Emmaus - ኤማሁስ

Emmaus - ኤማሁስ ይህ ገጽ ኦርቶዶክሳዊ ትውፊት ላይ ትኩረት ያደረጉ ጽሑፎች እና ቪዲዮዎች የሚቀርቡበት ነው።

ሙሉው ቪዲዮ ይኸው።
20/09/2025

ሙሉው ቪዲዮ ይኸው።

#አነቃቂንግግሮች #ኤማሁስ #ይወዳጁን #የአዲሱዘመንእንቅስቃሴ #ሂንዱይዝም #ኦርቶዶክሳዊነት

 #ኤማሁስፖድካስት "የአዲሱ ዘመን ሃይማኖት/New age religion/"ን በመመልከት 2018ን ጀምራለች። ቅዳሜ ይጠብቁን
18/09/2025

#ኤማሁስፖድካስት "የአዲሱ ዘመን ሃይማኖት/New age religion/"ን በመመልከት 2018ን ጀምራለች። ቅዳሜ ይጠብቁን

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

ኤማሁስ ጥያቄ እና መልስ  #3 ደርሰናል። በዚህ ክፍል ከጋብቻ ጋር በተያያዘ የቀረበልንን ጥያቄ ለመመለስ ሞክረናል። ይከታተሉ
30/08/2025

ኤማሁስ ጥያቄ እና መልስ #3 ደርሰናል። በዚህ ክፍል ከጋብቻ ጋር በተያያዘ የቀረበልንን ጥያቄ ለመመለስ ሞክረናል። ይከታተሉ

ይኼ ጥያቄ በቴሌግራም አድራሻችን () ከተቀበልናቸው ጥያቄዎች መሀከል አንዱ ነው። የቀረበውን መልስ ያድምጡ። እዚሁ ላይ ተጨማሪ ወይንም ሌላ ጥያቄ ካለዎት ደግሞ በተቀመጠው ሊንክ ...

"ክፋትን እፈጥራለሁ" በሚል ርእስ በኤማሁስ መጽሔት የወጣው የብንያም ጽሑፍ ላይ ኤልያስ ገብረሥላሴ ይኼንን አስተያየት ሰጥቷል።
27/08/2025

"ክፋትን እፈጥራለሁ" በሚል ርእስ በኤማሁስ መጽሔት የወጣው የብንያም ጽሑፍ ላይ ኤልያስ ገብረሥላሴ ይኼንን አስተያየት ሰጥቷል።

መከራ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ድንገተኛ የሆነ ክስተት አይደለም ። ፍቅር በሆነው እግዚአብሔር ለጥቅማችን የሚፈቀድ የእርምት መንገድ ነው እንጂ ። በየዘመኑ ቤተክርስቲያን በወቅታ...

ባለፈው ጊዜ የጥያቄ እና መልስ መርሐግብር ለማዘጋጀት አስበን ጥያቄዎችን በቴሌግራም አድራሻችን () ስንቀበል ቆይተናል። ዛሬ  #ቅዱሳትመጻሕፍትን በተመለከተ የደረሰንን ጥያቄ በመመልከት ጀምረ...
16/08/2025

ባለፈው ጊዜ የጥያቄ እና መልስ መርሐግብር ለማዘጋጀት አስበን ጥያቄዎችን በቴሌግራም አድራሻችን () ስንቀበል ቆይተናል። ዛሬ #ቅዱሳትመጻሕፍትን በተመለከተ የደረሰንን ጥያቄ በመመልከት ጀምረናል። ይከታተሉ። መልስ ቢቀርብባቸው የምትሏቸውን ጥያቄዎቾንም ያድርሱን::

Share your videos with friends, family, and the world

15/08/2025

Theosophia በሚባለው መደላድል ከምናውቃቸው ወንድሞች አንዱ የሆነው ዘሚካኤል በኤማሁስ መጽሔት ላይ "ስለ ሕይወት ትርጉም መታጣት" በሚል ርእስ ያስነበበን ጽሑፍ ላይ የሚከተለውን ትችት አቅርቧል። በቀጣይ ከኤማሁስ ሁለት የጽሑፍ ምላሾች ይቀርባሉ። ወንድማችን ዘሚካኤልን ስለ አበርክቶው እናመሰግነዋለን።

