04/10/2025
6
የዘመናችን ጥበበኛ ጊታሪስት ፣ኪቦርዲስት የሙዚቃ አቀናባሪ የዜማ እና ግጥም ደራሲ፣ፕሮዲዩሰር ሁለገቡ ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ካረፈ እነሆ መስከረም 24/2017 ስድስት አመት ይሆነዋል ።
የኤልያስ መልካ አድናቂዎች ህብረት የኤልያስን 6ኛ አመት በማስመልከት ልዩ የመታሰቢያ ፕርግራም አዘጋጅተዋል በሚከተሉት ክንዋኔዎች የምንዘክረው ይሆናል:-
- ቅዳሜ መስከረም 24 ጠዋት 4 ሰአት ዊንጌት አካባቢ በሚገኘው በጴጥሮስ ወጳውሎስ አበባ በማኖር እና ሻማ በማብራት:
- እሁድ ምስከረም 25 ከአዲሱ ሚካኤል ቤ/ክ ፊትለፊት ገነት ህንጻ አጠገብ በሚገኘው በእማማ ዝናሽ በጎ አድራጎት ማዕከል ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር ምሳ በመብላት የሚያሳልፉ መሆኑን ተናግረዋል በዚህ የመታሰቢያ ዝግጅት እንድትታደሙ እየጋበዝን በእለቱ ወደ ማዕከሉ ሲመጡ ለአረጋውያን ይጠቅማል የምትሉትን የንፅህና መጠበቂያዎች አልባሳት
#ጫማ
#ዱቄት
#ዘይት
የመሳሰሉትን ይዘው በመምጣት አጋርነትዎን ያሳዩ ሲሉ እንግዲህ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።