GMN News World

GMN News World Find the latest breaking news and information on the top stories, weather, business, entertainment, politics, and more, from GMN Ethiopia English service.

21/07/2024
ለአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች የተላለፈ ጥሪየጭቆና ቀንበር የሆነውን አዲሱን ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እንዲሁም የመንግስትን ፖለቲካዊ የዋና ከተማ ውሳኔ በመቃወም የጋሞ ህዝብ የሚያደርገውን ተቃውሞ...
12/08/2023

ለአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች የተላለፈ ጥሪ

የጭቆና ቀንበር የሆነውን አዲሱን ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እንዲሁም የመንግስትን ፖለቲካዊ የዋና ከተማ ውሳኔ በመቃወም የጋሞ ህዝብ የሚያደርገውን ተቃውሞ አጠናክሮ በመቀጠል ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የተለያዩ ህዝባዊ የእምቢተኝነት ተግባራት ይከናወናሉ።

የከምባታ ህዝብ የተቃውሞ ሰልፍ ፍቃድ አገኘበመጪው ነሀሴ 8 በዱራሜ ከተማ ለሚካሄደው ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ መንግስት ፍቃድ መስጠቱ ታወቀ። የከምባታ ህዝብ በቅርቡ ይፋ በተደረገው የክላስተር ...
11/08/2023

የከምባታ ህዝብ የተቃውሞ ሰልፍ ፍቃድ አገኘ

በመጪው ነሀሴ 8 በዱራሜ ከተማ ለሚካሄደው ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ መንግስት ፍቃድ መስጠቱ ታወቀ። የከምባታ ህዝብ በቅርቡ ይፋ በተደረገው የክላስተር አደረጃጀት ቅሬታውን ሲያቀርብ መምጣቱ ይታወቃል። በመሆኑም በዕለቱ ከመላው ከምባታ የተወጣጣ የህብረተሰብ ክፍል የተቃውሞ ድምፁን በመንግሥት ላይ እንደሚያሰማ ይጠበቃል።

ትላንት በአርባምንጭ ሊደረግ የታቀደውን ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ መከላከያ ሰራዊቱ እና የደቡብ ልዩ ሀይል ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት በሀይል እንዳስቆሙት ይታወሳል። ቢሆንም ግን መላው የጋሞ ህዝብ የሚያደርገውን ተቃውሞ ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሏል።

ነገ በአርባምንጭ ከተማ ለሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል። ሰልፉ ሠላማዊ ሆኖ በተሳካ መልኩ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል። ጋሞ...
09/08/2023

ነገ በአርባምንጭ ከተማ ለሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል። ሰልፉ ሠላማዊ ሆኖ በተሳካ መልኩ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል። ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የጠራው ይህ የተቃውሞ ሰልፍ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን የአካባቢው ባለሥልጣናት ፍቃድ ስለመስጠታቸው የተባለ ነገር የለም። የሰልፉን ቆይታ በቀጥታ ከስፍራው የምናስተላልፍ መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን።

ነገ በአርባምንጭ ከተማ የአደባባይ ተቃውሞ ይካሄዳል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ከተማን ለመምረጥ የተላለፈውን  ፖለቲካዊ ውሳኔ በመቃወም የአርባምንጭ እና የአጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪዎች የሚሳ...
09/08/2023

ነገ በአርባምንጭ ከተማ የአደባባይ ተቃውሞ ይካሄዳል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ከተማን ለመምረጥ የተላለፈውን ፖለቲካዊ ውሳኔ በመቃወም የአርባምንጭ እና የአጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪዎች የሚሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ በከተማዋ እንደሚካሄድ ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታውቋል። ነገ ሀሙስ ከጠዋት ጀምሮ በሚካሄደው ሰልፍ ላይ መላው የከተማዋ ነዋሪ እንዲሳተፍ ጋዴፓ ጥሪ አቅርቧል።

