Abiy Demilew አብይ ደምለው

Abiy Demilew አብይ ደምለው Media & Communications, Journalist, Cultural Activist

_____________   _____________                🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹የ1970ዎቹ አጋማሽ ከፈነጠቃቸው የዘመናዊ ሙዚቃችን ክዋክብት መሃል በትንፋ...
17/11/2024

_____________ _____________

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የ1970ዎቹ አጋማሽ ከፈነጠቃቸው የዘመናዊ ሙዚቃችን ክዋክብት መሃል በትንፋሽ መሳሪያዎች ዘርፍ (Brass Section) በተለይም #በአልቶና #ቴነር ሳክስፎን አጨዋወቱ የራሱን አይተኬ አሻራ ያስቀመጠና ከ60ዎቹ ወርቃማው ትውልድ በኋላ የተከሰተ ተወርዋሪ ኮከብ ነው ።

በርካታ የሙዚቃ ክዋክብትን ለዘመናዊ ሙዚቃችን ያበረከተው ኪነት ቡድን ውስጥ የበቀለው የሙዚቃ ህይወቱ #ከዳዲሞስ ባንድ እስከ #አሞራውና ብሎም ድረስ አጓጉዞታል።

#በዳዲሞስ ባንድ ውስጥ የተጫወታቸው ስራዎቹ ህያውነት እንደተጠበቀ ቢሆንም፤ በተለይ ግን ከተቀላቀለ በኋላ የሰራቸው ስራዎቹ የዘላለማዊ ስራዎች ክብርን አስገኝተውለታል።

በግሉና በጥምረት የሰራቸው አልበሞቹም በድንቅ በመሣሪያ የተቀነባበሩ ስራዎች (Instrumental) ዘርፍ በወርቃማ አልበምነት የተመዘገቡለት አሻራዎቹ ናቸው።

ለማንኛውም ይህንን የሙዚቃ ክስተት በሬድዮ ፕሮግራሜ #አፍሮቴይነር ላይ አቅርቤው ስለራሱና ጋር ስለሰራቸው ስራዎቹ በሰፊው አውግቶኛል። ከዚህ ረዥምና ውብ ቃለምልልስ ላይ ከነቅንብሩ የ 9 ደቂቃ ቅንጭብ እነሆ ጋበዝኳችሁ።

ክብር ዘመን-ተሻጋሪ ስራዎችን ላቆዩልን የመንፈስ ሀብቶቻችን ሁሉ ይሁንልኝ!

゚viral

_______   _______                                       🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹                                በክለሳ...
23/07/2024

_______ _______


🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በክለሳ የታተመ Revised Edition
ያልተሰማው የሀዋሳ ጉድ
******************

ክፍል ፪

"...በውስጣችን ከባድ አለመረጋጋት ተፈጠረ። 'ስራውን ምን እናድርገው?፣ ሰባብረን ሽንት ቤት እንክተተው? እንደዚያ ብናደርግ ደግሞ ታውታውሰዋለህ? እናስታውሰዋለን?' መባባል ጀምረን ነበር ይላል ።

ሀዋሳ ወደለየለት ስርዓት አልበኝነት እየተሸጋገረች ነው። ከባባድ የተኩስ ደምፆች እየተሰሙ ድንጋጤ እና ፍራቻው ተባብሷል። በተለይም በሃዋሳ የ ኬላ ላይ የተፈጠረው አባድ ተኩስ ሁሉንም አስደንግጧል።
********
አንድ በከባድ አጀብ ከአዲስ አበባ መስመር የሚመጣ 'ኮንቮይ' ደግሞ ከ የኬላ ዘቦች (ዋርዲያዎች) ጋር "አልፋለሁ..አታልፍም" ውዝግብ እየፈጠረ ነው።

በተለይም ሶስተኛዋ መኪና ውስጥ የነበሩ ሶስት ከባባድ "ጉምቱዎች" ቆጣ ብለው ኬላ እንዲከፈትላቸው ይጠይቃሉ።

"...እኛ የቱንም ባለስልጣን እንዳናሳልፍ ታዘናል! መመሪያ ደግሞ መመሪያ ነው!" ይላሉ የኬላ ዘቦች።

"አዛዥህን አገናኘኝ!" አሉ ከሶስቱ አንደኛው ጄነራል መኮንን በቁጣ። መልሱ አሁንም በድጋሚ "አትወጡም!" ይሆንና ውዝግቡ ይጦዛል።

እዚህች መኪና ውስጥ ሁለት የጄኔራል መኮንን ማዕረግ የለበሱ "ትልልቅ" ሰዎች ሲኖሩ፤ ሌላኛው ደግሞ ሰቪል የለበሱ 'ቁልፍ' የወቅቱ ባለስልጣን ናቸው።

አሁንም ጄነራሉ "ክፈት ብዬሃለሁ ክፈት!" ብለው በቁጣ አዘዙና ወደ መኪናቸው ገብተው መንቀሳቀስ ጀመሩ። ማማው ላይ ያሉ የኬላ ዘቦች ጭምር መሳሪያ አቀባብለው "ቁም!" ቢሉም መኪናዋ በፍጥነት ጉዞዋን ወደ ኬላው ትቀጥላለች።

