28/11/2025
የአለምን ቀልብ የገዛች፣ አለምን ለማስተናገድ የተዘጋጀች ዘመናዊቷ ከተማ
ይህች ከተማ በፈጠራና በእድገት እየተገነባች የዘመናዊነት ድንቅ ጥበብን እየተላበሰች ትገኛለች፤ ከሩቅ የምታብረቀርቅ፣ የአለምን ቀልብ በግርማ ሞገስ የገዛች የአፍሪካ አውራ ከተማ! እጅግ አስደናቂ የሆኑ ሰማይ ጠቀስ ፎቆችና በኪነ ህንጻ የላቀ ጥበብ የተሰሩ መዋቅሮቿ የሰው ልጅን የፈጠራ አቅም የሚያንፀባርቁ ሆነው እየታዩባት ነው። ከተማዋ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከባህል፣ ከቅርስና ከተፈጥሮ ገፅታ ጋር አዋህዳ፣ ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምርጥ የአኗኗር ልምድን እያመጣች ነው።
በእያንዳንዱ አቅጣጫ የብዝሃነት ውበት የሚንጸባረቅባት፣ አለምን በአንድ ቦታ ሰብስባ በደማቅ ፈገግታ ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ያለች፣ ለነገው ዘመን የተዘጋጀች የብልጽግናና የዘመናዊነት ማዕከል ነች። ይህች ከተማ ከከተማነት በላይ ሆና፣ ለዓለም አቀፍ ትብብርና የጋራ ዕድገት ህያው መድረክ እየሆነች ነው።