Fact News

Fact News Fact news : Keep watching For All latest updates Of News All over woreld

Fact news : Keep watching For All latest updates Of News All over woreld :::::::::::Fact news : Keep watching For All latest updates Of News All over woreld

10/01/2022

ለሰዎች ገደብን አብጅላቸው
ያላመንክበትን ነገር ካለምንም የጥፋተኝነት ስሜት እምቢ ማለትን መልመድ መልካም ልማድ ነው፡፡ የሰው ስሜት ላለመጉዳትና ክፉ መስሎ ላለመታየት ለሁሉም ነገር እሺ ማለት ማንነትህን እንደሚሸረሽረው አትርሳ ፡፡

https://www.facebook.com/Newsfactnews/

Fact news : Keep watching For All latest updates Of News All over woreld

በደንብ አስተዉሉ ምን ይታያቺሆል?
05/01/2022

በደንብ አስተዉሉ ምን ይታያቺሆል?

ጠዋት ፊልትማን ነገ ወደ አዲስአበባ ይገባሉ ተባለ ከሰአት ደግሞ ከስልጣናቸዉ ሊለቁ ነዉ አረ ጎበዝ አታደናክሩን እንጂ?
05/01/2022

ጠዋት ፊልትማን ነገ ወደ አዲስአበባ ይገባሉ ተባለ
ከሰአት ደግሞ ከስልጣናቸዉ ሊለቁ ነዉ
አረ ጎበዝ አታደናክሩን እንጂ?

በወራሪ ቡድኑ የጥፋት ተግባር ተሰብሮ የነበረው የአለውሃ ድልድይ በአዲስ  የብረት ድልድይ   የግንባታ ስራው  ተጠናቆ ለትራንስፖርት አግልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ከፍት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች...
05/01/2022

በወራሪ ቡድኑ የጥፋት ተግባር ተሰብሮ የነበረው የአለውሃ ድልድይ በአዲስ የብረት ድልድይ የግንባታ ስራው ተጠናቆ ለትራንስፖርት አግልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ከፍት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አሰተዳደር አሰታወቀ።

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ ዲስትሪክት ባለፉት ቀናት አዲሱን የብረት ድልድይ ግንባታ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ ሲያድርግ ቆይቷል ።

ይህን ተከትሎም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረውን ይህን ድልድይ በአዲስ የብርት ድልድይ በመገንባት መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት ዳግም እንዲጀመር ተደርጓል።

የብረት ድልድዩ እስከ 600 ኩንታል ወይም 60 ቶን ድረስ መሸከም የሚችል አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ነው።
የብረት ድልድዩ አጠቃላይ ርዝመቱ 54 ነጥብ 86 ሜትር ነው።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት እና የምርት ምልልስ ታሳቢ ያደረገ ደረጃውን የጠበቀ ድልድይ ለመገንባት እየተነቀሳቀሰ ሲሆን
በአሁኑ ወቅትም የዲዛይን ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ ወደ ግንባታ ስራ ይሸጋገራል።

የአለውሃ ድልድይ በሰሜን ወሎ ዞን ከወልድያ ወደ ቆቦ በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ነው።

አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈጸመበት ወቅት ለህዝቡ እውነተኛ አባት ሆነው ለቆዩት ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ተሽከርካሪ ተበረከተታህሳስ 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው የህወሓ...
02/01/2022

አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈጸመበት ወቅት ለህዝቡ እውነተኛ አባት ሆነው ለቆዩት ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ተሽከርካሪ ተበረከተ

ታህሳስ 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው የህወሓት ቡድን በተወረረበት ወቅት ለህዝቡ እውነተኛ አባት ሆነው ለቆዩት ለብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ተሽከርካሪ ተበረከተላቸው።

የተሽከርካሪ ስጦታውን የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ እና የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ አስረክበዋቸዋል።

የብጹዕነታቸውን ተሽከርካሪ አሸባሪው የህወሓት ቡድን እንደዘረፋቸው ይታወቃል።

ዛሬ በስጦታ የተረከቡት ተሽከርካርም ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መሆኑም ተገልጿል።

አቡነ ኤርሚያስም መንግስት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት መርሳና ጊራናን በመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሠ ነው***********************የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት መርሳና ጊራናን በመቆጣጠር ወደፊት ...
17/12/2021

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት መርሳና ጊራናን በመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሠ ነው
***********************

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት መርሳና ጊራናን በመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሠ ነው፡፡

የአትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በቆቦ ግንባር ቀደም ብሎ የዞብል ከፍተኛ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን፣ በራያ ሰሜናዊ አቅጣጫ ያሉትን ከፍተኛ ቦታዎችን ጨምሮ ተቆጣጥሯል፡፡ በዞብል ደቡብ አቅጣጫ ደግሞ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የነበረው የወገን ጦር አሁን ደግሞ የጉራ ወርቄ ከፍተኛ ሰንሰለታማ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ በማጽዳት፣ ቀደም ብሎ የተቆረጠውን የወልድያ መቀሌ መሥመር አሰፋፍቶ፣ ወደ ወልድያ በቅርብ ርቀት እየገሠገሠ ይገኛል፡፡

ባለፈው ጊዜ ውጫሌ ከተማን ነጸ ያወጣው የወገን ጦር፣ በዚሁ ግንባር የውጫሌ ወረዳን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የውርጌሳ፣ የሊብሶ፣የጊራና፣የመርሳ፣የኪሌ፣ከተሞችንና በሰሜን ወሎ የሀብሩ ወረዳን ከፍተኛ ሰንሰለታማ ተራሮችን በእጁ አስገብቷል፡፡

በእነዚህ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች ጀግኖቹ የወገን ጥምር ጦር በንሥሮቹ አየር ኃይላችን በመታገዝ ጠላትን ከመርሳ በስተጀርባ ቆርጦ በመግባት፣ በውጫሌና ውርጌሳ መካከል የነበረውን ጠላት ሙሉ በሙሉ ደምስሰውታል፤ ምርኮኛና ቁስለኛም አድርገውታል፡፡ የአካባቢው ኅብረተሰብ ከወገን ጥምር ጦር ጋር በመቀናጀት፣ እግሬ አውጪኝ ብሎ የሚሸሸውን ጠላት ከየጢሻው እየመነጠረ በመደምሰስ አኩሪ ጀብድ ፈጽሟል፡፡ ጠላትም የዘረፈውን ንብረትና ተተኳሾቹን ፈጽሞ ይዞ እንዳይወጣ አድርጎታል፡፡ የወገን ጥምር ጦር በወልድያና ሐራ ከተሞች መካከል የሚገኘውንና መውጫ ያጣውን ጠላት ለመደምሰስ፣ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው፡፡
https://www.facebook.com/Newsfactnews/

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተደረገው የታፍ ማሻሻያበአዲስ አበባ በሚኒባሶች እና ታክሲዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ተደርጓልሚኒባስ (ቅጥቅጥ...
17/12/2021

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተደረገው የታፍ ማሻሻያ

በአዲስ አበባ በሚኒባሶች እና ታክሲዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ተደርጓል

ሚኒባስ (ቅጥቅጥ ወይም ሃይገር ባስ) የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ በሚኒባስ በኪሎሜትር ከ40 ሳንቲም ወደ 45 ሳንቲም ከፍ የተደረገ ሲሆን÷ በሚኒባሶች የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛው 1 ብር ሲሆን÷ ከፍተኛው ደግሞ 2 ብር ሆኗል።

የአውስትራሊያ የስነጥበብ ምክር ቤት የዚህ አመት የክብር ፌሎውሺፕ እድል የተሰጣቸውን ስምንት አርቲስቶች ስም ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ለሁለት አመት የሚቆየው የፌሎውሺፕ እድል ወደሰ...
17/12/2021

የአውስትራሊያ የስነጥበብ ምክር ቤት የዚህ አመት የክብር ፌሎውሺፕ እድል የተሰጣቸውን ስምንት አርቲስቶች ስም ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ለሁለት አመት የሚቆየው የፌሎውሺፕ እድል ወደሰማኒያ ሺህ ዶላር የሚያወጣ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በዚህ እድል አርቲስቶች የፈጠራ ስራቸውን ለማዳበርና ሙያቸውን ለማሳደግ የሚችሉበት ነው፡፡

ዛሬ ይፋ ከሆኑት ስምንት አለም አቀፍ አርቲስቶች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያዊው የፖፕና ሬጌ ድምፃዊው ናትናኤል ይመር ወይንም በቅፅል ስሙ ናቲ ማን አንዱ ነው፡፡

የአውስትራሊያ መንግስታዊው ምክር ቤት ለምን ናቲ ማንን እንደመረጠው በሰጠው ገለፃ ላይ ‹‹በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ውስጥ ለአስራ ስምንት አመታት የቆየና ሶስት አልበሞችን ያወጣ ከመሆኑም በላይ በተለያዩ የአለም ክፍሎች እየተዘዋወረ ስራዎቹን ያቀረበ ነው፡፡ ናቲ በሙያው ውስጥ ሊዘልቅ የቻለው በአገር ውስጥ ሆነ በዲያስፖራው ሙዚቃዎቹ ተፅእኖ ፈጣሪ በመሆናቸው ነው›› ብሏል፡፡