በዚህ ጊዜ ከማማው ዋርዲያዎች የጥይት እሩምታ ይዘንብባት ጀመረ። በተጨማሪም ከዘቦቹ የተተኮሰ RPG የላውንቸር አረር እየተምዘገዘገ ደርሶ መኪናዋን አበራይቶ ያጎንና ሰማይ አድርሶ ይጥላታል።

አራት እግሯ ወደላይ ተገልብጦ መኪናዋ በእሳት ስትለበለብ ውስጧ የነበሩት ሶስት ሰዎች በቅፅበት ተሰውተዋል።

ከእሩምታ ተኩሱና ከላውንቸሩ ፍንዳታ በተጨማሪ መኪናዋ ውስጥ ተጭነው የነበሩ በርካታ ተቀጣጣይ መሳሪያዎች እየፈነዳዱ መኪናዋን እንዲሁም ውስጧ የነበሩ ተሳፋሪዎቿን በጠራራ ፀሃይ እንደ ጧፍ አቀለጧቸው።

ከሁሉ አስገራሚ የነበረው ግን እንደጧፍ እየተንቀለቀለ ይነድ የነበረው ብርና ዶላር ጉዳይ ነበር።

እዚህች መኪና ውስጥ ጋይተው የሞቱትን የሚሊተሪ አዛዦች ስም ለጊዜው እናቆየውና ሶስቱ የሙዚቃ ክዋክብት ባሉበት ሸበሌ ሆቴል መጥተው ጥግ ላይ አልጋ የያዙ ከባድ ባለስልጣን የነ አቤን ትኩረት ስበዋል። ሰውየው በጥንቃቄ ይወጣሉ፣ በጥንቃቄ ይገባሉ። ለወቅቱ ዘመናዊ የምትባል ላንድክሩዘር መኪና ግቢ ውስጥ አቁመዋል። በፍጥነት እየተቀያየሩ ባለው የሃዋሳ ሁኔታ እርሳቸውም የተጨነቁ ይመስላል።

እኚህ ሲቪልና የወቅቱ "ቁልፍ" ባለስልጣን የቤተመንግስቱ የገንዘብ ሃላፊው ጓድ ነበሩ። (በጓድ ዙርያ በሌላ ርዕስ በሰፊው የማወራችሁ ይኖራል)

ፕሬዝዳንት #መንግስቱ ከናይሮቢም ሆነ ዚምባቡዌ እንደገቡ ስልክ ደውለው ከባድ አደራ የሰጧቸው ልዩ ሸሪካቸው ጓድ አሳዛኝ አሟሟት ከጠቢባኑ ትውስታ ጋር በቀጣይ ክፍሎች እንመለስበታለን።
*************
የኬላው ላይ ተኩስና የጄኔራሎቹን ግድያ ትዕዛዝ በሬድዮ አዲስ አበባ ቢሯቸው ውስጥ ቁጭ ብለው ያስፈፀሙትም የደህንነት ሚኒስትሩ ኮሎኔል መሆናቸውን ዘግይተን አውቀነዋል።

********
ግንቦት 20 አዲስ አበባን የኢህአዴግ ሰራዊት ተቆጣጥሮም እንኳን በሀዋሳ የነበረው ሁኔታ አስፈሪ ስለነበር አረጌ ( )፣ ይልምሽ ( ) እና አቤ ( ) እርስ በርስ እየተጠባበቁ ሆቴል ውስጥ ናቸው።

በተለይም የጄኔራሎቹን የበቀደም'ለት ግድያ ከሰሙ በኋላ ደንግጠው መጪውን በዝምታ ለመጠባበቅ ተገደዋል።

#ከአቤና #ይልምሽ ይልቅ የተሻለ የመውጫ መንገድ እያፈላለገ የነበረው አረጋኸኝ ወራሽ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ #አረጌ በሙዚቀኝነት የወጣበት እናት ክፍሉ ነበርና ነው። በተጨማሪም ከተማው ውስጥም የሚያውቃቸው ትልልቅ ሰዎች ነበሩ።

"...ኢህአዴግ አገሪቱን መቆጣጠሩን፤ የበቅሎ ቤቱ ፍንዳታ የሚባለውን ሁሉ የምንሰማው በሬድዮ ብቻ ነበር" ይላል አረጌ ( ) ሲያጫውተኝ።

ሀዋሳ ላይ ከግንቦት 20 ጀምሮ ሰራዊቱ ተበትኖ ከተማውን የሚያስተዳድረው ማን እንደሆነም አይታወቅም ነበር። ሰባት ቀን ሙሉ ደርግም የለ-ኢህአዴግም አልገባ።
**********

ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ የለቀቅነው ይህ አስገራሚ ታሪክ በተጨማሪ ክፍሎች ሀዋሳ ላይ ባልተሰሙ ታሪካዊ ክስተቶች የሶስቱ ጓደኛሞች ታሪክ ይመለሳል።
*********
ይቀጥላል

,
,








10/07/2024

__________ __________
መከራን የተለማመደ ሀገር
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በእጅጉ የማከብራቸው በውስጡ መስመር ከባድ ጥያቄና ለሁላችንም የሚሆን ተግሳፅ የያዘ መልዕክት ቢሰጡኝ ራሴን፣ ሀገሬንና ሚዲያዎቻችንን ታዘብኩና ይህቺን ማለት ፈለኩ።

