Momentum Media Production

Momentum Media Production Ethiopia

https://www.facebook.com/share/p/18hZcTKFtu/?mibextid=wwXIfr
28/05/2026

https://www.facebook.com/share/p/18hZcTKFtu/?mibextid=wwXIfr

ግንቦት 19/2018

በደርግ ዘመነ መንግሥት የተሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በመምራት የሚታወቁት አቶ ካሳ ገብሬ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

አቶ ካሳ በ92 ዓመት እድሜያቸው ይኖሩበት በነበረው አሜሪካ ሀገር ህይወታቸው ያለፈው በዛሬው እለት ነው።

ኢንጂነር ካሳ ገብሬ ከኢትዮጵያ ህንፃ ኮሌጅ በሲቪል ምህንድስና ካናዳ ሀገር በሚገኘው የብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የአንድ ዓመት የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን መከታተላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

በትምህርት ሚኒስቴር በዋና መሃንዲስነት፣ በቤቶችና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትርነት፣ በኤርትራ የጠቅላይ ግዛቱ ዋና መሃንዲስ፣ በሕንጻ ኮንስትራክሽን ሚኒስትርነት እና በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነቶች እስከ ደርግ ስርዓት ማብቃት ድርስ አገልግለዋል።

ኢንጂነር ካሳ በደርግ ስርዓት ወቅት የተሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችንም መርተዋል።

በሶማሌ ወረራ ጦርነት ወቅት ህዝባዊ ሠራዊት የሰለጠንበትን የታጠቅ ጦር ሜዳ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማዘጋጀታቸው ከሚጠቀስላቸው ስራዎቻቸው መከከል ይገኝበታል።

የጀግኖችና ህፃናት አምባ ምስረታዎች ወቅት የግንባታ ዘርፉን መርተዋል።

የጣና በለስ ግድብ፣ የቀይ መስቀል ሕንጻ፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል፣ ፍልውሃ ሕንጻዎች፣ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን፣ በርካታ የከተማ ፕላኖችና ድልድዮች ከታላላቅ ሥራዎቻቸው መካከል ይጠቀሳሉ።

በዚህም ጉልህ አስተዋጿቸው ለዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ከመሠረት ጣዮች መካከል አንዱ ተደርገውም ይነሳሉ።

አገሪቷ ከፍተኛ የድርቅ አደጋ ውስጥ በገባችበት ወቅትም ዜጎችን ድርቅ ካለበት ወደ ድርቅ ወደሌለበት አካባቢ በማዛወር ከእልቂትና ከረሃብ አደጋ በመታደግ ትልቅ ሰብዓዊ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውምን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ኢንጂነር ካሳ በኢህአዴግ መንግሥት ዘመን 12 ዓመት ከ3 ወር ታስረዋል።

ከእስር ከተፈቱ በኋላ አብዛኛውን ኑሯቸውን ያደረጉት በአሜሪካ ሀገር ሲሆን መጽሐፍ ጽፈው አጠናቅቀው፣ ግን ለሕትመት ሳይበቃ አረፈዋል።

አቶ ካሳ ገብሬ የሁለት ወንዶች እና የሁለት ሴቶች ልጆች አባትም ነበሩ።

በ92 ዓመት እድሜያቸው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ኢንጂነር ካሳ ገብሬ የቀብር ስነስርዓታቸው በአሜሪካን ሀገር ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል፣ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓም፣ በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ በ3:30 ሰዓት የሚፈፀም ሲሆን በአዲስ አበባ የመታሰቢያ መርሃግብር በቀጣይ ቀናት ይደረግላቸዋል ተብሏል።

https://www.facebook.com/share/p/18aH87Ptie/?mibextid=wwXIfr
07/04/2026

https://www.facebook.com/share/p/18aH87Ptie/?mibextid=wwXIfr

አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አምባሳደር ቆንጂት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በ1950ዎቹ በለጋ እድሜያቸው ተቀላቅለው ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት አገልግለዋል።

አምባሳደር ቆንጂት ከዮዲት እምሩ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደርም ናቸው።

አምባሳደሯ በኦቶዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭና ቬይና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን÷ በአፍሪካ ሕብረትና በተባባሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ መልዕክተኛ በመሆንም ሰርተዋል።

