Teselonke media

Teselonke media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Teselonke media, News & Media Website, Addis Ababa.

30/08/2024

በቃ ሄቨን ተረሳች???

19/08/2024

«ብር ሳይሆን ለአንቺ ክብር ያለው ወንድ አግቢ!»
:
:-
:
➊.ህይወትሽ የሚደምቀው በፍቅር እንጂ በብር አይደለም፣

↪ገንዘብን በማንኛውም ሰአት ከሰራሽ ልታገኚው ትችያለሽ፣

↪ፍቅር የሚገኘው ግን ከፈጣሪ ነው፣

↪ስለዚህ አብዝተሽ አምላክሽን ለምኚ።

➋.ወንድን ልጅ ከወደደሽ ራሱን ይሰጥሻል።

►ይህ ማለት ደግሞ አንቺ አንደፈለግሽ አንገት ሆነሽ ታዞሪዋለሽ፣

➌.ብዙ ሀብት ኖሮት ምንም ስብእና ወይም ላንቺ ክብር ከጎደለው ሰው ጋር አይደለም ትዳር ለአንድ ቀን አብሮ ለመዋል እንዳትመኚ።

➍.በማስመሰል እራሱን ደብቆ ከሚመጣ አስመሳይ ወንድ ወጥመድ እንዳትገቢ ጥንቃቄ ይኑርሽ።

↪ምክንያቱም ብዙ ወንድ በማስመሰል የሚፈልገውን እስኪያገኝ የማይፈልገውን ያደርጋልና።

↪እንዲህ አይነቱን ወንድ በኑሮ ሂደት እንደ እስስት ሲቀያየር ትመለከችዋለሽ።

➎.በውሳኔው የማይጸና እና አቋም የሌለው ሰው ላይ ብትወድቂ እድሜሽን በሙሉ ስትንከራተቺ ትኖሪያለሽና እንደዚ አይነቱን ወንድ ለማስተካከል ካልችልሽ በትዳር እንዳትታሰሪ ጠንቃቃ ሁኚ።

➏.ደስታ የሚገኘው የውስጥን ፍላጎት በነጻነት መግለጽ ሲቻል ነውና ነጻነትሽን የሚነፍግ ፍልጎትሽን የማይጠይቅ ወንድ ገና ሲጀመር አትቅረቢው።

►ምክንያቱም እንደዚህ አይነቱ ወንድ ምንጊዜም እራሱ የሚያወራውን እንጂ አንቺ የምታወሪውን አይሰማም፣ ቢሰማም ቦታ አይሰጠውም፣ እርሱ በወደደው እንጂ አንቺ በመረጥሽ መንገድም አይጓዝምና።

➐.አንቺ ለምትናገሪው ለምታደርጊው ነገር ስህተት ቢመስለው እንኳን በቀስታ እንጂ ጮሆ የሚናገር ወዳጅ አታበጂ።

►ምክንያቱም ዛሬ ከጮኸብሽ ነገ ሊመታሽ እጁን የማያነሳበት ምንም ምክያት የለውምና።

➑.ከሀብት ከቁሳቁስ በላይ ንጹህ ልቡን ንጹህ ፍቅርን የሚሰጥሽን ወንድ ተመኚ።

►ምክንያቱም የሁሉም መሰረቱ ፍቅር ነውና።
:
➒.የወንድን ያለውን ሀብት ወይም ኪሱን ሳይሆን ይዞ የመጣውን ንጹህ ፍቅር ተመልከች።

↪ምክንያቱም እንደዚህ አይነቱን ወንድ ትልቅ ዛፍ ሆኖ ሊጠልልሽ ፍሬ ሊሰጥሽ ይችላልና።

↪ምክንያቱም የሁሉም መሰረቱ ፍቅር ነውና።

➓.ደስተኛ የሆነ ህይወት ከፈለግሽ ግን እህቴ ሁል ጊዜም አስተውይ ብር ሳይሆን ለአንቺ ክብር ያለው ወንድ አግቢ።

#አምላክ ከወረት ፍጹም የጸዳ ንጺሕ ፍቅር ያድለን!(አሜን)
:
"በንጹሕ ፍቅር ያቆየን"

 ! !በድብደባ አንድ አይኑን ያጣው አትሌት አደጋው እንዴት ደረሰበት?!    | የ17 አመቱ አትሌት ሰው መሆን ታሪኩ፤ ፔሩ ለሚካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች  ለሀገር ውክልና ተመርጦ ፌ...
19/08/2024

!