የጋዜጠኛ ፅሁፍ አጣቅሰው በእጅጉ የተገረሙበትንና ያዘኑበትን ነጥብ አስቀምጠዋል።

የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን አገባደው ወደቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ የነበሩ
ከ100 በላይ ተማሪዎች መታገታቸውን የሰማነው ባለፈው ሳምንት ቢሆንም የየትኛውንም ሚዲያ ትኩረት አግኝተው ዜናው ሊዘገብ አለመቻሉን አንስተዋል።

"የምርም መከራን ተለማምደነው? ለሰው ልጅ ህይወት በዚህ መጠን መጨነቅ አቁመናል ወይ?" ይሉና ይሄ አይነት ክፉ ልምምድ የአንድ ማህበረሰብን የሞራል ዝቅታን እንደሚያመለክት ተናግረዋል። "በተቃራኒውም ለቀጣይ ክፉ ተግባራት የይለፍ ፈቃድ እንደመስጠት ይቆጠራል" ይላሉ።
***********
እውነትም ምን ሆነናል? ነው ወይንስ መንጌ እንዳሉት ነገሩ መርዝም ሲቆይ ይለመዳል ሆኖብናል?

የ100 ወጣት ተማሪዎች መታገት ለሃገራችን ሚዲያ ርዕሰ ዜና መሆን የማይችልበት ምክንያት ምን ይሆን?

ከጥቂት አመታት በፊት የናይጄሪያው ቦኮሐራም 200 (ተማሪ) ልጃገረዶችን ባገተበት ወቅት የኛዎቹን ጨምሮ የአለም ሚዲያ ሁሉ ትኩረት ሆነው አልነበረምን? ታዲያ የኛ ተማሪዎች ከናይጄሪያውያን የሚያንሱ ሠዎች ናቸውን?

እንደ ሚዲያ ለህዝባችን መጮህ የምንጀምረው መቼ ይሆን? ወይንስ ባረበብን የፍራቻ ቆፈን ተጠፍንገን ሁላችንም እንደ ህዝብ ተያይዘን ወደ ቁልቁለት እየነጎድን ይሆን?

በመሰረቱ (በግሌ) የሃገራችን የሚዲያ ስሪቱ በራሱ ከስረመሰረቱ መፈተሽ ያለበት ይመስለኛል።

አሁንም ግን ምን አይነት ድንዛዜ ውስጥ ነው የወደቅነው የሚለውን መወያየት የሚያስፈልገን ይመስለኛል።

የተከበሩ ከልብ አመሰግናለሁ።


*****************
ባለፈው ሳምንት የታገቱት ከ100 በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አሁንም አልተለቀቁም። ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ በቃላት ሊነገር የማይችል ጭንቅ እና ስቃይ ውስጥ ይገኛል፣ እኛ ግን የስቃይ ጥግን ተለማመድነው መሰል ዝም፣ ጭጭ ተብሏል። የመንግስት ሚድያው ጭራሽ መዘገብ አልቻለም፣ ትንሽ የሚፅፉት የግል እና የውጭ ሚድያዎች ናቸው።

ህዳር 2012 ታግተው ደብዛቸው የጠፋው የደምቢ ዶሎ ሴት ተማሪዎች እንኳን በወቅቱ በመንግስት ሚድያዎች ጭምር መነጋገርያ ነበሩ።

የዛሬ ስምንት አመት ደግሞ የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ታጣቂዎች ወደ ጋምቤላ ክልል በመግባት በርካታ ህፃናትን አግተው ከወሰዱ በኋላ በምድር እና በአየር አሰሳ እና ኦፐሬሽን ተደርጎ ህፃናቱ እንደተመለሱ እናስታውሳለን።

አሁን የታገቱት ተማሪዎች ከ500 ሺህ ብር እስከ 1 ሚልዮን ብር በስልክ እየተደወለ ማስለቀቂያ ክፈሉ እየተባለ ነው።

ብዙዎች አሁን እየጠየቁ ያሉት ይህን ተከታትሎ መፍትሄ የሚሰጥ የደህንነት እና የፀጥታው አካል ምን እየሰራ ነው የሚለውን ነው። ከመቶ በላይ ሰው ከሳምንት በላይ የታገተበት ቦታ አይታወቅም?

ህዝብ መልስ ይጠብቃል።

_________   _________                                              ታሪካዊ ቪዲዮ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇨🇺🇨🇺🇨🇺🇨🇺🇨🇺🇨🇺🇨🇺🇨🇺በደም ግንኙነት የተጣመረው...
25/06/2024

_________ _________

ታሪካዊ ቪዲዮ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇨🇺🇨🇺🇨🇺🇨🇺🇨🇺🇨🇺🇨🇺🇨🇺

በደም ግንኙነት የተጣመረው የኢትዮጵያና ኩባ ወዳጅነት ወደ ሃምሳኛ አመቱ እየተንደረደረ ይገኛል።

አስተዳደር ለዘመናት የቆየውን ታሪካዊ ግንኙነት ወደጎን በማድረግ በሌለ አቅማችን ለጦር መሳሪያ ግዢ የከፈልነውን ገንዘብና መሳሪያ በመከልከሉ ኢትዮጵያ ያለ ወዳጅና ያለ ረዳት ሀገር ለብቻዋ የቆመችበት ሁኔታ ተፈጠረ።

