1 Birr

1 Birr ወቅቲዊ ጉዳይ የሚዳሰስበት ዐውድ

መንግስታችን ሀኪሞች እያደረጉ ያሉት ትግል ተጠልፏል አለ። ለሀገሩ ዜጎች የመብት ጥያቄ ከመቀበል ይልቅ የውጪ ዜጎችን በዶላር ለመክክፈል ማቀዱን የሸገር ሲቲ ብልጽግና ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃ...
11/05/2025

መንግስታችን ሀኪሞች እያደረጉ ያሉት ትግል ተጠልፏል አለ። ለሀገሩ ዜጎች የመብት ጥያቄ ከመቀበል ይልቅ የውጪ ዜጎችን በዶላር ለመክክፈል ማቀዱን የሸገር ሲቲ ብልጽግና ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀልቤሳ እንዲህ አስፍሯል።

የፎቶ ሱስ 😁
21/04/2025

የፎቶ ሱስ 😁

ባለፈው ዓመት ኤጲስ ቆጰሳት የተሾሙላቸው የወለጋ ዞኖች አህጉረ ስብከት በአንድ ሊቀ ጳጳስ እንዲመሩ ተወሰነ !ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ከቀ...
01/06/2024

ባለፈው ዓመት ኤጲስ ቆጰሳት የተሾሙላቸው የወለጋ ዞኖች አህጉረ ስብከት በአንድ ሊቀ ጳጳስ እንዲመሩ ተወሰነ !

ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ከቀትር በፊት ውሎው 7 አህጉረ ስብከት በአንድ ሊቀ ጳጳስ እንዲመሩ በማድረግ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ ውሳኔ ሰጥተዋል።

ባለፈው ዓመት ለኦሮሚያ አህጉረ ስብከት ከተሾሙ 9 ጳጳሳት መካከል 3ቱ ለወለጋ አህጉረ ስብከት የተሾሙ ቢሆንም ወደመንበረ ጵጵስናቸው ሄደው ማገልገል አለመቻላቸውን ገልጸው ዝውውር ጠይቀዋል።

በዛሬው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶስ በዚሁ ጥያቄ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በያዙት 3 አህጉረ ስብከት ላይ 4ቱን የወለጋ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሰሩ በመወሰን በታሪክ 7 አህጉረ ስብከትን በአንድ ጊዜ የመሩ ሊቀ ጳጳስ ሆነዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የአንዳንድ አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ጨምሮ የሌሎች አባቶችንም ዝውውር ያጸደቀ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ተሚማ

ቅዱስነታቸው የደቡብ አፍሪካ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ።******ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ...
22/05/2024

ቅዱስነታቸው የደቡብ አፍሪካ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ።
******

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ
ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዮንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣የደቡብ ኦሞና
አሪ ዞኖች ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የዳውሮ-ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች በደቡብ አፍሪካ ሲያካሒዱት የቆዩትን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ቅዱስነታቸውና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዙት የልዑካን ቡድን አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ክቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገው
ላቸዋል።

በመቀጠልም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል መርሐ ግብር የሚካሔድ ሲሆን በዚሁ መርሐ ግብር ላይም ቅዱስ ፓትርያርኩ ትምህርተ ወንጌል፣ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ሰጥተው የአቀባበል መርሐ ግብሩ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

"እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰራው በላይ ነው የሰራሽው" ከንቲባ አዳነች አቤቤን ለማመስግነ የተነገረ ቃል።
10/05/2024

"እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰራው በላይ ነው የሰራሽው" ከንቲባ አዳነች አቤቤን ለማመስግነ የተነገረ ቃል።

አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ . . .ለእናንተ ግን ወዮላችሁና መግቢያ ፈልጉ!ሚያዝያ ፳፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጸሐፊ፥እንዲሁም የምዕራብና የደቡብ አፍሪካ አኅጉረ ...
03/05/2024

አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ . . .ለእናንተ ግን ወዮላችሁና መግቢያ ፈልጉ!
ሚያዝያ ፳፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጸሐፊ፥እንዲሁም የምዕራብና የደቡብ አፍሪካ አኅጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ:-ሊቀ ማዕምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፥የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ:-ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መምህር ዋስይሁን በላይ በግፍ ታስረዋል።
ቤተ ክርስቲያን መስቀል ላይ ናት፤ ይህ ደግሞ የቀረች አንዲቷ ቀይ ካርድ ነበረችና መዘዟት፤ እነዚህን ሰዎች መርምሯቸው ግን ወንጀል አታገኙባቸውም።

ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ለ582 ደቀመዛሙርት መዓርገ ክህነት ሰጡ።ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የምዕራብ አርሲ ፣ጉጂ፣ምዕራብ ጉጂ  ፣ቦረና  ሊበን  አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶ...
28/04/2024

ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ለ582 ደቀመዛሙርት መዓርገ ክህነት ሰጡ።

ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የምዕራብ አርሲ ፣ጉጂ፣ምዕራብ ጉጂ ፣ቦረና ሊበን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለ582 ደቀመዛሙርት መዓርገ ክህነት በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ደብረ አስቦ አ/ተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰጥተዋል።

