
09/08/2025
ፓስተር ቼሬ እስራኤልን ለምን አስደነበራት ?
ፓስተር ቸሬ የናደው እስራኤል ኢምባሲ በሚሊየኖች ያወጣበት የደከመበት ትርክት ነው
የእስራኤል ኤምባሲ እጅግ በተቀናጀ መንገድ ከፕሮቴስታንት መሪዎች ጋር በመሆን እጅግ በጣም አሳዛኝ ስራ እየሰራ ነው። ይኸውም የእስራኤልን ትርክት ኢትዮጵያን መሰረት አድርገው ለመላው አፍሪካ ለማሰራጨት አንድ ትልቅ ፕሮጀክት አላቸው።
ይህ ፕሮጀክት በዋንኛነት የሚመራው በዶክተር አበራ በለጠ በተባለው የኤልሻዳይ ቲቪ ባለቤትና ሰባኪ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ታላላቅ የሆኑ የወንጌላውያን መሪዎች በኢትዮጵያ ከዚያም አለፍ ብሎ በአፍሪካ የሚሳተፉበት ነው።
ይህ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ዋና አቀናጅነት የሚሰራ ሲሆን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ፓስተሮች የሚገኙበት ከአሜሪካ ጭምር የሚመጡ የወንጌላውያን መሪዎች የሚሳተፉበት ለመጽሐፍ ቅዱሷ የተጠቀሰችውን እስራኤልን ጥበቃ የሚል ትርክት የሚፈጠርበት ነው።
በዚህ ላይ ትልልቅ የወንጌላውያን መሪዎች ፓስተር ፃዲቁ አብዶን ጨምሮ ሌሎችም የአፍሪካውያን የወንጌል መሪዎች የሚሳተፉበት ነው። ይህ ትልቅ ፕሮጀክት በሰፊው ሲሰራበት ቆይቷል።
ይህ ብቻ ሳይበቃ በተለያዩ የፕሮቴስታንት ሚዲያዎች በየጊዜው በመቅረብ የእስራኤሉ አምባሳደር ሌሎችም ጭምር ይህንኑ ትርክት በየጊዜው ሲገልፁ ቆይተዋል።
ትርክት የመቀየር ስራ በሰፊው ለመስራት ተሞክሯል ::
ታዲያ ይህ ሁሉ ባለበት ነበረ በአንድ መድረክ ላይ የተናገራት የተወሰነች ደቂቃ ንግግር ለዘመናት ሲገነቡት የነበረውን ትርክት በአንዴ አፈር ድሜ ነው ያበላችው።
በፕሮቴስታንቱና በእስራኤል መካከል ያለው ያልተቀደሰ ጋብቻ ፍጹም ሰብአዊነትን ያጣ ተግባር ነው። ይህንን እንግዲህ በድፍረት በመናገሩ ነው ፓስተር ቸሬ ላይ ያወጡት።
ህፃናትን በግፍ እየጨፈጨፉ በረሃብ እየቀጡ እንደዚህ አይነት ሀይማኖተኝነት የለም ::
© Abdurahim Ahmed