ይህንን የፌሎውሺፕ እድል በማግኘቱ ናቲ ማን ከታዋቂ የአውስትራሊያ ድምፃዊያን ጋር አብሮ አልበም የሚያወጣ ሲሆን የመድረክ ስራም እንደሚያቀርብ ከምክር ቤቱ መግለጫ ላይ ተመልክተናል፡፡
Via፦ zehabesha

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቱርክ ገቡጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው በሦስተኛው የቱርክ አፍሪካ አጋርነት ጉባኤ ለመሳተፍ ቱርክ፣ ኢስታንቡል ገብተዋል።ጠቅላይ ሚኒስ...
17/12/2021

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቱርክ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው በሦስተኛው የቱርክ አፍሪካ አጋርነት ጉባኤ ለመሳተፍ ቱርክ፣ ኢስታንቡል ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢስታንቡል ሲደርሱ የሀገሪቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና በቱርክ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

ፔጁን ላይክ ያድርጉ 👍💚💛❤️like Page 👍👍💚💛❤️
16/12/2021

ፔጁን ላይክ ያድርጉ 👍
💚💛❤️
like Page 👍👍
💚💛❤️

በደብረታቦር ከተማ የክላሽንኮቭ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች*****************በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የክላሽንኮቨ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በ...
15/12/2021

በደብረታቦር ከተማ የክላሽንኮቭ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች
*****************

በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የክላሽንኮቨ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ያለው ዘለቀ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ግለሰቧ ትናንት ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ስር የዋለችው ከህብረተሰቡ ጥቆማ የደረሰው ፖሊስ በመኖሪያ ቤቷ ባደረገው ፍተሻ የክላሽንኮቭ ጥይት ተከማችቶ በማግኘቱ ነው።

ተጠርጣሪዋ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተደረገባት መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝም ክትትል እየተደረገ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል።

ህብረተሰቡ አካባቢውን ከህገ ወጥ ተግባራትና ሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

ስለ ቶማስ ጀጃው ሞላ    በግንባር በአካል በመገኘት በፋኖ አስተባባሪነት ያለማቋረጥ በትግሉ እየተሳተፉ ካሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አንዱ Thomas Jejaw Molla ነው። ይህን ወ...
15/12/2021

ስለ ቶማስ ጀጃው ሞላ

በግንባር በአካል በመገኘት በፋኖ አስተባባሪነት ያለማቋረጥ በትግሉ እየተሳተፉ ካሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አንዱ Thomas Jejaw Molla ነው። ይህን ወጣት ያወኩት እዚሁ በሶሻል ሚዲያ ሰፈር ነው፤ ከዚህ የዘለለ ትውውቅ የለንም። ቶማስ ስለራሱ ብዙ እንዲነገርለት አይፈልግም...በጣም ትሁት ወጣት ነው። በተደጋጋሚ ከሚፅፋቸው ፅሁፎቹም እንደተረዳሁት ቶማስ በተናጠላዊ ሳይሆን በቡድን ሥራና ውጤት ከሚያምኑት ወገን ነው። ሆኖም በሚዛናዊና በሳል እንዲሁም ስሜት ባልጠለዛቸው ሀገር-ተኮር ፅሁፎቹ የተነሳ ዛሬ በይፋ በገፄ ያደረኩትን ቀደም ሲል በውስጥ ገፅ ከማመስገን ታቅቤ አላውቅም።

ታዲያ ከዕለታት አንድ ቀን ቶማስን በውስጥ መስመር አግኝቼው...አንተ ግንባር እየተፋለምክ ነውና ባለትዳር ከሆንክ ለቤተሰብህ እንኳን የአቅሜን ያህል ድጋፍ እንዳደርግ የባንክ ቁጥራቸውን ላክልኝ... አልኩት። ቶማስ "እኔ ገና ትዳር ያልመሠረትኩ ላጤ ነኝና ምንም አያስፈልገኝም" በማለት መለሰልኝ። በመቀጠልም...እሺ አንዴ አስቤበታለሁና አንተ ግንባር ስለሆንክ ለወላጆችህ እንኳን የተወሰነ ነገር ላድርግ... አልኩት። የቶማስ ምላሹ አሁንም "ወላጆቼ ለራሳቸው የሚበቃ ገቢ ስላላቸው ዕርዳታ አያስፈልገቸውም" በማለት መለሰልኝ። በመጨረሻም ጫናዬ ሲበዛ ለራሱም ለቤተሰቡም የነፈገውን ድጋፍ አጠገቡ ላሉ ፋኖዎች ለሎጂስቲክ አላማ እንዲውል ወስኖ በሐሳቡ ተስማማን።