!




በድብደባ አንድ አይኑን ያጣው አትሌት አደጋው እንዴት ደረሰበት?!

| የ17 አመቱ አትሌት ሰው መሆን ታሪኩ፤ ፔሩ ለሚካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች ለሀገር ውክልና ተመርጦ ፌደረሽኑ ባዘጋጀላቸው ሆቴል በዝግጅት ላይነበር ። በዚህ ሁኔታ እያለ ባለፈው እሁድ የከሰዓት በኋላ ፕሮግራም ለመስራት ወደ ጫካ ወጣ ብሎ ልምምዱን ጨርሶ ያቀዘቅዛል ። በዚህ ሁኔታ አንድ ሰው ወደ አትሌቱ ይቀርብና ፓሊስ ነኝ በማለት ፤
' እዚህ አካባቢ ቁማር የሚጫወቱ ታውቃለህ ' በማለት ይጠይቃል ። አላውቅም ብሎ እንደመለሰ ወዲያው በፍጥነት አንገቱን ሲይዘው አትሌቱም እራሱን ለመከላከል ጥረት ያፈርጋል ።

ሌሎች ሁለት ሰዎች በድነገት በመምጣ በሁለት በድንጋይ ጭንቅላቱን በመምታ አልወድቅ ሲል በሽጉጥ አይኑን ተኩሰው ከመቱት በኋላ በኪሱ ያለውን ሞባይል በመውስድ እንደተሰወሩ ጓደኛቹ ለኢትዮ ራነርስ ገልፀዋል። ጉዳቱም ከፍተኛ ነው።

አትሌቱ በዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ ሲሆን የፌደረሽን ሰዎች እየመጡም እየጠየቁት እንደሆነ ለህክምና የሚወጣውን የወጭ ደረሰኝ ያዙ ማንኛውንም ወጪ እንሸፍናለን በማለት በቃል እንደነገሯቸውም ጓደኞቹ ለኢትይ ራነርስ ገልፀዋል።

ልጁ ለሀገር ውክልና ተመርጦ ባለበት ሁኔታ ነውና አደጋው የደረሰበት ሙሉ ሀላፊነት ፌደረሽኑ ይወስዳል ብለን እንገምታለን።

ምን አልባት በፓሪስ በመጣው ውጤት የተበሳጩ ሌቦች ሊሆኑ ስለሚችሉ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴም ህክምናው ላይ እጁን ያስገባል የሚል ግምት አለን።

ኢትዮራነርስ የአትሌቱን ሁኔታ እስከ መጨረሻው እየተከታተለ መረጃውን ለአትሌትክሰሰ ቤተሰቦች ያደርሳችኋል።

Via Ethio runners

ምን ማለት ነዉ???በሕፃን ሔቨን ጉዳይ የተጀመረው የሚዲያ ዘመቻ እንዲቆም የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ጠየቀማህበሩ እንዳለው የወንጀል ክርክር ሂደቱ ገና ያልተጠናቀቀ በመሆኑ የሚዲያ ዘመቻው ...
19/08/2024

ምን ማለት ነዉ???
በሕፃን ሔቨን ጉዳይ የተጀመረው የሚዲያ ዘመቻ እንዲቆም የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ጠየቀ

ማህበሩ እንዳለው የወንጀል ክርክር ሂደቱ ገና ያልተጠናቀቀ በመሆኑ የሚዲያ ዘመቻው የዳኝነት ነጻነትን የሚጋፋ ነው ብሏል

የ7 ዓመቷ ህጻን ሔቨን ከአንድ ዓመት በፊት በባህርዳር በተፈጸመባት የአስገድዶ መደፈር ህይወቷ አልፏል ተብሏል

የ7 ዓመቷ ህጻን ሔቨን ከአንድ ዓመት በፊት በባህርዳር በተፈጸመባት የአስገድዶ መደፈር ህይወቷ አልፏል ተብሏል

19/08/2024

የልጁን ደፋሪ የዘር ፍሬዎቹን ቀጥቅጦ እና በእሳት ጠብሶ የገደለው አባት

👇🏾

ስሙ ለደህንነቱ ሲባል ያልተገለፀው የ36 አመት ህንዳዊ ሀገር ሰላም ብሎ የሚኖር ህይወቱን የሚያመሰቃቅል ነገር ገጠመው

የ13 አመት ልጁ እንደ ቤተሰብ ተቀብለው በሚያኖሩት እና ከተመሳሳይ መንደር ወደ ህንዷ ዋና ከተማ ደልሂ የመጣው ተከራይ እጇን አስሮ :አፏን አፍኖ እና ጉልበቱን ተጠቅሞ ደፈራት

