Hulu Media

Hulu Media Hulu Media is an Ethiopian media and infotainment page. Enjoy your time with Hulu Media!!!!

Hulu Media is an Ethiopian media and infotainment page founded on June 19, 2015. It is one of the few page that provide Ethiopians with access to the information and entertainment.

ሳንጃው ጠብ አይመርጥም!!!
22/08/2020

ሳንጃው ጠብ አይመርጥም!!!

" "ሪቮሉሽኖች የጭካኔን ሸክም አቃለው አያውቁ፣ ግን ወደሌላው ትከሻ ያዛውሩታል። " ~ ጆርጅ በርናንድ ሾውይህ እውነተኛ ቃል ነው። ግን የሰው ልጆች አተኩረው ሊመረምሩትና ሊጠቀሙበት አልቻሉ...
21/08/2020

" "ሪቮሉሽኖች የጭካኔን ሸክም አቃለው አያውቁ፣ ግን ወደሌላው ትከሻ ያዛውሩታል። " ~ ጆርጅ በርናንድ ሾው
ይህ እውነተኛ ቃል ነው። ግን የሰው ልጆች አተኩረው ሊመረምሩትና ሊጠቀሙበት አልቻሉም።
ሰዎች እንደሰዎች ሊያስቡና እንደሰዎች ሊኖሩ የሚችሉበት አንድ ዘዴ መገኘት አለበት። በበኩሌ በመንፈሳዊ አምናለው። በርግጥ የቤተ ከቋንቋ አይደለም። እኔ ከቋንቋ ጉዳይ የለኝም። ቋነቋ ገለባ ነው። እኛ መፈለግ ያለብን በገለባው ውስጥ የሚገኘውን ፍሬ ነው።
እውነተኛ መንፈሳዊ ሪቮሉሽነሪ የናዝሬቱ እየሱስ መሆኑን አውቃለው። እርሱ በባዶ ቋነቋ መጠቀምን አይፈቅድም። እርሱ ስለእውነትና ስለፍትህ ተናገረ። በባዶ ቋነቋ የሚያምኑ ፈሪሳውያን ትምህርቱን ተቃወሙ። ግን ዓለም የርሱን ትምህርት መከተል እስካልቻለች ድረስ ፍትሕ ማግኘት አትችልም። "
ከብርሃኑ ድንቄ ቄሳርና አብዮት መፅሀፍ የተወሰደ

  : የኮሮና ቫይረስ ሲገድል ጥቁር ነጭ አማራ ትግሬ ኦሮሞ ጉራጌ....አይልም። ውድ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በናንተ ብርታት ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ለመርዳት እየተዋጣ ያለው ...
03/04/2020

: የኮሮና ቫይረስ ሲገድል ጥቁር ነጭ አማራ ትግሬ ኦሮሞ ጉራጌ....አይልም።
ውድ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በናንተ ብርታት ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ለመርዳት እየተዋጣ ያለው ገንዘብ $549,077 ደርሷል $750,000 እስኪደርስ እንበርታ! ይህን መጥፎ ግዜ አንድ ላይ በመሆን እናልፈዋለን ለኢትዮጵያ ሀገራችን እና ህዝቦቿ እንደርስላታለን::
ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የበኩሎን አስተዋጽኦ ለሚወዷት ለሀገሮትና ሕዝቦቿ ያበርክቱ!
https://www.gofundme.com/f/EthiopiansAgainstCoronaVirus

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!!

የሐኪም አበበች ሽፈራው የምርምር ውጤትንና በማሕበራዊ ሚዲያዎች የሚሠራጨውን ወሬ በተመለከተበመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡❤️ እንደሚታወቀው በዓለም ላይ የተስፋፋ...
01/04/2020

የሐኪም አበበች ሽፈራው የምርምር ውጤትንና በማሕበራዊ ሚዲያዎች የሚሠራጨውን ወሬ በተመለከተ

በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡

❤️ እንደሚታወቀው በዓለም ላይ የተስፋፋው ገዳይ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) በመላው ዓለም 912,572 ሰዎችን የያዘ ሲሆን 45,541 ሰዎችን ገድሏል። ዓለምን ሁሉ ያስጨነቀ ይህን ወረርሽኝ ለመግታት ሁሉም ሀገራት የራሳቸውን ምርምር እያደረጉ ይገኛሉ።