መልካም ንባብ።

፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠ ፠

አብዛኛው የነገረ መለኮት ውይይት መድረኮች ላይ የሚያዘወትር ሰው ያውቃቸዋል እና ለእኛም ደግሞ የቅርብ ወንድሞቻችን ናቸው። ዘወትር ከተለመዱ ቀሊል ሃሳቦች ይልቅ አብዛኛውን ጊዜ ማእከላዊ እና ጠንካራ ሃሳቦች ላይ ያዘወትራሉ። እና ደግሞ በቅርቡ ብዙ ጠቃሚ ሃሳቦችን የያዘ አንድ ዲጂታል መፅሔት አውጥተዋል። እኝህ ወንድሞች አንድ ላይ ኤማሁስ ይባላሉ። ዛሬ በዚህ መጽሔት ላይ ከተፃፉ ብዙ ደስ ከሚያሰኙ ፅሁፎች መካከል በወንድማችን ዮሃንስ ሙሉጌታ የተፃፈውን ፅሁፍ ሃሳብን ልሰጥበት መጥቻለው። ፅሁፉ ሙሉ በሙሉ በትህትና እና በፍቅር የተፃፈ እንጂ ለነቀፋ እና ለማስነወር በፍፁም የተፃፈ አይደለም። ነገር ግን አንዳንድ ነገሮች አሳማኝ ያልሆኑ ስለመሰለኝ አስተያየት ልሰጥበት ወደጃለው። ፅሁፉ የህይወትን ትርጉም በማግኘት እና በራስ ወዳድነት መሃል ያለውን ተቃርኖ ለማሳየት የተፃፈ ነው። እና ራስ ወዳድነት እና ገለልተኝነትን በፍልስፍና እና በቤተክርስትያን ትምህርት ከነገረ እግዚአብሔር እና ከነገረ ቤተክርስትያን አንፃር ይተቻል። ብዙዎቹ የምንስማማባቸው መሰረታዊያን ናቸው። ስለዚህ ነገር ላላረዝም ቅር ያሰኙንን ብቻ እፅፋለው። ሃሳቡን በምል ለመረዳት ግን አስቀድማችሁ ድረገፃቸው ላይ ገብታችሁ እንድታነቡ ጋብዛችኋለው።

ፅሁፉ አስቀድሞ ፍቅርን ከነገረ እግዚአብሔር አንፃር ይተረጉመዋል።

በመሰረታዊነት እግዚአብሔር እውነት ስለሆነ እና ሁሉም ነገር ህልውናው በእግዚአብሔር ስለሆነ ህልውና ያለው እውነት እንጂ ሃሰት አይደለም ብሎ ይጀምራል።

እዚህ ላይ ጸሐፊው እውነትን የተረጎመበት ትርጉም ግልፅ ካለመሆኑ የተነሳ ለመረዳት አስቸጋሪ ነው። እውነትን ግን በአብዛኞቹ ዘንድ ተቀባይነት ባለው ትርጓሜ ብንተረጉመው፦ ሁለት አይነት ትርጓሜ ይኖረዋል ነገረ እውቀታዊ(epistemological ) ሁለተኛው ደግሞ ከዊናዊ(ontological ) ነው

ነገረ እውቀታዊ

Truth is the quality of statement belief being in agreement with reality, facts, or what is the case.

እውነት የሆነውን ነው ያልሆነውን ደግሞ አይደለም ማለት ነው። (Aristotle Metaphysics, IV. 7))

በዚህ ትርጓሜ መሰረት እውነትነት እና ሃሰትነት ለሰው ልጆች እምነት የምንሰጠው ዓረፍተ ነገራዊ ጠባይ ወይም ደግሞ ስለ ህልውና (reality) የሚናገሩ ዓረፍተ ነገሮች እንጂ በራሳቸው አቃኒም(concert reality)ያላቸው ህልውናዎች አይደሉም። ስለዚህ በዚህ ትርጉም መሰረት ሃሰት ብቻ አይደለም እውነትም ህልውና የለውም።

