17/04/2026
ኢትዮጵያውያን ከገቢያቸው 58.5 በመቶውን ለምግብ ፍጆታ ያውላሉ‼️
የዓለም ባንክ ይፋ ባደረገው አዲስ አህጉራዊ ሪፖርት፤ በኢትዮጵያ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና የሚያሳይ አሳሳቢ አኃዝ ይፋ አድርጓል።
ሪፖርቱ እንደሚጠቁመው፣ ኢትዮጵያውያን ከአጠቃላይ ወጪያቸው ውስጥ ከ58.5 በመቶ በላይ የሚሆነውን ለምግብ ፍጆታ ብቻ ለማዋል ተገደዋል።
የዋጋ ንረቱ የከተማ ነዋሪዎችን ብቻ ሳይሆን፣ በገጠር የሚገኙ ዜጎችንም በከፍተኛ ሁኔታ እየፈተነ ይገኛል።
የሸቀጦች ዋጋ መጨመር በገጠር ያለውን የኑሮ ሚዛን እያናጋው መሆኑ ተመልክቷል።
በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ቀውስ የነዳጅ ዋጋን በመጨመር፣ በሀገር ውስጥ ያለውን የትራንስፖርትና የምርት ዋጋ ይበልጥ ሊያናረው እንደሚችል ባንኩ አስጠንቅቋል።
ይህ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከምግብ ዋስትና ጋር ተዳምሮ የዜጎችን የመግዛት አቅም ይበልጥ ሊያዳክም እንደሚችል ተጠቁሟል።
Addis Truth