"ለማንም ሰው ትንፍሽ ብትዪ አባትሽን እና እናትሽን እገላለሁ" ብሎ ያስፈራራት ህጻን በደሏን እና ህመሟን ይዛ ለማንም ሳትናገር ወራቶች ተቆጠሩ

**********

ከወራቶች በኃላ ይህች ታዳጊ የማቅለሽለሽ እና የህመም ስሜት ተሰምቷት አባት ወደ ሆስፒታል ሲወስዳት "ከማህፀን ውጪ እርግዝና ተፈጥሯል" ብለው አረዱት

ልጅቷ ደፋሪዋን ተናገረች: ድርጊቱ እንዴት እንደተፈፀመ አስረዳች - አባት እሳት ጎረሰ: እሳት ለበሰ

ጉዳዩን በሚስጥር የያዘው አባት ልጅቷን ወደ ቤት ወስዶ ለሚስቱ ከተከራዩ ጋር የማወራው ጉዳይ አለ ብሏት

ሚስትም እንደሁልጊዜው ሊጫወቱ ነው ብላ በራሷ ስራ ተጠምዳለች

***********

አባት የተከራዩ ክፍል ገብቶ ያደደረገው ድርጊት መላውን ህንድ ያስደነገጠ ሲሆን ብዙዎች "ጀግና" ሲሉት አወድሰውታል

👇🏾

በሩን ቆለፈ: ተከራዩን ያዘው: እጁን የፊጢኝ አሰረው: አፉ ውስጥ ጨርቅ ወተፈበት

ከዚያም ስቶቭን ለኩሶ ብረት እያጋለ የዘር ፍሬውን አስደግፎ አሰቃየው: በዚህ ብቻ አላበቃም ሰውዬውን ገደለው

በስተመጨረም እጁን ለፖሊስ ሰጠ

የደልሂ ፖሊስ አዛዥ ፍትህ በፖሊስ እጅ ናት ሲሉት አባት እንዲህ ብሎ መለሰ

👇🏾

“እኔ አባቷ የተሰማኝን ያህል የልጄን ህመም ፖሊስ አይሰማውም"

Via- Zemelak Endrias

18/08/2024
የመጨረሻዬ የኦሎምፒክ መረጃ ነዉ።
17/08/2024

የመጨረሻዬ የኦሎምፒክ መረጃ ነዉ።

ፍትህ ለዚች እናት
16/08/2024

ፍትህ ለዚች እናት

 #የዝንጀሮ ፈንጣጣ አውሮፓ ገባ‼️የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የዓለም አቀፍ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት እንደሆነ ካወጀ በኃላ ስዊድን የሚጀመሪያውን ኬዝ አግኝታ...
16/08/2024

#የዝንጀሮ ፈንጣጣ አውሮፓ ገባ‼️
የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የዓለም አቀፍ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት እንደሆነ ካወጀ በኃላ ስዊድን የሚጀመሪያውን ኬዝ አግኝታለች‼️
በቫይረሱ የተያዘው ሰው ወደ አፍሪካ የጉዞ ታሪክ አለው ተብሏል።
ፓኪስታንም በተመሳሳይ ሶስት በMpox ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ማግኘቷን ይፋ አድርጋለች። 3ቱም ቫይረሱ የተገኘባቸው ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ተጉዘው ፓኪስታን የገቡ እንደሆነ የሀገሪቱ የጤና ባለስልጣናት ገልጸዋል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ቫይረሱ በተለይም አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሳራጨ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜም በ4 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ኬንያ ፣ በቡሩንዲ ፣ በሩዋንዳ ፣ በኡጋንዳ ተገኝቷል።

በቫይረስ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው Mpox በወሲባዊ ግንኙነት ፣ በቆዳ ንክኪ ፣ በቅርብ ርቀት ሆኖ ማውራት / መተንፈስ ፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ባለ የቅርብ ግንኙነት ይተላለፋል።
እንደ CDC Africa መረጃ እስካሁን በአፍሪካ ከ500 በላይ ሰዎች በበሽታው ሞተዋል።
=================

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Teselonke media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share