ከደቂቃዎች በፊት ከቶማስ ጋር ከግንባር ሆኖ በውስጥ መስመር እያወራን እያለ "ለመስመር ሥራ እየወጣሁኝ ነው፣ ለማንኛውም እንበርታ" በሚል በተለመደው የማበረታቻ መልዕክቱ ንግግራችንን አቋርጦ ወደ መስክ ወጥቷል።

እስቲ እኔም መልዕክቴን ከመቋጨቴ በፊት ቶማስ ዛሬ ከግንባር ሆኖ ለኢትዮጵያውያንና ለመንግስት በገፁ ላይ ያስተላለፈውን መልዕክት ላካፍላችሁ፦

"ብዙዎች ለማንነታቸውና ለነፃነታቸው መከበር መተኪያ የሌለውን ወድ ሕይወታቸውን በሁሉም የጦር ግንባሮች እየከፈሉ ባሉበት ሁኔታ ጦርነቱን እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ንግድ ላይ የተሰማሩ የጦር መሳሪያዎችን ከወገን ጦር በተለያዬ መንገድ በመግዛት ወይም እንደሚዋጋ ሰው በልመና በመቀበል ለጠላት(ለሕወሓትና ለኦነግ ሸኔ) በከፍተኛ ገንዘብ በመሸጥ የሚያስታጥቁ፤ እንዋጋለን እያሉ ከግንባር የሚቀበሉትን የጥይት ፍሬን ለጠላት ጭምር አሳልፈው በከፍተኛ ገንዘብ የሚሸጡና በጥይት እጥረት የተነሳ ግን መልሰው መዋጋት እንዳልቻሉ መንግስትን የሚያማርሩ ነውረኞችና ሰነፎች፤ በእየግሮሰሪ አረቂ ቤቱ በየጫት መደቡ ተቀምጠው ግንባር ባለ ፋኖ ሰራዊት ወይም ጀግና ሰው ስም ሀብት ለመፍጠር ለማጭበርበር የሚዳክሩ፤ የወገን ጥምር ጦር በተቆጣጠረባቸው አካባቢዎች የመንግስታዊ መዋቅሩን ድክመት ተመልክተው ዘረፋ የፈፀሙና የሚፈፅሙ በፋኖ ስም የተሰማሩ የግል ጥቅም አራማጅ ወንጀለኞች ያድቡ ዘንድ የግድ በሚመለከተው አካል በትኩረት ሊሰራ ይገባል።

በየትኛውም ግንባር የተሰማራ ወይም ለመዝመት ፍላጎት ያለው ማንኛውም አካል ዲሲፕሊንድ ሊሆን ይገባል። ማንም ለንግድ ወይም በዘፈቀደ እንደልቡ በራሱ ስሜት ግንባር አካባቢ ሊንቀሳቀስ አይገባም። የወገንን ጦር በተቆርቋሪነት ስም ግንባር ድረስ ተገኝቶ በሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በተለያየ መንገድ መሳሪያና ጥይት በመግዛት ትጥቅ የሚያስፈታ ሰራዊቱን የሚሸረሽርና የሚበትን የጠላት ተልዕኮ በተሸከመ አካል ላይ መንግስት እስካሁን የማያዳግም እርምጃ አለመውሰዱ የሚያሳፍር ቢሆንም አሁንም አልረፈደም። አንዳንድ የደህነት ባለሙያ ነን የሚሉ ሕገ-ውጥ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ለእነሱና ለሌሎቹም ሽፋን የሚሰጡ ባለስልጣናት ከድርጊታቸው ይታረሙ ዘንድ ሌሎችም ፈለጋቸውን እንዳይከተሉ ከታሰበ መቀጣጫ ሊሆኑም ይገባል። ማንም በዚህ የሕልውና ጦርነት በግንባር እየተገኘም ሆነ ከተማ ላይ ሆኖ በወንድሞቻችን መስዋዕትነት ገንዘብ ሊነግድ አይገባም። የሐገር ክህደት ወንጀልም ነው።

