26/07/2022
" ዳግማዊ የሰው ልጆች አባት ነብዩላህ ኑህ "
- የመጀመሪያው የሰው ልጆች አባት አደም ( ዐ.ሰ ) ከሞቱ ከ1000 አመት በኋላ በረሱልነት የተላኩት ኑህ ( ዐ.ሰ) ናቸው።
- ሽርክ የተጀመረው በኑህ ዘመን ሲሆን ወደ አላህ በመጣራት ( በተውሂድ) ከ900 አመት በላይ ያሳለፉ ሲሆን ግን የሰለመላቸው( ያመነላቸው) 80 ብቻ ነው
- ከዚያም የዘንባባ ዛፍ እንድተክል አላህ አዘዘው። ዛፎቹ ከተተከሉ ቡኋላ ለ 40 አመት ሴቶቻቸው አይፀንሱም ነበር። አላህ 50 አመት ሲሞላቸው ዛፎችን ቁረጥ የሚል ትዕዛዝ ሰጠው። ከዚያም መርከብ ስራ የሚል ትዕዛዝ በመላኢካው ጂብሪል አማካኝነት መልዕክት ለኑህ መጣለት።
* ኑህ (ዐ.ሰ) የሰራው መርከብ
የጎን ስፍት = 800 ክንድ
ዕርዝመት = 1200 ክንድ
ከፍታ = 80 ክንድ ነበር።
- ኑህ መርከቧን ሰርቶ ሲጨርስ 80 አማኞችን፣ከቤት እና ከዱር እንስሳ አንድ ወንድ ና ሴት ጥንድ ጥንድ አድርጎ መርከቡ ላይ እንድጭን ታዘዘ።
- ኑህ ሁለት ሚስት ነበሩት አንዷ ሙስሊም ስትሆን ሁለተኛዋ ካፊር ነበረች እሱ ግን ሙስሊሟን ብቻ መርከቡ ላይ ጫነ።
- እንድሁም ኑህ 4 (አራት) ልጆቹን እንድጭን ተዘዘ ማለትም
1. ሳም = የአረቦች ፣ ሮም እና ፐርሺያ ዘሮች
2. ሐም = የቂብጥ ፣ በርበር እና ሱዳን ዘሮች
3. ያፈስ = የቱርክ ፣ ሶቃሊባ እና የዕጁጅ እና
መዕጁጅ ዘሮች
4. ከነዐ
- ከዚያም ነብዩላህ ኑህ ( ዐ.ሰ) ልጆቹን መርከቧ ላይ እንድወጡ አዘዟቸው ነገር ግን ሶስቱ እሽ ብለው ሲወጡ ከነዐ እንቢ አልወጣም አለ። ሁሉም መርከቧ ላይ ቦታቸውን ሲይዙ ፀሀይ ብርሃኗን ተነጠቀች፤ ሰማይም ዶፍ ዝናቧን ማውረድ ጀመረች ፤ መሬትም የያዘችውን ውሀ ተፍች መሬትም በጎርፍ ተጥለቀለቀ።
- ኑህ መርከቧ ላይ ሁኖ ወደታች ሲመለከት ከነዐ ልጃቸው በጎርፍ ውስጥ ሲባክን አዩት ኑህም ልጄ ሆይ ና መርከቧ ላይ ውጣ ትድን ዘንድ አሉት ልጁም ከተራራ ላይ እወጣለሁ እንቢ አለ። ኑህም አላህ ካዘዘው ዛሬ የሚቀር የለም እሱ ያዘነለት ቢሆን እንጅ አሉት። ወዲያውኑ ከተራራ ላይ ማዕበል ጎርፍ ተነስቶ ከነዐን ልጃቸውን እና መሬት ላይ ያለ ሁሉ ጠፋ መርከቧ ላይ ያሉት ብቻ ሲቀሩ።
- በመጨረሻም ለ 40 ቀን መሬት በጎርፍ ከተጥለቀለቀች ቡሃላ መርከቧ " ጁዲይ " በተባለ ተራራ ላይ አረፈች። አማኞችም ከጎርፍ ማዕበል ድነው ህይወታቸውን በኢባዳ ማሳለፍ ቀጠሉ።
ማሳሰቢያ፦ ከነብዩላህ ኑህ ታሪክ የምንረዳው ለተውሂድ እና ለእያንዳንዱ የዕለት ተዕለት ህይወታችን ሶብርና በአላህ መመካት ወሳኝ እንደሆነ ያስተምረናል።
አላህ በ ነብዩላህ ኑህ ላይ ሰላም ያስፍን
ምንጭ፦ ከነብያት ታሪክ የተወሰዴ