ከሰኔ 2009 እስከ መስከረም 2011 ዓ.ም ደግሞ ኢጋድ በመራው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይ ልዩ አማካሪ ሆነው ማገልገላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

ሚኒስቴሩ በአምባሳደር ቆንጂት ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መጽናናትን ተመኝቷል።

11/02/2026

በታላቅ ክብር እና ሀዘን የሚታወስ፦ የአቶ አማን ፍስሀፅዮን የህይወት ጉዞ

የብዙዎች ተስፋ፣ የችግረኞች ደራሽ፦ በሚዲያ ጥበባቸው የሰውነትን ዋጋ ያስመሰከሩት ባለውለታ

የኢትዮጵያ ሚዲያ ታሪክ ሲነሳ ስማቸው ከፊት መስመር የሚጠቀሰው ታላቁ ባለራዕይ አቶ አማን ፍስሀፅዮን ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ፣ መላው የኢትዮጵያ የብሮድካስት ኢንዱስትሪ እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በጥልቅ ሀዘን ላይ ይገኛሉ።

አቶ አማን ለኢትዮጵያ ሚዲያ ዕድገት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከግል ስኬት ባለፈ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ነበር።

የኢቢኤስ (EBS) መስራችና መሪ አቶ አማን እ.ኤ.አ በ2008 EBS TVን ሲመሰርቱ ዋነኛ ዓላማቸው በውጭ ሀገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ (Diaspora) ከሀገሩ ባህል፣ ቋንቋ እና ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በቅርበት እንዲገናኝ ማድረግ ነበር።

ዛሬ ኢቢኤስ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾች ያሉት፣ ለጥበብ እና ለባህል ትልቅ ስፍራ የሚሰጥ ግዙፍ ተቋም ሆኗል።

አቶ አማን የኢቢኤስ መሪ ብቻ ሳይሆኑ፣ ለመላው የኢትዮጵያ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች መብትና ዕድገት የቆሙ ታላቅ ሰው ነበሩ፦

* የኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማህበር (AEB) መስራችና ሰብሳቢ፦ የግል የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ተደራጅተው መብታቸውን እንዲያስከብሩ እና በጋራ እንዲያድጉ ትልቅ ስራ ሰርተዋል።

* የኢትዮሳት (Ethiosat) ጠንሳሽ የኢትዮጵያ ቻናሎች ከሌሎች ሳተላይቶች ወጥተው በራሳቸው የሳተላይት ምህዋር (NSS-12) እንዲሰባሰቡ በማድረግ፣ የውጭ ምንዛሪ ለሀገር እንዲድን እና ጥራት ያለው ስርጭት ለህዝብ እንዲደርስ አድርገዋል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት እውቅና የተሰጣቸው አቶ አማን፣ የሚዲያ ስራን ከንግድ ስኬት ጋር በማጣመር በመቶዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል።

በተለይም ዘመናዊ የቶክ ሾው (Talk Shows) እና የመዝናኛ ፕሮግራሞች በኢትዮጵያ እንዲለመዱ መንገዱን የቀደዱ ቀዳሚ ሰው ናቸው።

ከሚዲያ ስራቸው ባሻገር፣ አቶ አማን ለብዙ አቅመ ደካማ ኢትዮጵያውያን የደረሱ፣ በችግር ውስጥ ያሉትን የረዱ እና ለሰው አዛኝ የነበሩ ደግ ሰው ነበሩ። በዝግጅቶቻቸውም ሆነ በግል ህይወታቸው የብዙዎችን ህይወት በበጎ ተፅዕኖ ቀይረዋል።

የአቶ አማን ህልፈት ለአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ትልቅ ኪሳራ ነው። ሆኖም ግን፣ የፈጠሩት ተቋም፣ የሰሩት በጎ ስራ እና ያሳዩት የጽናት መንገድ ለብዙዎች አርአያ ሆኖ ይኖራል።

በድጋሚ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለቅርብ ወዳጆቻቸው እና ለመላው የኢቢኤስ ሰራተኞች መጽናናትን እንመኛለን።
ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን!