ማንነታቸውንና ነፃነታቸውን ለማስከበር ስለ እናት ኢትዮጵያ ሲሉ በክብር የወደቁትን የጀግኖቻችንን ደም እንደጠጣችሁት እንቆጥረዋለን። ጦርነቱን በሚመራው አካል ስር ሆኖ ወደግንባር የማይሰማራ ግለሰብም ሆነ ቡድን ለጠላት ጉልበት ሊፈጥር የሚችል የጥፋት ሃይል ነው። በተቆርቋሪነት ስም ወደግንባር ስንቅ ይዘው በመዝለቅ የወገንን ጦር አሰላለፍ ሁኔታ ለጠላት አሳልፈው የሚሰጡ የአምቡላንስ ሹፌሮችም ሆኑ ሎጅስቲክ የጫኑ ሹፌሮች ላይም ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል። ጦርነቱ እስካልተጠናቀቀ ድረስ በቸልታ ማለፍ አይገባም።
በዚህ የሕልውና ጦርነት የተጧጧፈ ንግድ ውስጥ ያላችሁ ሰዎች የወንድሞቻችንን ደምና አጥንት ሸጣችሁ ለመክበርና ለመብላት እንዳሰባችሁ ሳይሆን እንዳደረጋችሁት ልትቆጥሩት ይገባል። ደግሞም ነው። እንዴት የወንድማችሁ ስጋ ተላምጦና ጥሟችሁ ሊበላችሁ ይችላል? ደሙስ እንዴት ከጉሮሯችሁ ሊወርድላችሁ ይቻላችኋል? ከባድ ነው እኮ። እርም ነው።

ገንዘብ ለትራንስፖርት ለምግብ ለካርድ ለውጊያ ሲገባ መሳሪያ ጥይት መጠየቅና ለማግኘት መሯሯጥ የወግ ነው። ተገቢም ነው። ከዚህ ውጭ ላለ ነገር በሕልውና ጦርነቱ መነገድ ግን ከባድ ሀጢያት አረመኔነትም ነው። ስንት ጀግኖች አንድያ ነብሳቸውን በሁሉም የጦር ግንባር እየሰጡ ንግድ ላይ መሰማራትና ሀብት ለመፍጠሪያ ማሰብ ይቅርታ የማያሰጥ ወንጀል ነው። ከዚህ በላይ አሳፋሪና ጠላትነት ፈፅሞ ሊኖር አይችልም። እናም በዚህ የጥፋት የነውረኝነት እንቅስቃሴ ላይ ያለን ሰዎች ወደቀልባችን እንመለስ። ስንት አመትስ እንዳልተኖረ ነው። ቢበዛ 80 ነው እሱም ለተመረጡት ነው እንዲል መዝሙረኛው ዳዊት።

እንድታሰምሩበትና እንድታውቁት የምንፈልገው ጉዳይ ቢኖር መንግስት አስቸኳይ ኮማንድ ፖስቱ የተለመደውን የጥፋት አላማን እያየና እየሰማ ባላየና ባልሰማ ቢያልፋችሁ እና የለመዳችሁትን አፍራሽ የጥፋት አላማን በነውራችሁ አጊጣችሁ እናስቀጥላለን የምትሉ ከሆነ እኛ ባላየና ባልሰማ ልናልፋችሁ በሁሉም ግንባሮች እንዲሁም አጠገባችንም በክብር የወደቁ የፈሰሰው የጀግኖች ወንድሞቻችን ደም ይፋረደናልና ፈፅሞ አንችልም።ማን ምን መሆኑንና እየሰራ እንደሚገኝ ስለጥፋት አላማችሁ አስረጅ የሆነ ከበቂ በላይ ቴትራ ባይት መረጃ አለን።

ማንንም ለከት የለሽ የደም ነጋዴ አሳማና የትህነግ ጉዳይ አስፈፃሚን አካል መንግስት ያለምህረት የማያዳግም እርምጃ ሊወስድበትና ሕግ ሊያስከብር እንደሚገባው ደጋግመን እናሳስባለን።ግዴታውም ነው። ከሕልውና በላይ ምንስ ነገር ኖሮ ነው? ለእኛ አንዳችስ እንኳን‼️

እኛ የእነዛ ሀገር የገነቡ አኩሪ ታሪክ ሰሪ አይበገሬ አባቶቻችን ልጆች እንጅ የሀገር ሻጮችና አገር አፍራሽ ባንዳና የባንዳ ልጆች አይደለንምና አማራን አንገት ለማስደፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚሰሩ የጥፋት አካላት ጋር ሕብረት ሊኖረን አይገባም‼️

ኢትዮጵያ ማህፀነ ለምለም የእልፍ ጀግኖች መፍለቂ
Getahun heramo

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fact News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share