ይሄ አስቀድመን የተመለከትነው የእውነት ትርጉም ነገረ እውቀታዊ ሲሆን ሁለተኛው ትርጓሜ ደግሞ በቶማስ አኳይነስ የተብራራው(ምንም እንኳን ከርሱ በፊት ቢኖርም) ከዊናዊ የእውነት ትርጉም ነው (ontological truth)

ከዊናዊ (ontological) የእውነት ትርጉም ግን በአእምሮ አይወሰንም። ነገሮች በህልውናቸው እና በባህሪያቸው ሊኖራቸው የሚገባውን ነገር መያዝ ነው እውነት ። ለምሳሌ አንድ ሰው እውነተኛ ሰው የሚሆነው የሰውነትን ባህርያት ካሟላ ነው። ሰውን የሚመስል አሻንጉሊት እውነተኛ ሰው አይደለም። ጥንታዊ በሆነው philosophy እውነትነት እንደ መልካምነት እና ውበት ነገሮች ህልውና ስላላቸው ብቻ የሚኖራቸው ጠባይ ነው። እና ህልውና ያለው ነገር በሙሉ መታወቅ የሚችል ነው። ስለዚህ በማንም አእምሮ በመታወቅ ሳይሆን በራሱ ያለው ህልውና የአንድ ነገር ከዊናዊ እውነት ሲሆን ነገረ እውቀታዊ እውነት ግን በሰዎች አእምሮ እና በነገሮች እውነትነት መሃል ያለ ተያያዥነት ነው።
በአጭሩ ግን ለማስረዳት ከዊናዊ እውነትነት ነገሮች በባህሪያቸው ሊኖራቸው የሚገባውን ነገሮች መያዝ ነው እውነተኛ ሰው ለመሆን የሰውነትን ባህሪይ መያዝ ነው ሰው የሚመስል ሰው ያልሆነ ነገር ontological truth ይጎድለዋል ማለት ነው

ነገረ መለኮታዊ ትርጓሜውን ካየነው ባህርይው ከህልውናው ጋር ፈፅሞ አንድ የሆነ እውነተኛው ህልውና እግዚአብሔር ስለሆነ እግዚአብሔር እራሱ እውነት ነው (veritas) በማለት classical theists ያብራራሉ። (ባህርይው እና ህልውናው የማይነጣጠል ፍጹም ወጥ ነው (his existence is identical his essence) የሚለው ትምህርት ኦርቶዶክሳዊ እንዳልሆነ ግን ልብ በሉ)።
ከዊናዊ የእውነት ትርጓሜ እንደሚከተለው ይሆናል፦

Truth is being of thing in so far as it is intelligible to an intellect the conformity of things essence and existence to the divine idea and to its own nature.

እውነት ማለት የአንድ ፍጥረት ህልውና ለአእምሮ የሚገለጥበት መጠን ነው ይህም የፍጥረቱ ባህርይና ህልውና ከመለኮታዊ እሳቤና ከገዛ ተፈጥሮ ጋር መስማማቱ ነው።

ስለዚህ በዚህ ትርጓሜ አንድ ነገር በህልውና እውነትም ሃሰትም ሊሆን ይችላል። ስለዚህ በዚህ ትርጓሜ መሰረት ደግሞ እውነት ብቻ ሳይሆን ሃሰትም ህልውና አለው (እውነተኛ ያልሆነ ሰው ነገር ግን ሰውን የሚመስል ህልውና)።

ስለዚህ ፀሃፊው እውነት እንጂ ሀሰት ህልውና የለውም ያለበትን የእውነት እና የሀሰት ትርጉም ማስቀመጥ አለበት።

በመጨረሻም እውነት ነገረ እውቀታዊ ቢሆን እውነትም ሃሰትም ህልውና የላቸውም ምክንያቱም በዚህ ትርጉም እውነትነት የዓረፍተ ነገር ጠባይ ነው ከዊናዊ ቢሆን ደግሞ እውንትም ሃሰትም ህልውና አላቸው። ምን አይነት የእውነት ትርጉም እውነትን ህልውና ሐሰትን ደግሞ የህልውና አለመኖር እንዳደረጋቸው ጽሑፉ ግልጽ ስላላደረገ አንብበን ማድነቅም ሆነ መተቸት አስቸጋሪ አድርጎብናል😁