#ከዚያድባሬ ጎን በመቆም የሶማሊያ መንግስት ኦጋዴንን ለመውረር ሲንደረደር መሳሪያ ጭምር እየሰጠች ትደግፍ ነበር።

እዚህ ጋር ታድያ #የዚያድባሬ መንግስት በድንገት የሶቪየት ዲፕሎማቶችንና ዜጎችን ሀገሩን ለቀው እንዲወጡ የወሰነው ውሳኔ የጨዋታውን አካሄድ ሊቀይር ቻለ።

በሌላ በኩል ደግሞ አፍሪቃን ከቅኝ ግዛትና የኢምፔሪያሊዝም ወረራ ለመታደግ የተመራው አብዮት አይኑን ወደ ኢትዮጵያ ማማተር የጀመረበት ወቅት ነበር።

አልጀርስ ላይ በተደረገው የ ገለልተኛ ሀገራት ጉባኤ ላይ ያደረገው ታሪካዊ ንግግር ኢትዮጵያን ጨምሮ በቅኝግዛት ቀንበር ስር ለነበሩ የአፍሪቃ ሀገራት ተስፋን ፈነጠቀ።

#ፊደል ፈጣን ውሳኔ በመወሰን በወቅቱ አልጄሪያ ላይ ሰፍሮ የነበረውን ጦራቸውን ወደ ኢትዮጵያ በፍጥነት እንዲንቀሳቀስ ትዕዛዝ በመስጠት፤ የወቅቱ የኩባ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የካስትሮ ታናሽ ወንድም ወደ መንጌ በረው በመምጣት ዜናውን እንዲያበስሩ ተደረገ።

እስከ አፍንጫው የታጠቀ ሠራዊት እና የሶቪዬት ጦር መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ መትመም ሲጀምሩ ሁሉም ግጥምጥም አለ። በዚህ ጊዜ #መንጌ ክተት አውጀው 300ሺህ የሚሆን የሚኒሻ ሠራዊት #በታጠቅ ሠፍሮ ሌት ተቀን እየሰለጠነ ነበር።

ይህንን የተመለከተው #የየመን ሶሻሊስት ሪፐብሊክ መንግስት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ወታደሮችና መሳሪያ ይዞ ከተፍ አለ። ደግሞ ታጠቅ የገባውን 300ሺህ ጦር የሚሊተሪ ልብሱን አለበሰች።

ይሄ ሁሉ የመጣው #ኩባ፣ ፊደል ካስትሮና ቼ ጊቫራ በወሰኑት ድንቅ ውሳኔ ነበርና እውቅና ዝነኛ የሆኑትን የኩባ የጦር አበጋዝ በመላክ ጦሩ በቀጥታ የውጊያ ቀጣና ውስጥ በመግባት ወረራውን እንዲቀለበስ ትዕዛዝ ተሰጠ።
**************
ለማንኛውም በዚያ ሁኔታ የጀመረው የኢትዮጵያና ኩባ ወዳጅነት ዛሬም ድረስ በከፍተኛ ጥብቀት የቀጠለ ሊሆን ችሏል።

ከታች ባዘጋጀሁላችሁ ቪዲዮ ላይ ፊደል ካስትሮ 1972ላይ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የነበረውን አቀባበል እንዲሁም መንጌ ኩባ በሄዱበት ወቅት የነበረውን ታሪካዊ አቀባበል ታዩታላችሁ። በተለይም የመንጌን የሀቫና አቀባበል የኩባ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ከሶስት አመት በፊት የላከልኝ ነውና በደንብ ተመልከቱት።

ቪቫ ወዳጅነት!
ዘላለማዊ ክብር !

Try the free video editor CapCut to create videos! https://www.capcut.com/t/Zs8rYUVKL/

_____  ? _____                      ባለቤት አልባ ሐገር🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ወዳጄ ዙቤይዳ አወል Zubeyda Awel ሰሞኑን ሲያሳስበኝ የከረመውን...
03/06/2024

_____ ? _____
ባለቤት አልባ ሐገር
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ወዳጄ ዙቤይዳ አወል Zubeyda Awel
ሰሞኑን ሲያሳስበኝ የከረመውን ይህንን ጉዳይ አነሳችውና እኔንም ቆሰቆሰችኝ።

እናም ለመሆኑ ባሁኑ ጊዜ ከልጆቻችን ጋር ተቀምጠን ያለመሳቀቅ የምንመለከታቸው የቴሌቪዥን መዝናኛ ፕሮግራሞች ይኖሩን ይሆን? በተለይ የሳምንት መጨረሻ (Weekend) የሚተላለፉቱ ብዬ ለመጠየቅ ተገደድኩ።

አንድ ሚዲያ በሚሰራቸው የፕሮግራም ይዘቶችና አቀራረቦች ሲሆን ሲሆን እንደ ጣቢያ የራሱ ስፔሻላይዜሽን ፈጥሮና Target Audienceሱን ወስኖ ይነሳል። ለዚያም ነው የዜና ቻናል፣ የመዝናኛ ቻናል፣ የሙዚቃ ቻናል፣ የስፖርት ስቴሽን ወዘተ የሚል ዘርፍ የሚወጣላቸው።