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

https://youtu.be/YHpqrJC5ATQ?si=noTxd4zQtWhBf4y4
16/01/2026

https://youtu.be/YHpqrJC5ATQ?si=noTxd4zQtWhBf4y4

አዋዜን ሰብስክራይብ በማድረግ አስገራሚ፣ አዝናኝ፣ አስተማሪና አነጋገሪ የሆኑ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና አለም አቀፍ • ትንታኔዎችን ወደ እናንተ ያቀርባል ፡፡

10/11/2025

ዕውቁ የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ዕውቁ የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ በ87 ዓመት ዕድሜ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ዛሬ እሑድ ጥቅምት 30/2018 ነው።

በኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት ጉልሕ አሻራ ማሳረፍ የቻሉት ፕሮፌሰሩ በርካታ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አቅርበዋል። ከሥራዎቻቸው መካከል የኢትዮጵያ ረጅም የሕዝብና የመንግሥት ታሪክ እና የኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ መሠረቶችና መሣሪያዎች ተጠቃሽ ናቸው።

ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ የተወለዱት በቀድሞው ከንባታና ሐዲያ አውራጃ በኩፋላ ቀበሌ ግንቦት 12/1930 ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቢቾ ሆሣዕና ሚሽን፣ በመንግሥት ትምህርት ቤት እንዲሁም ኋላ ላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አዳማ በሚገኘው በዐፄ ገላውዴዎስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረዋል።

ከዚያም መዳረሻቸውን አሜሪካ በማድረግ በኮሙኒቲ ኮሌጅ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለው በኀብረተሰብ ታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪ አጠናቀዋል። ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ታሪክ ጥናት ሁለተኛ ዲግሪ፣ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካና በአውሮፖ ታሪክና በፍልስፍና ደግሞ የዶክትሬት ዲግሪ ወስደዋል።

ዶክትሬታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸው ለሁለት ዓመታት በቨርጂኒያ ዩንየን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አስተምረዋል። ፕሮፌሰር ላጲሶ ድሌቦ የኢትዮጵያ ታሪክ የእስልምናው፣ የክርስትናው እና የሌሎች ሃይማኖቶች እንዲሁም የበርካታ ቋንቋዎች እና ሕዝቦች መስተጋብር ነው በሚለው ሙግታቸው ይታወሳሉ። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
!

ከጥቂት አመታት በፊት የፊልም ፖሊሲው ከመውጣቱ በፊት የኢትዮጵያ ፊልም ፕሮውዲሰር አሶሶሽን መሪዎች ቢኒ  ይድኔ  አርማ  ኤርሚ  እና እኔ በመሆን በመኖሪያ በቤታቸው በመገኘት ብዙ መልክም እ...
17/08/2025

ከጥቂት አመታት በፊት የፊልም ፖሊሲው ከመውጣቱ በፊት የኢትዮጵያ ፊልም ፕሮውዲሰር አሶሶሽን መሪዎች ቢኒ ይድኔ አርማ ኤርሚ እና እኔ በመሆን በመኖሪያ በቤታቸው በመገኘት ብዙ መልክም እና ቁብ ነገሮችን ተጨዋውተን እንደነበር የቅርብ ትዝታዮ ነው::

በጊዜውም ብዙ ጠቃሚ ምክሮችን ስለዘርፉ እና ለኛ እንዳካፈሉን ሁላችንም አንዘነጋም::ጋሽ ደቤ በጥበቡ በርካታ ሥራዎችን የሠራ በዘርፍ እንቱታን ካተረፉ ስመ ጥር እንጋፋ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች ውስጥ ከግንባር ቀደሞቹ ውስጥ የሚጠቀስ ነው :: ለሀገርህ ልህዝብህ ላደረከው እስትዋፆ ውለታ ትልቅ ምስጋናና አክብሮት አለኝ በሰራሃቸው ሥራዎች ባበርከትከው አስተዋፆ ሁሌም ስታወስ ትኖራለህ ትውልድ ያልፋል ህዝብ ይቀጥላል:: " አሸብርቆ ደምቆ እንደ ፀሐይ......" RIP ............ደበበ እሸቱ::

አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት ደበበ እሸቱ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

አርቲስት ደበበ እሸቱ በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን÷ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም እና በጋዜጠኝነት ሙያ በርካታ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አቅርቧል፡፡

