Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hãbţĩŝh G.Gĩŕmã, Digital creator, Addis Ababa.

 !በገረሴ ከተማ የአከባቢው ተወላጅ የምሁራን የሰላም፣የአንድነትና የልማት ጉዳዮች የምክክር መድረክ
12/05/2025

!
በገረሴ ከተማ የአከባቢው ተወላጅ የምሁራን የሰላም፣
የአንድነትና የልማት ጉዳዮች የምክክር መድረክ

27/04/2025

የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና።”
— ማቴዎስ 3፥3

በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ።የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማርያና ሪፐራል ሆስፒታል !!
17/06/2024

በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ።
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማርያና ሪፐራል ሆስፒታል !!

🏃🏃ለሁሉም ከተማ አስተዳደርና ወረዳዎች🏃🏃👉URGENT🙏🕞/በጣም አስቸኳይ መልዕክት አሁን ከክልል የደረሰን/በሀገር አቀፍ ደረጃ የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ክልሉን የሚ...
18/01/2024

🏃🏃ለሁሉም ከተማ አስተዳደርና ወረዳዎች🏃🏃
👉URGENT🙏
🕞/በጣም አስቸኳይ መልዕክት አሁን ከክልል የደረሰን/
በሀገር አቀፍ ደረጃ የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ክልሉን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመመልመል ከጥር 13/2016 እስከ 17/2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በክልል ደረጃ ሁሉም ዞኖች የሚሳተፉበት የአትሌቲክስ ውድድር ይካሄዳል።
በመሆኑም በዚህ ውድድር መሳተፍ ታዳጊዎችና ተተኪ ስፖርተኞች በአትሌቲክስ ዘርፍ ክለብ የመግባት ዕድል የሚያገኙበት መድረክ ነውና የጋሞ ዞንን ሊወክሉ የሚችሉ ስፖርተኞችን ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በዓልን ምክንያት ሳናደርግ ስፖርተኞች ይህ ዕድል እንዳያመልጣቸው በማድረግ ከጥር 11 - 12 ለሁለት ቀን ወደ ዞን ይዛችሁ በመምጣት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ታስመርጡ ዘንድ ይህ ጥሪ ተላልፏል።
ምልመላ የሚካሄድበት የስርት ዓይነት:-
1, በውርወራ (አሎሎ፣ ድስከስና ጦር ውርወራ)
2, በዝላይ (ርዝመት ዝላይና ከፍታ ዝላይ)
3, በሩጫ ከ100ሜ-10,000ሜ (100ሜ፣ 200ሜ፣ 400ሜ፣ 800ሜ፣ 1500ሜ፣ 5000ሜ እና 10,000ሜ)
ምልመላው የሚካሄደው በሁለቱም ፆታ ነው!

የገረሴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት እና ደረጃ ለማሳደግ የሀብት አሰባሰብ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው።የገረሴ ከተማ አስተዳደር የገረሴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሀብት አሰባሰብ ንቅናቄ ለማ...
13/01/2024

የገረሴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት እና ደረጃ ለማሳደግ የሀብት አሰባሰብ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው።
የገረሴ ከተማ አስተዳደር የገረሴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሀብት አሰባሰብ ንቅናቄ ለማካሄድ አብይ ኮሚቴ የማቋቋም እና የሀብት አሰባሰብ ዕቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የገረሴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሰይፉ ዎናቃ፣ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ አስራት፣ የገረሴ ከተማ አሰተዳደር አስተባባሪ አካላት፣ የገረሴ ዙርያ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካሳሁን ካማ እና የአስተባባሪ አካላት፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የጋሞ ልማት ማህበር፣ አርባምንጭ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ እና በአርባምንጭ ያሉ የገረሴ እና አካባቢ ተወላጆች ተገኝተዋል።
አቶ ሰይፉ ወናቃ የጋሞ ዞን ጤና መምርያ ኃላፊ እና የገረሴ መጀመርያ ደረጃ ሆስፕታል ቦርድ ሰብሳቢ ባደረጉት ንግግር የቦርድ ሰብሳቢ ከሆኑ ለሦስተኛ ዙር መምጣታቸውን ገልጸው ለህብረተሰቡ ከሚሰጠው አገልግሎት እና የህብረተሰቡ ፍላጎት ለማርካት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን ቦርዱ ተወያይቶ የተሻለ ቁሳቁስ እና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ደረጃውን ከፍ ለማድረግ መታሰቡን ገልፀዋል።
የተሻለ የጤና አገልግሎት ማግኘት የሕዝቡ ደሞክራሲያዊ መብቱ በመሆኑ ጥራት ያለው እና ፍትሃዊ ጤና አገልግሎት ለማግኘት የህብረተሰቡን ተሳትፎ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
አቶ አለማየሁ አሥራት የገረሴ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ እና የገረሴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ በበኩላቸው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሆስፒታሉ ስመሠረት በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፊተኛ ሀብት በማሰባሰብ የውስጥ ቁሳቁስ በማሟላት ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ ከፊተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።
በ2015 ዓ.ም የተቀረጸው የሀብት አሰባሰብ ፕሮጀክት በሆስፒታሉ ቦርድ የጸደቀ ሲሆን ዛሬ አብይ ኮሚቴው ተወያይቶበት ያጸድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የሀብት አሰባሳቢ አብይ ኮሚቴ መተዳደሪያ ደንብም እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

ይህ ከታች በፎቶ የሚትመለከቱት ዱር እንስሳት በጋሞ ዞን ማዜ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ ናቸው፡፡Maze National Park! in Gamo ZoneThe Maze national park was est...
12/01/2024

ይህ ከታች በፎቶ የሚትመለከቱት ዱር እንስሳት በጋሞ ዞን ማዜ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ ናቸው፡፡
Maze National Park! in Gamo Zone
The Maze national park was established in 1997 E.C /2005/. The distance of Maze NP from Addis Abeba and Hawassa is 468 km and 248 km respectively. The MNP is surrounded by 5 wordas. These are Kucha, Alpa kucha, Daramalo and Kamba Wordas are found in Gamo zone, Zala worda is Gofa zone.
The maze national park passed two phases before it gets the naming maze national park, the first phase during this time becomes a controlled hunting area. To create a chronological time sequence b/n first and second phases, there is no exact time. The second phase is called a wildlife reserve area. Again, this time span is long before the park bears the naming maze national park.
The total surface area of the park is 202 km2. The largest area coverage of the park is plain topography. The rainfall extends from March to September, among these months there is variation in rainfall in the area. From December to February, there is little or no rainfall.
The park fortune possesses a number of rivers and streams which ultimately drain into Omo river. The name of the park is derived from the river called the maze river. The maze river has a number of tributaries, these are dumb, sage, llamas and Doha.
Maze national park is endowed with a large number of wildlife. It is much more pronounced over natural attraction. These are vegetation and animals. Vegetations:- the park is covered by the savannah grassland with scattered deciduous broad-leaved trees as well as riverine forest association along the main water courses. No endemic plant is registered.
Wild animals: the park embraces a large number of wild animals. There are different kinds of wild animals including the endemic animal. The park supports a large number of precious animals so-called Swayne's hartebeests. So far, 39 large and medium-sized mammals and 196 birds, ships have been recorded.

