FAJR News Ethiopia

FAJR News Ethiopia Fajr News Ethiopia

የህወሓት አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የመከላከያ ሠራዊት  አስታወቀ !ሌተናል ጀነራል አስራት  ዴኔሮ ዛሬ  ረፋድ  እንደተናገሩት  የህወሓት አመራሮችን ...
18/12/2020

የህወሓት አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ !

ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ ዛሬ ረፋድ እንደተናገሩት የህወሓት አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

በዚህም የመከላከያ ሠራዊት የህወሓት አመራሮች ያሉበትን ቦታ ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ አመልክተዋል፡፡

FAJR News Ethiopiaበአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት በደረሱ የእሳት አደጋዎች ከ200 ሺህ ብር በላይ ንብረት መውደሙ ተገለጸ፡፡የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢት...
16/11/2020

FAJR News Ethiopia
በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት በደረሱ የእሳት አደጋዎች ከ200 ሺህ ብር በላይ ንብረት መውደሙ ተገለጸ፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቅው ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ አራት የእሳት አደጋዎች መከሰታቸውን አስታውቋል፡፡

የመጀመርያው የእሳት አደጋ የተከሰተው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ በአንድ መኖርያ ቤት ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡

በዚህ አደጋ 100 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት አደጋ የደረሰበት ሲሆን ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ ነው የተገለጸው፡፡

ሁለተኛ አደጋ የደረሰው ደግሞ በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት በመኖርያ ቤት የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡

በዚህኛውም አደጋ ምክንያት ከአምስት ሺህ ብር በላይ በሚሆን ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከሶስት ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ንብረት ደግሞ ማዳኑን ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

ሌላኛው የእሳት አደጋ የደረሰው በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት በአንድ መኖርያ ቤት ላይ የደረሰ አደጋ ነው፡፡

ከዚህኛው አደጋ ጋር በተያያዘም 50 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ከውድመት ማዳኑን ነው የገለጸው፡፡

አራተኛ አደጋ የደረሰው ደግሞ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት የኮንስትራክሽን እቃዎች በተከማቹበት መጋዘን ውስጥ የተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ነው፡፡

ከአደጋው 80 ሺህ ብር የሚሆን ንብረት የወደመ ሲሆን ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ ነው የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ የነገሩን፡፡

 የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከሕወሐት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ በተለያዩ የዜና አውታሮች የቀረበው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን  የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ግብረ ኃይል አስታ...
16/11/2020


የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከሕወሐት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ በተለያዩ የዜና አውታሮች የቀረበው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡
የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝም የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ግብረ ኃይል ገልጿል፡፡
የሚዲያ አካላት እንደ መሠረታዊ የጋዜጠኝነት አሠራር የኢትዮጵያን የሕግ የበላይነትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ሁልጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይል ፕሬስ ሴክሪታሪያት በኩል እንዲያረጋግጡም ጥሪ አቅርቧል፡፡

04/11/2020

Here are the facts...

  News Ethiopia
19/10/2020

News Ethiopia

13/10/2020
13/10/2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ወለድ አልባ ባንክ የስራ ፍቃድ ርክክብ በዘምዘም ባንክ እና ብሄራዊ ባንክ መካከል ተደረገ። ዘምዘም ባንክ ከ13 አመታት የ....

13/10/2020

The First Ethiopian Full Fledged Interest Free Bank

Address

Addis Ababa

Telephone

+251902448004

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FAJR News Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share