በመላው ጋሞ ዞን ዛሬም ለ3ኛ ቀን ተባብሶ የቀጠለው ህዝባዊ ተቃውሞ አርባምንጭ ለደቡብ ኢትዮጵያ ዋና ከተማነት የሚያበቃትን ሙሉ መስፈርት አሟልታ ስትጠባበቅ መንግስት በፖለቲካ ውሳኔ ወላይታ ...
08/08/2023

በመላው ጋሞ ዞን ዛሬም ለ3ኛ ቀን ተባብሶ የቀጠለው ህዝባዊ ተቃውሞ

አርባምንጭ ለደቡብ ኢትዮጵያ ዋና ከተማነት የሚያበቃትን ሙሉ መስፈርት አሟልታ ስትጠባበቅ መንግስት በፖለቲካ ውሳኔ ወላይታ ሶዶ ዋና ከተማ እንድትሆን መምረጡ በመላው ጋሞ ዞን ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞን ተቀስቅሷል። ከነገ በስቲያ ሀሙስ በከተማዋ በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት ህዝባዊ ተቃውሞ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

መንግስት የህዝብን ጥያቄ ተመልክቶ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ህዝባዊ ተቃውሞ እና እምቢተኝነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። ይሄም በሠላም ተምሳሌትነት የምትታወቀውን ከተማ ወደግጭት እንዳያስገባ ተሰግቷል።

አርባምንጭ በህዝባዊ ተቃውሞ እየተናጠች ትገኛለች የከተማዋ ትልቁ ገበያ በሥራ ማቆም አድማ የተዘጋ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ደግሞ ትላልቅ የጎዳና ላይ ትዕይንተ ህዝቦች ይደረጋሉ። ዛሬ በከተማዋ የ...
08/08/2023

አርባምንጭ በህዝባዊ ተቃውሞ እየተናጠች ትገኛለች

የከተማዋ ትልቁ ገበያ በሥራ ማቆም አድማ የተዘጋ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ደግሞ ትላልቅ የጎዳና ላይ ትዕይንተ ህዝቦች ይደረጋሉ። ዛሬ በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች ነዋሪው በየሰፈሩ ጎዳና ላይ ወጥቶ ተቃውሞ እያሰማ ይገኛል። ከነገ በስቲያ ደግሞ መሬት አንቀጥቅጥ ፀረ መንግስት ሰልፍ ይካሄዳል። አርባምንጭ አዲስ የሚመሰረተው ክልል ዋና ከተማ እንደምትሆን ቃል ተገብቶ እያለ አዲስ ውሳኔ ተወስኗል በሚል መላው የጋሞ ህዝብ መንግሥትን እየተቃወመ መሆኑ ይታወቃል።

ታላቅ የሰለማዊ ሰልፍ ጥሪ በአርባ ምንጭ ከተማ===============================የጋሞ ህዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰንና ራስን በራስ የማስተዳደር እንዲሁም የጋሞ ብሔራዊ ክ...
07/08/2023

ታላቅ የሰለማዊ ሰልፍ ጥሪ በአርባ ምንጭ ከተማ
===============================
የጋሞ ህዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰንና ራስን በራስ የማስተዳደር እንዲሁም የጋሞ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የማቋቋም ህገመንግስታዊ ጥያቄ ከቀበሌ ጀምሮ ያሉ የህዝብ ህጋዊ ውክልና በነበራቸው ምክር ቤቶች ጥያቄ ካቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ህጋዊ ምላሽ እንዲሰጥ እየጠየቅን መቆየታችን ይታወቃል።

