Prosperity ADDIS ብልፅግና አዲስ

Prosperity ADDIS ብልፅግና አዲስ UPRISING PEACE, DEMOCRACY ,UNITY & DEVELOPMENT

24/08/2025
24/08/2025

የአይበገሬነታችን ማሳያ፣ የሀገራችን ትንሳኤ ማብሰሪያ ግድብ!

ኢትዮጵያዊያን በጋራ ጉዳያቸው ላይ በህብር ደምቀው ከመሪዎቻቸው ጎን በመቆም የቁጭት ምንጭ ሆኖ በቆየው በዓባይ ወንዝ ላይ አኩሪ ታሪክ ፅፈዋል፡፡ በቅርቡ ለምርቃት የሚበቃው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የትብብራችን ውጤት ነው፡፡

ተጋርጠውበት የነበሩትን በርካታ ተግዳሮቶች እንዲሁም ጫናዎች በድል አድራጊነት በመሻገር ለፍፃሜ የበቃው ግድባችን አይበገሬነታችንን ለዓለም አሳይቷል፡፡

የሰንደቅ ዓላማችን ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴ ግድባችን የተለያዩ ሴራዎችን በመበጣጠስ፣ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ ጫናዎችን በመቋቋም በእልህ እና ወኔ በማለፍ ለፍሬ ያበቃነው አንደኛው የብሔራዊ ኩራታችን ምንጭ ነው፡፡

በአድዋ ጦርነት በወራሪዎች ላይ የተረባረበው የኢትዮጵያውያን ክንድ በዘመናችንም የጣና ሀይቅን ሁለት እጥፍ የሚያህል የውሀ መጠን የሚይዝ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ግዙፍ ግድብ ገንብቷል፡፡

የሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራ ያረፈበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በላብአችን የፃፍነው፣ በድካማችን ያሳካነው አኩሪ ታሪካችን ጭምር ነው።

በቅርቡ ሪቫን የምንቆርጥለት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን ትስስራችንን ይበልጥ በማጥበቅ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያበስራል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

Address

Addis Ababa

Telephone

+25111 667 3938

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity ADDIS ብልፅግና አዲስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Prosperity ADDIS ብልፅግና አዲስ:

Share