❤️ ከአፍሪካም በጥንታዊ የሕክምና ዕውቀት ከፍተኛ የታሪክ ደረጃ ያላት ታላቋ ክብርት ሀገራችን ኢትዮጵያ ናት። ቀደምት ኢትዮጵያውያንም በዕፅዋት፣ በእንስሳት፣ በማዕድናት ውጤቶች ሕዝቡን ከማከምና መድኃኒት ከመቀመም ዐልፈው ዓለምን ያስደነቁ በተለይ በጀርመን ተወስደው የሚመረመሩ እነ መጽሐፈ መድኃኒትን፣ መጽሐፈ ዕፀ ደብዳቤ፣ መጽሐፈ አእባንን፣ የማከምያ ጠልሰሞችን መርምረው ጽፈው አልፈዋል። በዋሽንግተን ዲሲ በካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ አሜሪካ እንኳን በዐይኔ ያየኋቸው ወደ 400 የሚጠጉ የመድኃኒት ዝርዝር የያዙ ጥቅሎች ናቸው። እስከ ዶክትሬት ደረጃ እንደሚጠኑም አውቃለሁ።

❤️ ከእኛ ተወስደው ሌላውን ዓለም ሲያበለጽጉ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በዘመናዊ መልኩ እንደነርሱ የራሳችንን ንብረቶችና ዕውቀቶች እንዳንመረምራቸው እንዳናጠናቸው ሆን ተብሎ የተንኮል ደባ በመደረጉ የባህል ሕክምና ዐዋቂዎች ክፉ ስም እንዲሰጣቸው፣ ዕውቀታቸውም እንዳይስፋፋ ሲደረግ ኖሯል። ይኼ የራስን ዕውቀት የማስጣል ሤራ እንደ እኛ ለምሳሌ ቻይናውያን ላይም ቢደርስባቸውም በሀገር ፍቅርና በአመራራቸው ጥንካሬ ፈተናውን ተቋቁመውት የእራሳቸውን የባህል ሕክምናን ከዘመናዊው ጋር አጣምረው ታላቅ ደረጃ ላይ አድርሰውታል። ይልቁንም በዚህ ታላቅ ወረርሽኝ የቻይና የባሕል ሕክምና ጠበብት ከዘመናዊው ጋር ተቀናጅተው ታላቅ ሥራን ለሀገራቸው እያበረከቱ ይገኛሉ።

❤️ በተለያየ ጊዜ ወረርሽኝ ተከሥቶ ሕዝብን በሚያጠቃ ጊዜ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ሕዝቡን ከአደገኞች ቫይረሶች ያክሙ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ይኽን ዕውቀት ጠንቅቀው የሚያውቁት የኢትዮጵያ የሕክምና ሊቃውንት ለእዚህ ገዳይ ቫይረስ የነበረውን ለሀገራችን አበርክተዋል። በዚህም ከፍተኛ ምስጋና ሊቀርብላቸው ይገባል። ሀገር የምትፈልገው የወሬ ኤክስፐርቶችን ሳይሆን ያላቸውን የሚያበረክቱላት ሕዝቡን በችግሩ የሚደርሱለትን ብቻ ነው።

❤️ በዚህ ዙርያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.)፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ቫይረሱ ለማከም የሚያስችል የመድኃኒት ምርምር የመጀመሪያ የቤተ ሙከራ መሠረታዊ የምርምር ሂደትንና ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግን በስኬት እንዳለፈ ገልጸዋል፡፡

❤️ የመጀመሪያ ምርምር ሂደትን በተገቢው መንገድ አልፎ ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻ እና ክሊኒካል ፍተሻ ሥራዎች እንዲሸጋገር መደረጉን ገልጸዋል። ይህም በመንግሥት መደረጉ ታላቅና ሀገርን የሚያኮራ መሆኑን ሳናደንቅ አናልፍም።

