Ethio news

Ethio news ፈጣን ዜና ከፍለጉ ፎሎ ያርጉ

13/04/2023
10/04/2023

ኃይል













 #አሁን" ኢፍጣራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።በዚሁ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተገኝ...
08/04/2023

#አሁን

" ኢፍጣራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዚሁ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተገኝቶ ስነስርዓቱን እየታደመ ነው።

https://t.me/ethionews45

 #ነዳጅ" ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት  #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈፀማል " - የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣንከሚያዚያ 16 ጀምሮ አዲ...
07/04/2023

#ነዳጅ

" ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈፀማል " - የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን

ከሚያዚያ 16 ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ገልጾ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም አሳውቋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ጀምሮ #በአስገዳጅነት እንደሚተገበር ተጠቁሟል።

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በ " ቴሌ ብር " ውጤታማ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።

ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በ " ቴሌ ብር " ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አመልክቷል።

የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መገንባቱንም አስረድቷል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር ደግሞ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ያለ ሲሆን በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን ይፈታል ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ሲል አሳውቋል።

#ኢዜአ

https://t.me/ethionews45

Address

አዲስ አበባ
Addis Ababa

Telephone

+251927398048

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio news:

Share