29/09/2025
📌 "ጎረቤቶቻችን አሁንም ራሳቸውን ለድርድር ዝግጁ ቢያረጉ መልካም ነው!
ጠ /ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ
የባህር በርን በተመለከተ የዐቢቹ ቃል እየተፈፀመ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዳሴ ግድቡ ምርቃት ላይ ሲናገሩ "ጎረቤቶቻችን በፈጠነ ጊዜ ራሳቸውን ለድርድር ዝግጁ ቢያረጉ መልካም ነው" ብለው ተናግረው ነበር፡፡ንግግሩ ይመለከተቸዋል የተባሉት ኤርትራ እና ሶማሊያም ፈጠን ያለ መልስ ሰጥተዋል፡፡የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀገራቸው በወደብ ጉዳይ በጋራ ለመጠቀም ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህም ሰሞኑን ከተመድ ስብሰባ ጎን ለጎን ከአሜሪካ ልዩ የአፍሪካ ቀንድ መልእክተኛ ጋር ባደረጉት ውይይት "ስለ ቀጠናዊ ጉዳዮች መክረዋል" ተብሏል፡፡ምናልባትም አሜሪካኖቹ ኤርትራውያኑን በወደብ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ለምን አትነጋገሩም!?" ሳይሏቸው አይቀርም፡፡ለወትሮው ስለወደብ ጉዳይ ሲጠየቁ "በሉአላዊነት ላይ ድርድር የለም" የሚሉት የአስመራ ሰዎች እንዲህ አይነት "መደራደር እንችላለን" የሚል ትርጉም ያለው ለዘብ ያለ መልስ ለምን ሰጡ? ከተባለ አንድም ኢትዮጵያ ነገሩን አጠንክራ ስለያዘች እና ወደ ጦርነትም ልትገባበት እንደምትችል ስለገመቱ ይመስላል፡፡ጦርነት ከተገባ ደግሞ ነገሩ ዝቅ ሲል ለኢሳያስ አፈወርቂ የስልጣን ህልውና ከፍ ሲል ለኤርትራ ዘላቂ ህልውና ብዙ አደጋዎችን ያነገበ ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡
በሌላ መልኩ ኤርትራውያኑ "እንደራደራለን" አይነት መልስ የሰጡት አሜሪካውያኑን እና አውሮፓውያኑን ለማዘናጋት እና ጊዜ ለመግዛት ወደፊትም ነገሩ ወደ ጦርነት ከሄደ "እኛኮ ሲጀመር የሰላም አማራጮችን ሁሉ እሺ ብለን ነበር" ለማለት ነው እንጂ ከልባቸው እንዳልሆነ የታወቀ ነው፡፡ሶማሊያውያኑም ሆነ ኤርትራውያኑ አሁን "በጋራ መጠቀም" የሚሉት ሀሳብ ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ጋር ካላት "የወደብ ኪራይ" አሰራር ብዙም አይለይም፡፡ኢትዮጵያ ደሞ የፈለገችው የኪራይ ወደብ ሳይሆን የራሷን የባህር በር ነው፡፡ይሄ በሰላማዊ መንገድ ሊገኝበት የሚችልበት እድል ጨርሶ የለም ባይባልም ግን አናሳ ነው፡፡
እና ምን ተሻለ? አገራችን በሰላም አማራጭ በሰጥቶ መቀበል መርህ የሚገኝ የባህር በር ካለ ጦርነት ምርጫዋ አይደለም፥ ግን አሁን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው የባህር በር ጥያቄው ከጎረቤትም ሆነ ከሀያላኑ ዘንድ ትኩረት አግኝቷል፡፡
#ዐቢቹ
#ኢትዮጵያ