❤️ መድኃኒት ተሠርቶ ለሕሙማን እስኪደርስ የግድ የሚያልፍባቸው ዓለም ዐቀፍ ሕጎችን ሊያልፍ ግድ ነውና ሌሎች ተጨማሪ የምርምሩ ሂደት መረጃዎችንም በቀጣይ የሚገለጽ መሆኑን የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፎልናል።

❤️ ይህ እንዲሳካ ሁላችንም መጸለይ፣ በጎ መመኘት ሲገባ አንዳንዶች ግን በዚህ ገዳይ ወረርሽኝ ጊዜ እንኳ የፌስቡክ ሰው ለማብዛት ሲሉ የሐሰት ፌስቡክ ግሩፕ እየከፈቱ ሐኪም አበበች ሽፈራው ያላሉትን እየጻፉ ሰውን እያሳሳቱ መገኘታቸው ለዚህ መሳካት ጊዜያቸውን ዕውቀታቸውን እየሰጡ ያሉትን እያሳዘነ ይገኛል። ይልቁኑ ይህ የሐሰት ወሬ ፈጥራችሁ የምታሠራጩ ወገኖች እባካችሁን ይህ ድርጊታችሁ ተመራማሪዎችን ወደ ኋላ እንዳይጎትታቸው ማሰብ ያስፈልጋል።

❤️ ሐኪም አበበች ሳይሉ በሐሰት የተሠራጩ ብዙ ጉዳዮች ውስጥ ቫይረሱ ወደ ባሕር ውስጥ ከገቡት አጋንንት ካሠጠሟቸው አሣማ ነው ብለዋል የሚልና ሌሎች ውሸቶችን እየፈበረኩ የውሸት ዜና የሚያሠራጩ አሉና ከዚህ የሐሰት ወሬ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

❤️ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ የተሞከረው ሙከራ በሚመለከታቸው አካላትና በሐኪም አበበች ሽፈራው ብቻ በሕጋዊ ሚዲያዎች የሚገለጽ ሲሆን ከዛ ውጪ በየሚዲያው፣ በየፌስቡኩ የሚጻፈው ሁሉ እርሳቸውን የማይወክልና እርሳቸውም ያላሉትና የማያውቁት እንደሆነ ገልጸዋል።

❤️ መድኃኒቱ ተዘጋጅቶ ለአገልግሎት እስኪበቃ ድረስ ግን በሕመሙ የሚጠቁ ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው እንዳያልፍ ከባሕል መድኃኒት ሊቃውንት ጋር ተቀናጅቶ በሀገር ውስጥ በፍጥነት እንዲረዱ እንዲያገግሙ የሚቻልበትን ሁኔታ ግን መንግሥታችን ያስብበታል የሚል እምነት ያለን ሲሆን ሁላችንም ለዚህ መሳካት ልንጸልይበት ይገባል በማለት ጽሑፌን አበቃለሁ።

  : በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 13 ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት በነገው ዕለት ይደረጋል።በተመረጡት መንገዶች ላይ የመከላከያ መድሃኒት ርጭት ወይንም ዲስኢንፌክት ...
28/03/2020

: በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 13 ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት በነገው ዕለት ይደረጋል።

በተመረጡት መንገዶች ላይ የመከላከያ መድሃኒት ርጭት ወይንም ዲስኢንፌክት የማድረግ ስራ የሚከናወን ይሆናል።

በዚህም መሠረት፦

- መስቀል አደባባይ - ቦሌ ፣
- መስቀል አደባባይ - ጦር ሃይሎች ፣
- መስቀል አደባባይ - 6 ኪሎ ፣
- ከመስቀል አደባባይ - ጎተራ - ሳሪስ
- ከመስቀል አደባባይ - መገናኛ ፣
- ከብሄራዊ - ሜክሲኮ፣
- ከሱፐር ማርኬት - ካዛንችስ - ኡራዔል ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - አምባሳደር - መስቀል አደባባይ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - ፓስተር፣
- ከምኒልክ አደባባይ - 4 ኪሎ - መገናኛ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - 6 ኪሎ ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - አውቶብስ ተራ ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - ተክለሃይማኖት
ያሉት መንገዶች የመድሀኒት ርጭት የሚካሄድባቸው ይሆናል።