ለዚህም የተመልካቾቻቸውን የእድሜና የአስተሳሰብ ደረጃ በማጥናት በሚሰሩ ፕሮግራሞች ላይ በተለየ መልኩ የሚጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳይኖሩ እና በተለይም የህፃናትን አለም ከብክለት ለመጠበቅ ሀላፊነት የሚሰማቸው በእድሜ የበሰሉና ማህበራዊ ስነልቦና Social psychology ጨምረው ያጠኑ ሰዎች የሚቀጥሩት።

እናም ኤዲተሮች፣ ፕሮግራም መሪዎች፣ የቀጥታ ስርጭት ተከታታዮች፣ የቋንቋና ስነልቦና ባለሙያዎችን ሰብስበው ያሰራሉ።

ፕሮግራሞች በቋንቋው፣ በታሪኩ ወይም በአቀራረቡ ላይ ለህፃናትና ለታዳጊዎች የማይመጥን ይዘት ሲኖራቸው በቤተሰብ እገዛ የሚታይ (Parential Guide /PG) የሚል ስታንደርድ ከማስቀመጥ ጀምሮ "የሚቀጥለው ፕሮግራም ለነፍሰጡሮች፣ ለህፃናትና የልብ ችግር ላለባቸው አይመከርም" ብለው ስታንደርድ እስከማስቀመጥ ይደርሳሉ። ስለዚህም ሰው መርጦ ይመለከታቸዋል።

የማህበረሰብን መንፈሳዊና ባህላዊ እሴት የሚጥስ የቋንቋ ይዘት የተካተተበት ፕሮግራም ሲኖርም ቀድሞ ከማሳሰብ ጀምሮ ያልተገቡ ጨዋነት የጎደላቸውና ወሲባዊ የሆኑ ቃላትን በቴክኖሎጂው አንዲታፈን ያደርጋሉ።

እኛ ሀገር ደግሞ የምታውቁት ነው። ልጆቻችን ጋር ሆነን መመልከት የምንችለው የቴሌቪዥን ቻናልና መዝናኛ ፕሮግራም ካጣን ቆይተናል።

ኢትዮጵያዊ ሞራሊቲና የልጆቻችን የመንፈስ ነፃነት ላይ ዘመቻ የተከፈተ በሚመስል መልኩ ባልበሰሉ ፕሮግራም አቅራቢዎች ሲዘመትብን ይውላል።

በሳምንቱ መጨረሻ በሰራው ፕሮግራም ላይ "ባለቤቴን አስፈቅጄ ሴተኛአዳሪነት እሰራ ነበር" የተሰኘ ርዕሰ የተሰጠውን ፕሮግራም እነሆ ሲያስተላልፍ ለማየት በቃን። ያስደነግጣል። የምር ያስደነግጣል!

ስለዚህም ሌላ ምንም ዝብዝባ ሳላበዛ የተወሰኑ ጥያቄዎችን ላንሳና የራሳችሁን ፍርድ ስጡ።

*** የተፈለገው የማህበረሰብ ዋናው መሰረት የሆነውን የቤሰብና የትዳርን ተቋምነት ለማስረፅ ነውን?
*** በትዳር ውስጥ ፍቅር፣ እምነትና መተማመንን ለመገንባት ነውን?
*** በትዳር ውስጥ ለሚገጥም ፈተና ሁሉ ሴተኛአዳሪነትን የችግር መወጫ አቋራጭ መንገድ አደርገን እያቀረብን ነውን?
*** ለልጆቻችን ሴተኛአዳሪነት ነውር የሌለው ስራ አደርገን እያስተዋወቅንና ሀሳቡን እያለማመድን ነውን?
*** እንደዚያ ከሆነ ሴቶች ልጆቻችንን ደክመን ለምን እናስተምራለን? ከአእምሮ፣ ከእውቀትና ከጉልበታቸው በላይ ፆታቸው የተሻለ አቋራጭ ፀጋ እንደሚያመጣ እየመከርናቸው ነውን?
**************

ያገባናል የምንል ከሆነ እስቲ እነዚህን ጥያቄዎች እንወያይባቸው። ሴት ልጆቻችን ይህንን ፕሮግራም አይተው ለሚያነሱልኝ ጥያቄዎች ምን መልስ እንስጣቸው? ሴተኛ አዳሪነትን በኦፊሴል ይፋዊ እውቅና እየሰጠነው ነውን?

ሀገሩና ማህበረሰቡ በሁሉም ዘርፎች በመፈራረስ አደጋ ላይ እንዳለ የሚታየኝ ለኔ ብቻ ነው ወይስ ለናንተም? እንወያይበት። በተለይ ሚዲያው በእውቀትም ይሁን ባላዋቂነት ይህንን ዘመቻ እየመራ አይደለምን? ልጆቻችንንሰ ከስንቱ ማዕበል ጠብቀን እንችላለን?

በግሌ ሀላፊነት የሚሰማቸውና አስተዋይ የሆኑ ኤዲተሮች እና ፕሮግራም ዳይሬክተሮች የሌሉትና የተመልካቹን ዳይቨርስ ማንነት የማያገናዘቡ እንዲህ አይነት ፕሮግራሞች የሚቀርቡበት አሳዛኝ ቻናል ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

___________   ___________          IN SEARCH OF THE LEGEND🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ሠውየው  -   የወጣት ኢትዮጵያዊያንን ደም እንደ ...
14/02/2024

___________ ___________
IN SEARCH OF THE LEGEND
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ሠውየው - የወጣት ኢትዮጵያዊያንን ደም እንደ ዥረት ሲያፈስ ይመለከታል። በሀዘን ልቡ ይቆስላል። ግን ደግሞ ያንን ለማስቆም የሚያስችል ቅንጣት አቅም አልነበረውም። የበለጠ ሀዘን። አቅም አልባነት!