ለዲቁና ለቅስና እና ለቁምስና ፈተና ሲፈተኑ የቆዩ አግልጋዮች 546 ዲቁና፤34 የቅስና እና 3 የቁምስና መዓርግ የተሰጣቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 171 ዲቁና እና 5 የቅስና መዓርግ በአጠቃላይ 176 የተሰጣቸው በማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማእከል እና ሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ጋር በመተባበር ሲያስተምራችው የነበሩ ደቀመዛሙርት ናቸው።

ማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማእከል ከሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር በዚህ ዓመት ከዚህ ቀደም መዓርገ ክህነትን የተቀበሉ 61 ካህናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 237 መዓርገ ክህነት እዲቀበሉ አድርጓል።

በዛሬው ዕለት ክህነት የተቀበሉት አገልጋዮች በአካባቢው ያለውን የካህናት እጥረት ለመፍታት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።

ዘማሪ እዝራ ኃይለ ሚካኤል በቅዱስ ሲኖዶሱ ፈቃድ ቀኖናውን ጨርሶ (10 ወራት በቤተክርስቲያን አጸድ ተጠግቶ) ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መመለሱን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብ...
27/04/2024

ዘማሪ እዝራ ኃይለ ሚካኤል በቅዱስ ሲኖዶሱ ፈቃድ ቀኖናውን ጨርሶ (10 ወራት በቤተክርስቲያን አጸድ ተጠግቶ) ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መመለሱን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አሳውቋል!

የምዕራብ ሸዋ ሀገረ  ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል  ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ጨርሰዉ ወደ...
26/04/2024

የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ጨርሰዉ ወደ ሀገረ ስብከታቸው በሰላም ተመልሰዋል።

ወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ....በሆስፒታል ንግድ ፍቃድ የቤተእምነት ተልዕኮ እና ዓላማ የሚፈጽመው ተቋም ***ወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል በህክምናው ዘርፍ ላይ ዘር ቀለም እምነት...
26/04/2024

ወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ....በሆስፒታል ንግድ ፍቃድ የቤተእምነት ተልዕኮ እና ዓላማ የሚፈጽመው ተቋም
***

ወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል በህክምናው ዘርፍ ላይ ዘር ቀለም እምነት ሳልል ህመምተኞችን አገለግላለው ብሎ ወደ ዘርፉ የገባ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ነው።

ነገር ግን በግልጽ ይህ ሆስፒታል ራዕዬ "የኢየሰስ ክርስቶስ የምስራችን ወንጌል ማብሰር እና ደቀመዝሙር ማፍራት ነው " ብሎ ያለእፍረት በሆስፒታል የንግድ ፍቃድ ሰዎችን ሃይማኖታቸውን የማስካድ ጭካኔ የተሞላው የቤተእምነት ልምምድ ያደርጋል።

የሆስፒታሉ ተቋማዊ ተልዕኮ ምንድነው ተብሎ ሲጠየቅም " የምስራችሁን ወንጌል ማብሰር " የሚለውን ሐሳብ ከተልዕኮዎቹ መሃል አንዱ ያደርጉታል።

የሥራ ማስታወቂያ ሲያወጣ ደግሞ ተልዕኮ እና ራዕዩን የሚያከብር ግለሰብ ነው የምፈልገው ይልሃል።

ህመምተኛ እና አስታማሚ ከፍተኛ ክፍያ ከፍሎ እየተገለገለ የግዴታ ጸሎት እና እነርሱ በቤተእምነታቸው የሰሩት መንፈሣዊ ፊልሞች የግድ ይታዘዝብሃል።

መንግስትም ሆነ በንግድ አዋጁ መሰረት የንግድ ተቋማትን የሚቆጣጠሩ መዋቅር ወይም የጤና ሚኒስተር ይህን ተቋም የመገሰጽ ሞራልም አቅምም የላቸውም። ምክንያር ከተባለ ባለቤቶቹ የውጪ ሀገር ዜጋ ናቸው። ፕሮጀክቱም የሚካሄደው እንደ USAID ባሉ ግዙፍ የውጪ ተቋማት ነው።(ለእዚህ ማሳያ የሆስፒታሉ የአዲሱ የቀዶ ህክምና ክፍል ህንጻ ፕሮጀክት ማሳያ ነው)

ወዳጄ እዚህ ሀገር እኩልነት እንደሚባል ቃል የሚያሰቃይ ህመም የለም። ፌዴራል ፓሊሱ የሰራው ትክክል አይደለም...እዚህ ጋ ትክክል ያልሆነ ሥራ አለ ሲባል የእራሳቸውን በጌታ ዙፋን የአንተን በሴኩላሪዝም መደብ ይመድባሉ።

ይህን ይህን በጉያው የታቀፈ ሰው ሁሉ ነው ስለሴኩላሪዝም መምህር ነኝ ብሎ ሊያስተምር የሚንተባተበው።

ሴኩላሪዝም ....አፈር ድቼ በልተሻል።

Demelash kassaye -Arba Minch

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when 1 Birr posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share