
30/05/2025
የፌዴራል ተቋማት እና ማህበራት አጀንዳ ማሰባሰብ የቡድን ውይይት ተጀመረ
*************
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት የጀመረው የፌዴራል ተቋማት እና ማኅበራት አጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ የቡድን ውይይት ተጀምሯል፡፡
በቡድን ውይይቱ ተቋማትን እና የተለያዩ ሕብረተሰብ ከፍሎችን ወክለው በመድረኩ የተገኙ አካላት የወከሉትን ማኅበረሰብ እና ተቋምን አጀንዳ በጥልቀት ያነሳሉ፡፡
የቡድን ውይይቱ የተጀመረው በየቡድኖቹ ሰብሳቢ እና ፀሐፊ በመምረጥ ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹ ከወከሉት ማኅበረሰብ እና ተቋም አንጻር ሊያዝ ይገባል የሚሉትን አጀንዳ በነጻነት የሚያነሱ ይሆናል፡፡
የቡድን ውይይቱ እስከ ነገ ከሰዓት የሚቆይ ሲሆን፣ እሁድ ሁሉም የተግባባቸው አጀንዳዎች ተደራጅተው ለኮሚሽኑ የሚቀርቡ መሆናቸውን የወጣው መርሐ ግብር ያሳያል፡፡
በለሚ ታደሰ
#ምክክር