በሚወርድባት ሀገሩ ላይ ሆኖ የሙዚቃ ስራውን ለመቀጠል ከባድ የመንፈስና የሞራል ጥያቄ ቢፈታተነውና ፍፁም ሠላም ቢነሳው፤ አንዱ ቀን ላይ እንደ አይኑ ብሌን የሚወዳትን ሀገሩን ጥሎ ለመሸሽ ጓዙን ጠቀለለ። እናም በድንገት ከከተማው #ተሰወረ።

" #ምኒልክን ያያችሁ?!" ቢባልም "አየሁ" የሚል ጠፋ።
-----------------------
ከጥቂት አመታት በኋላ በአንድ ወዳጁ ምክንያት "ሡዳን ውስጥ ታይቷል" ከሚል ቁንፅል መረጃ ውጪ ሰውየው የት እንደገባ ሊታወቅ አልቻለም።
------------------------
1982 ክረምት ደግሞ አንድ የአለማችን ግዙፍ ቢሊየነር ቢሮ ማንኳኳት ጀምሯል።

"ሀገሬ ላይ መጥቼ ኢንቨስት ማድረግ እፈልጋለሁኝ ፈቃድ ይሰጠኝ" ብሎ #ከለንደን እና #ኒውዮርክ ጉዳዩን በቅርበት ይከታተላል።

ይሁንና የሠሜኑ ጦርነት እየገፋ መምጣት ሀገሪቱንና ፕሬዚዳንቱን ወጥረው ይዘዋቸው ኖሮ ለቀረበላቸው አጓጊ የኢንቨስትመንት ጥያቄ መልስ ሳይሰጡ 1983 አጋማሽ ይደርሳል።

ታድያ አንዱ ቀን ላይ ለወራት #በፕሬዝዳንቱ ጠረጴዛ ላይ ከላይ ተቀምጦ ውሳኔ ሲጠባበቅ የነበረው አዲስአበባ ላይ የመገንባት #በመንጌ ተፈርሞ ቀና መልስ በማግኘቱ ባለሀብቱ ወደ #ኢትዮጵያ ሊመጡ ሆነ።

ሰውየው ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ #አላሙዲን ነበሩ።

ታሪኩ እንግዲህ የሚጀምረው እዚህ ጋር ነው።
#ምኒልክን ፍለጋችን ይቀጥላል!
ይሁንና አንተ የትውልድ ትንግርት የሆንከው ደማቁ ኮከብ ሆይ....

ፈጣሪ ነፍስህን ጠብቆ በክብር በአፀደ ገነት ያኑርልን እልሃለሁ።

__________   __________                     🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ከብልፅግናው ጥቂት ተወዳጅ እንስት ባለስልጣናት መካከል ዶክተር   ወይንም የ...
09/02/2024

__________ __________

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ከብልፅግናው ጥቂት ተወዳጅ እንስት ባለስልጣናት መካከል ዶክተር ወይንም የሀገራችን ከስልጣን መነሳታቸውን ስሰማ አዘንኩ!

ለህዝብ ቅርብ በሆነ አንደበትና አቀራረብ ስለ በየምሽቱ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ እያሉ የየእለቱን የተጎጂዎቹ ቁጥር እየነገሩ፣ እየመከሩና እያስተማሩን ያንን ክፉ ዘመን ያሻገሩን ፈርጥ ናቸው።

#ሊያ ኮቪድን ለሚያክል እንደ ሠደድ እሳት ለሚንቀለቀል ወረርሽኝ ፍፁም የተደራጀ አቅምና ዝግጅት ያልነበረውን የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት በቆራጥነት መርተዋል።

እድሜያቸው ለዚህን ያህል አንቱታ ባያበቃቸውም፤ በስራቸው ግን በክብር "አንቱ" ልንላቸው እንገደዳለን።

ወጣት፣ ትሁት፣ ቆንጆ፣ ባለእውቀትና የኢትዮጵያን ያህል ግዙፍና የተወሳሰበ ሴክተር እስካሁን የመሩ የተሰጡ፣ የተቀቡና የተወደዱ መሪ ነበሩ።

ከብልፅግናው ቀላድ ከተመካንባቸው ተወዳጅ እንስት ሹመኞች መሃከል ወይዘሪት ዶክተር መንበር ለቀዋል። በግሌ ከምወዳቸው "የመጨረሻዎቹ" መሃል ወይዘሮ ብቻ ቀርተዋል።

ውድ ዶክተር

በዚያ የአለማችን የጭንቅ ሰዓት ሀላፊነት ወስደው ለመሩት፣ ላደራጁትና ላዘመኑት የጤና ጥበቃ አሰራር ብዙዎች ቢያመሰግኖትም፤ ከፊት ለፊት ወጥተው ህዝብን ለማዳን በወሰዱት ቆራጥና አይተኬ አመራር ደግሞ እኛ እንደ ህዝብ እናመሰግኖታለን!!!