ተዋናይ፣ ኮሜዲያን እና አዘጋጅ ሆኖ ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አርቲስቱ ÷ በቴአትር መድረኮች በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሥራዎችን በማቅረብ ይታወቃል፡፡

አርቲስት ደበበ በሀገር ፍቅርና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (በአሁኑ ብሔራዊ ቴአትር) መድረክ ላይ ለበርካታ ዓመታት በተዋናይነትና በአዘጋጅነት አገልግሏል።

አርቲስት ደበበ መጀመሪያ በቴአትር መድረክ የታየው በመንግስቱ ለማ ያላቻ ጋብቻ ሲሆን÷ በመቀጠልም በሬዲዮ እና ቴሌቪዥን የተለያዩ ሥራዎችን አቅርቧል፡፡

አርቲስቱ ከተሳተፈባቸው ሥራዎች መካከል ያላቻ ጋብቻ፣ ሮሚዮና ዡልየት፣ ጠልፎ በኪሴ፣ ዳንዴው ጨቡዴ ፣ዘ ጌም ኦፍ ቼዝ፣ ኦቴሎ፣ አንድ ዓመት ከአንድ ቀን፣ እናት ዓለም ጠኑ፣ በቀይካባ ስውር ደባ፣ የአዛውንቶች ክበብ፣ የወፍ ጎጆ ፣ የቬኒሱ ነጋዴ ፣ ማዕበል እና ሌሎች ይገኙበታል፡፡

በተለያዩ ታሪካዊና አዝናኝ ፊልሞች እንዲሁም የቴአትር ሥራዎች አድናቆት የተቸረው አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ÷ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የክብር ዶክትሬት ተሰጥቶታል፡፡

አርቲስቱ ሀገር ችግር ውስጥ በምትሆንበት ጊዜ ከፊት በመቆም በርካታ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን ÷ በበጎ ፈቃድ ሥራዎችም ግንባር ቀደም ነበር፡፡

በሌላ በኩል አርቲስት ደበበ እሸቱ በ1995 ዓ.ም በሃገራዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ የምክር ቤት አባል እስከመሆን ደርሷል፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እና ለመላው አድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።

17/09/2024

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በአደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

የፕሮፌሰር በየነን ሕልፈተ-ሕወት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

በአስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክትም÷ በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ ብለዋል።

ረዘም ላለ ጊዜ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ እመኛለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)።

https://www.facebook.com/share/p/613UdgD4Uwa7qL1n/?mibextid=WC7FNe
03/09/2024

https://www.facebook.com/share/p/613UdgD4Uwa7qL1n/?mibextid=WC7FNe

ደራሲ እና ኢንጂነር ታደለ ብጡል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
*********

ደራሲ እና ኢንጂነር ታደለ ብጡል ክብረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ኢንጂነር ታደለ ብጡል የባንክ ባለሙያ፣ ሲቪል መሀንዲስ እና ደራሲ ናቸው።

ማራዥት እና ሦስትዮሽ የተሰኙ የግጥም መድብሎች እንዲሁም የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል፣ የሀኪም ወርቅነህ እሸቴ፣ የአፄ ቴዎድሮስ እና የልዑል አለማሁ ቴዎድሮስን ግለ ታሪኮች ፅፈዋል። የአማርኛ የምልክት ቋንቋ መዝገበ ቃላትንም አዘጋጅተዋል።

ደራሲ እና ኢንጂነር ታደለ ብጡል በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ በመሳተፍም ይታወቃሉ። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የማታ ትምህርት ያስጀመሩ ናቸው። በታዋቂው አርበኛ የተሰየመውን ወንዲራድ ት/ቤትን ከሌሎች ጋር በመሆን አቋቁመዋል። የአክሱም ሀውልት ብሄራዊ አስመላሽ ኮሚቴ አባልም ነበሩ።

የተለያዩ ባህላዊ እና ትውፊታዊ ቅርሶችን ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት በራሳቸው ወጪ ገዝተው በመሰብሰብ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተለያዩ ሙዚየሞች በመለገስ ታሪካዊ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

የበጎ ሰው ተሸላሚው ኢንጂነር ታደለ ብጡል ክብረት በ97 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

Address

Addis Ababa
70028

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Momentum Media Production posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Momentum Media Production:

Share