ክፋትን በተመለከተ በቀጣይ ጽፋለው ይቆየን

ወዳጆች እንዴት ሰንብታችኋል?  #ኤማሁስመጽሔት እየተነበበችና ብዙ ግብረ መልስ ይዛ እየመጣች ነው። ይህም ለእኛ እጅግ አስደሳች ነገር ነው። "ሐሳቦች መዘዝ አላቸው" በሚል ርእስ ኤርምያስ ክ...
14/08/2025

ወዳጆች እንዴት ሰንብታችኋል?
#ኤማሁስመጽሔት እየተነበበችና ብዙ ግብረ መልስ ይዛ እየመጣች ነው። ይህም ለእኛ እጅግ አስደሳች ነገር ነው። "ሐሳቦች መዘዝ አላቸው" በሚል ርእስ ኤርምያስ ክንዴ የከተበውን መጣጥፍ በዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆነው ወዳጃችን መሐሪ ዘመልዐክ (PHD) እንደሚከተለው ቃኝቷታል።

መልካም ንባብ።

ከዛሬ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት የእጓለ ገብረ ዮሐንስ ‘የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ’ ለመጀመሪያ ጊዜ ካነበብኹ በኋላ ጸሐፊውን ከዚያ በፊት አለማወቄ ገርሞኝ እንደነበር አስታውሳለኹ .....

04/08/2025
ኤማሁስ ቅጽ1፣ ቁጥር አንድን በዚህ ሊንክ ገብተው ያገኟታል። መልካም ንባብ
03/08/2025

ኤማሁስ ቅጽ1፣ ቁጥር አንድን በዚህ ሊንክ ገብተው ያገኟታል። መልካም ንባብ

. . . የዘመናችን ተዋሥኦ በይዘቱም ሆነ በመንገዶቹ በግልብነት በእጅጉ የተጠቃ ነው ። ‘በይዘቱ እንዴት ?’ቢባል ሁነቶች ላይ ያተኮረ እና ወቅታዊነትን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ ። አንድም አ...

"እግዚአብሔር ካለ በእርግጥ ክፋት በዓለም ላይ ለሺህ ዓመታት እንዲነግሥ ይፈቅድ ነበር?" የብንያም ጽሑፍ ይኼንን ጠንከር ያለ ርእሰ ጉዳይ የተመለከተ ነው። ሙሉውን በቀጠሮአችን ቀን ይጠብቁ
31/07/2025

"እግዚአብሔር ካለ በእርግጥ ክፋት በዓለም ላይ ለሺህ ዓመታት እንዲነግሥ ይፈቅድ ነበር?" የብንያም ጽሑፍ ይኼንን ጠንከር ያለ ርእሰ ጉዳይ የተመለከተ ነው። ሙሉውን በቀጠሮአችን ቀን ይጠብቁ

ቆይታ ከኤማሁስ መጽሔት ኤዲተር ጋር
30/07/2025

ቆይታ ከኤማሁስ መጽሔት ኤዲተር ጋር

#መጽሔት #ኤማሁስ #ቤተክርስቲያን

ሐምሌ 27 ይጠብቁንኤማሁስ ፕሬስ ከሐምሌ ፣ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በየሦስት ወሩ ወደ ሕዝብ የምትደርስ ፥ ‘ኤማሁስ’ የተሰኘች (ለጊዜው ዲጂታል) መጽሔት ማሳተም ይጀምራል ። የመጽሔቱ ዓላማ ...
21/07/2025