ሌላው ሁሉ ቢቀር #ኮቪድ በተነሳ ቁጥር በተከታታይ ትውልዶች ዘንድ በክብር ስምዎ መጠራቱና መመስገኖ አይቀርምና ክብር ለርስዎ ይሁን።

____________   ____________                   🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ወደ ምርጫው ሲመጡ አሳት የበላ ትንታጉ፣ ምድር አንቀጥቅጡ፣ በግርማቸው፣ ...
05/02/2024

____________ ____________

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ወደ ምርጫው ሲመጡ አሳት የበላ ትንታጉ፣ ምድር አንቀጥቅጡ፣ በግርማቸው፣ በድምፃቸው ሞገስና በሚናገሯቸው ንግግሮች ከአሜሪካ ሴናተርነት አልፈው የመላው አለምን ቀልብ ያራዱት የመጀመሪያው ጥቁሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት #ኦባማ...

◈ሸበላው፣ መልከመልካሙ፣ ትሁቱና ዘናጩ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት....

◈በጥቁር ፀጉር ስልጣን ላይ ወጥተው በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው ላይ ባለ ነጭ ፀጉር ሆነው የታዩት #ኦባማ....

◈በእርሳቸው ዘመን ብዙ ስኬቶች የተመዘገቡላቸው ቢሆንም ነገርግን የአሜሪካ የክፍለዘመናት ችግሮች ተጠራርተው በትክሻቸው ላይ ወድቀው መከራ ያበዙባቸው መከረኛ ፕሬዚዳንት....

◈በእነዚያ ፈተናዎች መሃል ሆነውም ቢሆን ቀብር ላይ የወቅቱን የኩባውን ፕሬዚዳንት እጅ ስበው ጨብጠው ከ60 አመታት በላይ የተጠረነፈውን ጠላትነት የሰበሩት #ኦባማ.....

◈ #የፍልስጤምን የነፃነት ጥያቄ በማራመድ ብዙ መከራ የደረሰባቸው ምስኪኑ #ኦባማ...

◈ #ኢትዮጵያ ድረስ መጥተው ከጠሚ #ሀይለማርያም ጎን ቆመውና #ሀይለማርያምን #ጉራጊኛ አስጨፍረው፤ "ሀገራችሁ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነፃነት ምኩራብ እና ቀንዲል ስለሆነች እንደ አይናችሁ ብሌን ጠብቃችሁ ያዟት!" ያሉን ኦባማ....

◈ኢትዮጵያዊ ቦይፍሬንድ ይዛ የሚዲያ አይኖች ሁሉ ከላይዋ ላይ አልነቀል ያሏት የውብ ልጃቸው አንድ ዝግጅት ላይ ዛሬ ሲገኙ እንዲህ ሸብተው ታይተዋል።

የእውነት ዛሬ የጊዜን ተዓምር የመሰከርኩበት ቀን ነው መሰለኝ!

#ኦባማዬ ሸብተህም ቢሆን ገና ነህና በክብር ኑርልን ልለው ወደድኩ!!!

Long Live Obama❤







Abiy Demilew

____________   ___________         አስገራሚ የህይወት ግጥምጥሞሽ                 #የቦሌ ልጆችና  #አልቃይዳ          ገዳይ ስኳድ ጋር ተገናኘን! 🇪🇹🇪🇹🇪...
03/02/2024

____________ ___________
አስገራሚ የህይወት ግጥምጥሞሽ
#የቦሌ ልጆችና #አልቃይዳ
ገዳይ ስኳድ ጋር ተገናኘን!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ለመጀመሪያ ጊዜ የምትሰሙት #የቦሌ ሻላ ሠፈር የ18 ቀበሌ #አፓርታማ ሠፈር ልጆች ሳናውቅ የገባንበት እጅግ አደገኛ ወጥመድ።

በ #በአልቃይዳው ሼክ በቀጥታ ከሚታዘዘው እጅግ አደገኛ ገዳይ ስኳድ ጋር የ6ወር ጎደኝነት።

እውነተኛ ታሪክ!

ትንፋሽ የሚነጥቅ አስገራሚ ታሪክ በቅርብ ቀን!
Dawit Ambaw ተዘጋጅ

_____________   _____________                      ⭐UPADATE⭐                             🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹የታላ...
02/02/2024

_____________ _____________
⭐UPADATE⭐

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የታላቁና ተወዳጁ ድምፃዊው ባለቤት ወይዘሮ አስክሬን ነገ ጠዋት 1:00 ሰዓት ላይ አዲስአበባ እንደሚገባ ቤተሰቦቹ አስታውቀውኛል።

ጉሮሮዋ ላይ በገጠማት ከባድ ህመም ከፍተኛ የስቃይ ጊዜና ህክምና ላይ ያሳለፈችው የሚቻለው ርብርብ ሁሉ ሲደረግላት ቢቆይም ባለፈው ሳምንት ከዚህ አለም ድካምና ስቃይ ተገላግላለች።

ባለቤቷን ጨምሮ መላው ቤተሰቡ በከባድ ሐዘንና ህመም ውስጥ ቢሆኑም፤ ፈጣሪ ለሁሉም ፅናትና ብርታቱን እንዲሰጥና የባለቤቱንም ነፍስ በክብር እንዲቀበልልን እንፀልያለን።

