30/10/2025
2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ብስክሌት ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን አገኘ።
10ኪሜ በሸፈነው በሴቶች የግል ክሮኖ ማውንቴን ውድድር ትግራይ የወርቅና የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ኦሮሚያ የብር ሜዳሊያ አስመዝግቧል።
25ኪሜ በሸፈነው በወንዶች የግል ክርኖ ኮርስ ኦሮሚያ የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም አዲስ አበባ የብርና የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።
15ኪሜ በሴቶች ቡድን ክሮኖ ማውንቴን ኦሮሚያ ትግራይና አዲስ አበባ የወርቅ፣ የብርና የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።
30ኪሜ በወንዶች የቡድን ክርኖ ኮርስ ትግራይ፣ ኦሮሚያና አዲስ አበባ ከ1-3 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
40ኪሜ በሴቶች የጎዳና ዙር ውድድር ማውንቴን ኦሮሚያ የወርቅና የነሀስ ሜዳሊያ ሲያሸንፍ ትግራይ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል
80ኪሜ በወንዶች የጎዳና ዙር ውድድር ማውንቴን ትግራይ የወርቅና የነሀስ ሜዳሊያ ሲያሸንፍ አዲስ አበባ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።
Ethio Cycling News