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።የጋሞ...
25/12/2023

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።
የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ደበበ ወንቴ መምሪያው ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ ባከናወኑት ክትትል በሰው ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ገልፀዋል።
በቀን 14/4/2016 ዓ.ም መነሻውን ሻሸመኔ በማድረግ አርባምንጭን አቋርጦ ወደ ኬንያ ድንበር ሲጓዝ የነበረ የሠሌዳ ቁጥሩ ኦ-ሮ ኮድ 3- 22382 አይሱዙ FSR የጭነት መኪና ከሌሊቱ 8 ሰዓት አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ኤልጎ ቀበሌ ሲደርስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ተናግረዋል።
ተሽከርካሪው መሠል ህገ-ወጥ ተግባር ለመፈፀም እና በቀላል ፍተሻ ሊገኝ የማይችል ተጨማሪ የመጫኛ ክፍል በስውር መኪናው ላይ ማሰራቱን የገለፁት ኢንስፔክተር ደበበ በዚሁ ክፍል ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 105 ጥቅል አደንዛዥ ዕፅ ጭኖ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።
የመኪናው አሽከርካሪ ለጊዜው የተሰወረ ሲሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት ከአከባቢው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት ጥብቅ ክትትል እያደረጉ መሆኑንም አመላክተዋል።
አደንዛዥ ዕፅ በተለይ አምራች ኃይል የሆነውን ወጣቱን ክፍል ወደ አልተፈለገ ነገር በመምራት ወንጀል እንዲስፋፋ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ያሉት የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ህብረተሰቡ መሠል ድርጊቶች ሲገጥሙት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲያደርስም አሳስበዋል።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ በዞኑ የሚፈፀሙ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በመከላከል የህብረተሰቡን ሠላም ለመጠበቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝም ኢንስፔክተር ደበበ ጠቁመዋል።

መልካም  አዳር !!
28/09/2023

መልካም አዳር !!

መልካም ቀን ❗
16/09/2023

መልካም ቀን ❗

ከጋሞ ጨንቻ እስከ ቅዱስ ጊዮርጊስፈረሰኞቹ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀዋልአስቀድመው ጥቂት ተጫዋቾችን ያዘዋወሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ዛሬ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።በአፍሪ...
13/09/2023

ከጋሞ ጨንቻ እስከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈረሰኞቹ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀዋል
አስቀድመው ጥቂት ተጫዋቾችን ያዘዋወሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ዛሬ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።
በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ወደ ሁለተኛው ዙር ማጣሪያ የተቀላቀሉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አስቀድመው የተወሰኑ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ በመቀላቀል በርካት ያሉ የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል ማራዘማቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ ከአርባምንጭ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረማቸው ተረጋግጧል። ፈረሰኞቹን የተቀላቀሉት ሁለቱ ተጫዋቾች ተከላካዩ አሸናፊ ፊዳ እና አማካዩ እንዳልካቸው መስፍን ናቸው።
አሸናፊ ፊዳ ከአርባምንጭ ተስፋ ቡድን የተገኘ ሲሆን ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአርባምንጭ ከተማ ቆይታ ማድረጉ ይታወቃል። እንዳልካቸው መስፍን በበኩሉ ከዚህ ቀደም ለአንድ ዓመት ለጋሞ ጨንጫ ሲጫወት ቆይቶ ሁለቱን ዓመታት በአርባምንጭ ከተማ ቆይታ ያደረገ ሲሆን የታላቅ ወንድሙ ሙሉዓለም መስፍንን ፈለግ በመከተል ፈረሰኞቹ ቤት መቀላቀሉ ታውቋል።
ለሁለት ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት ለመቆየት የተስማሙት ሁለቱ ተጫዋቾቹ በርከት ያሉ ተጫዋቾቻቸውን ላጡት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በቦታቸው ጥሩ አማራጭ ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንኳን አድሱ  ዓመት ለ2016ዓ.ም  በሰላም አደረሰህ/ሽ/ሳችሁ!!! አድሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣የመተሳሰብ፣የአንድነት ፣ የአብሮነት ፣ የመረዳዳት፣ የጤና እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እመኛ...
12/09/2023

እንኳን አድሱ ዓመት ለ2016ዓ.ም በሰላም አደረሰህ/ሽ/ሳችሁ!!!

አድሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣የመተሳሰብ፣የአንድነት ፣ የአብሮነት ፣ የመረዳዳት፣ የጤና እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡

አድሱ ዓመት ፉጹም ይቅርታ በሰፈነበት ልቦና የተቀያየምን የሚንታረቅበት በንጹህ ህልውና ዘመኑን የሚንቀላቀልበት አሮጌውን ዘመን በሰላም ሸኝተን አድሱን ደግሞ ሞቅ ደመቅ አድርገን የሚንቀበልበት ዘመን ያድርግልን ፈጣሪ።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
መልካም በዓል
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hãbţĩŝh G.Gĩŕmã posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hãbţĩŝh G.Gĩŕmã:

Share