የቀብሩ ሰዓት እንደታወቀ የምንገልፅላችሁ ሲሆን ጋዜጠኞች፣ የሙያ አጋሮቹ፣ የኪነጥበቡ ሰዎች፣ የቴአትር ቤት ጓዶቹ፣ አድናቂዎቹና ሁላችንም የአርቲስቱን ባለቤት በስፍራው ተገኝተን በክብር እንድንሸኛት በአክብሮት እጠይቃለሁ።

Teshome Wolde
TG Mamo

______________   ______________                        እንኳን ደህና መጣሽ🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ፀሀይን የማስመለስ ጥያቄውና ሂደቱ...
01/02/2024

______________ ______________
እንኳን ደህና መጣሽ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

#ፀሀይን የማስመለስ ጥያቄውና ሂደቱ ገፍቶ የወጣው (እስከማውቀው ድረስ) በጠቅላይ ሚኒስትር #ሀይለማርያም ዘመን ነው።

እንደነዚህ አይነት ትልቅ የሃገርና የታሪክ ቅርሶችን ለማስመለስ ጊዜና ሂደት ይፈልጋል። ከአመታት በፊት ይህንኑ ጥያቄ #በሀይለማርያም የተጠየቁት የወቅቱ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር፤ "...የጣሊያን ፓርላማ ተወያይቶበት ከወሰነ እንጂ እኔ ማንዴቱ የለኝም። ይሁንና Lobby አደርጋለሁ!" ብለው እንደነበር በወቅቱ በአአ የጣሊያን ኤምባሲ ጋዜጠኞችን ጠርቶ ነግሮናል።

አሁን ያ ተሳክቶ #ፀሀይ ወደ እናት ሀገሯ መመለሷ አስደሳች ቢሆንም፤ የመንግስት ሚዲያውና የፓርቲው ሰዎች በብቸኝነት የጠቅላዩ የዲፕሎማሲ ትሩፋት አድርገው ሲያቀርቡት ስታይ ደስታህን ይነጥቁታል።

#ጣሊያን፣ #ፈረንሳይና #እንግሊዝና #ፖርቹጋል በቅኝ ግዛት ዘመን ላይ ከተለያዩ ሀገራት የዘረፏቸውን ቅርሶች ለባለቤት ሀገራት እንዲመልሱ፣ በነፃነት ትግሉ ወቅት ላደረሱት ሰብዓዊና ሞራላዊ ኪሳራ ካሣ እንዲከፍሉ በብዙ #የአፍሪቃና የአለም ሀገራት ተወጥረው ተይዘዋል።

በነዚያ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ሙዚየሞች፣ ጋለሪዎች፣ የቅርስ ተቋማትና አክራሪ (Nationalist) የፖለቲካ ክፍሎች ደግሞ በተቃራኒው ቅርሶች ተመልሰው ለሃገራቱ እንዳይሰጡ ከፍተኛ ግብግብና Lobby እንደሚያደርጉም ይታወቃል።

ምክንያቱ ደግሞ የቅርስ ዝርፊያ፣ ዝውውርና ሽያጭ ራሱን የቻለ የቢሊዮን ዶላር ኢንዱስትሪ ሆኖ ወጥቷልና ነው።

#ብሪታንያ #ለኬንያው የነፃነት እንቅስቃሴ አባላትና ቤተሰቦቻቸው ላይ በወቅቱ ለደረሰው የህይወትና የአካል መጉደል ካሣ በቅርቡ መክፈሏን እናስታውሳለን። #ለታንዛኒያም እንደዚሁ።
#ፈረንሣይም በተመሳሳይ ለአልጄሪያው የነፃነት ሀይሎች አባላትና ቤተሰቦቻቸው የሞራል ካሣ መክፈሏ ይታወቃል።

በዝርፊያ፣ በግዢ፣ በምርኮ፣ በጉልበትና በደላላ ወዘተ ተወስደው በመላው አውሮፓ ሙዚየሞች ተበትነው የሚገኙ የኢትዮጵያ ቅርሶች ህልቆ መሳፍርት የላቸውም።

ጠንካራ የሆነ ብሄራዊ ቡድን (Commission) ተቋቁሞና በየሃገራቱ የሚገኙ ቅርሶችን መዝግቦ ለማስመለስ የሚጥር ጠንካራ ተቋም በሌለበት ሁኔታ አንዷን ነጠላ ቅርስ እያስመለሱ የግለሰብ መሪ የዲፕሎማሲ የስኬት ሀድራ አድርጎ ማቅረብ በተከታታይ ትውልዶች የተደረጉ ጥረቶችና ድካሞች ላይ ውሃ መቸለስ ይመስለኛል።

ምክንያቱም ዘመን እንኳን ፕሮፌሰር ፕሮፌሰር ጨምሮ ብዙዎች ደክመውበታልና ነው። ከ"እኔ" በላይ "እኛ" የሚለው ይቅደም የምንለውም ለዚያ ነው።

ለማንኛውም #ፀሀይ እንኳን ወደ እናት ቤትሽ በክብር መጣሽ!!!

Address

Addis Ababa
AA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abiy Demilew አብይ ደምለው posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abiy Demilew አብይ ደምለው:

Share