30/10/2025
ከንስሃ ቀጥሎ እንደ ማጣት ሰውን ጭዋ ሚያረግ ነገር የለም man, laterally በቃ ገራሚ code 2 ነው የሆንኩት, ቀን ቀን ወጥሬ እሰራለው ማታ ላይ ያን የመገናኛ taxi ሰልፍ ብርክ ብርክ እስኪለኝ እሰለፋለሁ ቤት ስገባ marathon የሮጥኩ ይመስል ድክም እላለሁ, እራት ለመብላት ለራሱ moral አይኖረኝም....በቃ ከ corona ጀምሮ የ'lifeኤ heatmap ቢታይ ደማቅቅቅ አንድ መስመር ነበር የሚወጣው, ከስራ ወደቤት ከቤት ወደስራ, ዥዋዥዌ የሆነ life
ስልህ ፈልጌው አደለም እኮ, ግርጣት ነው እነደዚ የጡረተኛ life የሚያስኖረኝ.... man እንደኔ አለሌ plus የዋህ የለምምም ነው ምልህ.....ሰው እየጋበዝኩ ያለኝ ብር እንደ የተጠመደ ቦንብ የፈጠነ ነው ወደሁዋላ ማስቆጥረው....ለነገሩ የዋህ ሆኜ አደለም, እንደምችል ሰው እንዲያቅልኝ ነው ገባሃ...ሁሌ 6በ4 የሆነች ምሳ እቃ ከመያዝ አልፎ መጋበዝ እንደምችል ለማሳወቅ ነው
ታዲያ የሆነ diaspora ጀለሳችን መጣ እና " i wanna see addis in night" አለኝ and i said "me to"......diaspora አልመስልም እንደዚ ስል? ለነገሩ በቦሌ አራብሳ passport አዲሳባ የምኖር ፍሪክ ነኝ
ወጣነው club, እኔ ማቀው ድሮ club ከመውጣትህ በፊት cost and benefit analysis ሰርተህ ነው ምትወጣው, ማለት ማታ 1ስዓት ሲሆን የሆነች ግሮሰሪ ገብተህ ቢራህንም ስዓትህንም በአሪፉ ትገፋና ወደ ዋናው game ሄደህ "ግማሽ Gordon" ብለህ ዛር እና ቆሌህን አራግፈህ ትወጣለህ....ኡኡኡኡኡ እግረኛ ሆነህ over ደሞ ሌላ አስከፊ የህይወት ገፅታ ነው
diasporaው ጀለስ ግን መሸት ሲል የሆነ ቁርጥ ቤት ወስዶ የሚገርም ጉዝጉዋዝ አበላን....እኛ ቤት እኮ kilo ስጋ 6 ብረድስት ወጥ ነው የሚወጣት, እዚ ግን በግላጭ አገኝሁት, ብሶቴን ተወጣሁበት....እዛው እየተጫወትን አመሽተን ትንሽ ሰዓቱ እንደ ሄደ "let's go to the club" አለች ጀለስ, ከተማው ውስጥ አለ የተባለ club
ሄደን, ለወትሮ ሁሌ አንድ ጠርሙስ ቢራ እየያዝኩ እያስቸገርኩ በጋርድ ታንቄ ምወጣዉ ልጅ አሁን ሞቅ ባለ ሰላምታ ገባሁ
ሄደንም እነዚ የብረታብረት ጠርሙስ ወረዱ, ጀማውም አያሳፍርም እንደ እስፖንጅ ይመጠዋል, እኔም ልክ ኩንታ ኩንቴ ከባሪያነት ነፃ የወጣ ይመስል ጃኬቴን አውጥቼ አውለበልበዋለው......don't call me ሰገጥ, i mean it's been awhile እንደዚ ዓለሜን ካየው, አትፍረዱብኝ.... እከፍላለው ሳትል እንደመጠጣት ደስ የሚል ነገር የለም man.... one of the best night አሳልፈን
ሂሳብ ተብሎ መጣ
...."telebirr ይቻላል?......"cbebirr ስ?....."share ላርጋ"....."እስቲ bill ልደምር"....ምናምን እያልኩ አቧዋራ አስነሳው, then total ቢሉን ሳየው ብርድ ብርድ አለኝ, አደለም ደሞዜ የ3 አመት እቁብ ቢደርሰኝ ለራሱ የቢሉን ሂሳብ አይመጣም....ነብሴ ተጨነቀ diasporaው ባይይዝስ ብዬ....manዬም ምንም አልመሰለውም ስልኩን ላጥ አርጎ ከፈለ......like ቀጥታ ነው ጥያቄ መጠየቅ የጀመርኩት....
"እንዴት America ሄድክ?"
"አሪፍ ይከፈላላ እዛ?"
"በ libya ብሞክር እደርሳለው?"
"በተወደደ ኑሮ ሁለት ኩላሊት መያዜ ጥቅሙ እየታየኝ አይደለም, አንዱን ባንቀለቅለው America አያስገባኝም?"
........... 🤔🤔🤔 ..............
ምርጦቼ :- ነጻ የ ፎሬክስ ትሬዲንግ ስልጠና ከፈለጋችሁ👇👇👇 ሊንኩን ንኩትና (Join) ተቀላቀሉን ቴሌግራም ላይ
https://t.me/free_ace_trades/123
https://t.me/free_ace_trades/123
እና ደግሞ መፖሰት እንዳላቆ 🤗 ይችን " 👍" ነገር ወዬ በሉኝ ምርጦቼ 😉
" ዝም ብላችሁ ለይኩኝ ነው ምላችሁ "
ፔጁንም ፎሎ እና ላይክ አድርጉት 🙏
#ሼር #ኢትዮጵያ
አይቆጥርባችሁም ፔጁን ፎሎ ላይክ አድርጉት🙏