ሐምሌ 27 ይጠብቁን

ኤማሁስ ፕሬስ ከሐምሌ ፣ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በየሦስት ወሩ ወደ ሕዝብ የምትደርስ ፥ ‘ኤማሁስ’ የተሰኘች (ለጊዜው ዲጂታል) መጽሔት ማሳተም ይጀምራል ። የመጽሔቱ ዓላማ በዘመናችን ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ በሚደረገውም ሆነ በሌላ ዘርፎች በሚከናወነው ሕዝባዊ ተዋሥኦ ውስጥ በጉልህ የሚታየውን ግልብነት በተቻለ አቅም መሙላት ነው ።
ኤማሁስ ‘መጽሔት’ ብትሰኝም ቅሉ ይዘቷ ለአካዳሚያዊ ጽሑፎች የሚቀርብ ይሆናል ። ከኤማሁስ ጀርባ ያለው ሐሳብ በትምህርቱ ዓለም (ቢያንስ በፊት) እንደሚደረገው ጥልቀት ያላቸው ጽሑፎችን ማስተናገድ ሲሆን ነገር ግን አሁን እየሆነ እንዳለው ከሕዝባዊው ተዋሥኦ ያልተነጠለ ፣ ይልቁንም በአንባቢነትም ሆነ በጸሐፊነት ለመሳተፍ ለሕዝብ ክፍት የሆነ ተዋሥኦ መፍጠር ነው ።
በመሆኑም ኤማሁስ ከተለመዱት መጽሔቶች በተለየ መልኩ ከሁነቶች ይልቅ መሠረታዊ ሐሳቦች ላይ ያተኮሩ ፥ ወቅታዊ ጉዳዮችን ያማከሉ ነገር ግን ፍልስፍናዊ ይዘት እና ውቅር ያላቸውን ጽሑፎች ታስተናግዳለች ። የጸሐፊውን ስሜቶች እና አስተያየቶች የምታስተናግድ ፥ ነገር ግን ምክንያታዊነት ያልተለያቸው እንዲሁም የፍልስፍና እና የሐቅ መሠረት ላይ የቆሙ መሆናቸውን የምትጠይቅ ፥ ይህም መሆኑ እንዲታወቅ እንደ ትምህርታዊ ጽሑፎች በማጣቀሻዎች መደገፋቸውን የምታስገድድ ፥ ነገር ግን ጽሑፋቸውን በጥቂት ገጾች እንዲገድቡ ባለማስገደድ ለሐሳባቸው ሰፊ ነጻነት የምትሰጥ መድረክ ትሆናለች ። በዚህ ልክም ሆዷን አስፍታ በብዙ ገጾች ወደ ሕዝብ ትደርሳለች ።
የኤማሁስ ተዋሥኦ ብዙ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ፥ ብዙ ዓይነት ሐሳቦችንም የሚያሳትፍ ይሆናል ። የስምምነት እና የመደጋገፍ ብቻ ሳይሆን የሙግትም መድረክ ነው ለመፍጠር የምናልመው ። ከአባቶቻችን ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን ትምህርቷን እና ትውፊቷን የጠበቀችው እንዲህ ባለ ፥ ክርስቲያኖች እውነትን ፍለጋ በሚሟገቱበትም ጭምር ፥ ተዋሥኦ በመሆኑ ፥ እንዲህ ያለው ሙግት ለእኛ ዐዲስ ነገር ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ትውፊት የማስቀጠል ተግባር ነው ። ሌላው ቀርቶ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ያሉ ሰዎች እንኳን ሊሞግቱን ቢወዱ በቀናነት ለማስተናገድ በራችን ክፍት ይሆናል ። ክርስቲያኖች እምነታቸው ባለማወቅ የሚጠበቅ ሳይሆን ተፈትኖ ያለፈ እና የጠራ መሆን እንዳለበት ስለምናምን ፥ አንድም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለነውን ከማጽናት ባለፈ ሌሎችንም መጥራትም የተልዕኮአችን ዋና አካል ስለሆነ ፥ የተዋሥኦውን አድማስ በተቻለ መጠን ማስፋት አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን ። ስለዚህም እንዲህ ያለውን ጥልቅ እና እውነትን መዳረሻው ያደረገ ተዋሥኦ የሚሹትን ሁሉ በማንበብም ፣ በመጻፍም ይሳተፉ ዘንድ እንጋብዛለን ።
በዚህ መንፈስ ፣ የኤማሁስ የመጀመሪያዋ እትም ሐምሌ 27 ፣ 2017 ዓ.ም. ወደ እናንተ ትመጣለች ። ይጠብቁን

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Emmaus - ኤማሁስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share