ሆኖም ብልፅግና መንግሥት የህዝብን ጥያቄ በማፈን እና ህገመንግስቱን በመጣስ የሚነሱ የተቃውሞ ድምፃችንን ችላ በማለት በፓርቲ አቅጣጫ በሚል ህዝበ ውሳኔ አካሒዶ አሁን ላይ በየአካባቢው የፀጥታ ስጋት መንስኤ የሚሆን ውሳኔ አሳልፎ ለትግበራ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በመሆኑም የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ) በቀን 30/11/2015 ዓ.ም 4ኛ ዓመት 3ኛ ዙር ባደረገው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ፓርቲው የአደባባይ ሰለማዊ ሰልፍ እንዲጠራ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የፓርቲው አዲሱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቀን 1/12/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ህዝባዊ ሰለማዊ ሰልፍ በአርባ ምንጭ ከተማ በቀን 4/12/2015 ዓ.ም እዲደረግ በሙሉ ድምፅ ወስኗል። ጉዳዩ የፓርቲ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የጋሞ ህዝብና በጋሞ አካባቢ የሚኖሩ እንዲሁም የጋሞ ህዝብ ወዳጆች የሁላችን ጉዳይ ስለሆነ በዚህ ሳምንት ሐሙስ ዕለት እንዲደረግ ፓርቲው በጠራው ሰለማዊ ሰልፍ ላይ በነቂስ ወጥቶ የተቃውሞ ድምፁን እንዲያሰማ በአክብሮት ያሳውቃል።

የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
አርባምንጭ
ቀን 1 ነሐሴ 2015 ዓ.ም

አርባምንጭ እምቢ በቃኝ ብላለች።በኢትዮጵያ በሠላማዊ ከተማነቷ የምትታወቀው አርባምንጭ ከሰሞኑ መንግስት ያሳለፈውን ፖለቲካዊ ውሳኔ ተከትሎ በተለያዩ መንገዶች ህዝባዊ እምቢተኝነቷን እየገለፀች ...
07/08/2023

አርባምንጭ እምቢ በቃኝ ብላለች።

በኢትዮጵያ በሠላማዊ ከተማነቷ የምትታወቀው አርባምንጭ ከሰሞኑ መንግስት ያሳለፈውን ፖለቲካዊ ውሳኔ ተከትሎ በተለያዩ መንገዶች ህዝባዊ እምቢተኝነቷን እየገለፀች ትገኛለች።

ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የሥር ማቆም አድማ ነው። ዛሬ ሰኞ የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሞ ውሏል።

የመንግሥትን ውሳኔ በመቃወም በጋሞ ዞን የሚደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።
07/08/2023

የመንግሥትን ውሳኔ በመቃወም በጋሞ ዞን የሚደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።

የመንግሥትን ፖለቲካዊ የዋና ከተማ ውሳኔ አንቀበልም፤ ዋና ከተማችን አርባምንጭ ናት፤ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አይወክለንም፤ ለጥያቄያችን መልስ የማይሰጥ ከሆነ መብታችንን ለማስከበር ሁሉንም አማ...
07/08/2023

የመንግሥትን ፖለቲካዊ የዋና ከተማ ውሳኔ አንቀበልም፤ ዋና ከተማችን አርባምንጭ ናት፤ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አይወክለንም፤ ለጥያቄያችን መልስ የማይሰጥ ከሆነ መብታችንን ለማስከበር ሁሉንም አማራጮች እንጠቀማለን የሚሉ መልዕክቶችን ያስተጋቡ ሰልፈኞች በመላው ጋሞ የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛል።

በጋሞ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ እና ቁጣ እየተባባሰ መጥቷል። ዛሬ ለሶስተኛ ቀን እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ አርባምንጭን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎች ህዝቡ በመንግሥት ላይ ቁጣውን እየገለፀ ይገ...
07/08/2023

በጋሞ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ እና ቁጣ እየተባባሰ መጥቷል። ዛሬ ለሶስተኛ ቀን እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ አርባምንጭን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎች ህዝቡ በመንግሥት ላይ ቁጣውን እየገለፀ ይገኛል። ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከመመስረቱ በፊት ቃል የተገባው የአርባምንጭ ዋና ከተማነት ጥያቄ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ ጠይቀዋል።

Address

Akaki Kaliti
Addis Ababa
573

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GMN News World posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share