የፀረ-በሽታ አምጭ ተዋህስ መድሀኒት ርጭት ሚካሄድባቸው መንገዶች 41 ኪሎ ሜትር የሚሽፍኑ ናቸው። በዚህ ምክንያትም የተጥቀሱት መንገዶች ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ለአገልግሎት ዝግ የሚሆኑ ይሆናል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በቤታቸው ሆነው የሚሰሩና ወደ ቢሮ የሚገቡ ሰራተኞችን ለይተው ይፋ እያደረጉ ነው።  ...
24/03/2020

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በቤታቸው ሆነው የሚሰሩና ወደ ቢሮ የሚገቡ ሰራተኞችን ለይተው ይፋ እያደረጉ ነው።

: የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ሚኒስቴሩ በቤታቸው ውስጥ በኢሜል እና በስልክ ስራቸውን ማከናወን የሚችሉ እንዲሁም የሚኒስቴሩን የትራንስፖርት የማይጠቀሙ ሰራተኞች ከቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ወስኗል።

በዚህም መሰረት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ካሉ 377 ሰራተኞች ውስጥ 86 ስራ እንዲገቡ፣ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ካሉት 328 ሰራተኞች መካከል 19 ስራ እንዲገቡ፣ ብሄራዊ ቴአትር ካሉት 307 ሰራተኞች 14 ስራ እንዲገቡ፣ በስፖርት ኮሚሽን ካሉት 218 ሰራተኞች 42 ስራ እንዲገቡ እንዲሁም በሆቴልና ቱሪዝም ድርጅት ካሉት 215 ሰራተኞች 28 ስራ እንዲገቡ የወሰነ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ከቤት ሆነው ስራ እንዲያከናውኑ ተደርጓል ብለዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአጠቃላይ ካሉት ሰራተኞች ውስጥ 86 በመቶው ከቤታቸው፤ ከቀሪው 14 በመቶ ቢሮ ገብተው እንዲሰሩ መወሰኑን የገለፁት ዶክተር ሂሩት፥ እነዚህ ሰራተኞች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ሰርቪስ የሚጠቀሙ ይሆናል ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም በዋናው መስሪያ ቤት ካሉት አጠቃላይ 520 ሰራተኞች 128 ወይም 25 በመቶ ብቻ ቢሮ ገብተው አገልግሎት እንዲሰጡ፤ ቀሪው 75 በመቶ ሰራተኞች ከቤት እንዲሰሩ ውሳኔ አሳልፏል።

አዲስ አበባ ተቀማጭ የሆኑ የዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችና ኤምባሲዎች ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በዲጂታል መልኩ እንዲቀጥል አስፈላጊው መረጃ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

ግብርና ሚኒስቴርም ካሉት ሰራተኞች 80 በመቶ የሚሆኑትን ለ 15 ቀናት በቤታቸው እንዲያርፉ እና እጅግ አስፈላጊ ለሆኑ መንግስታዊ ስራዎች ደግሞ 20 በመቶ የሚሆኑትን ሰራተኞች ለቀጣይ 15 ቀናቶች የሚያሰራ ሲሆን፥ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚከተሉትን ምክረ ሀሳቦች በማኔጅመንት ወስኗል።

በቢሮ እንዲሰሩ የተደረጉ ሰራተኞች 20 በመቶ የሚሆኑት እና ለበርሃ አንበጣ ቁጥጥር መስክ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች እስፈላጊውን የመከላከል ስራ እና የማህበራዊ ርቀትን ጠብቀው እንዲሰሩ በሽታውን ለመከላከል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በቢሮ የተሰራጩ ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስታውቋል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከዋናው ግቢ 617 ሰራተኞች ውስጥ 119 በማስቀረት፣ በተጠሪ ተቋማት የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከ215 ሰራተኞች 62 ሰራተኞች በማስቀረት እንዲሁም ከትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ሙሉ በሙሉ የምርት ተግባሩን እንዲቆም በማድረግ ከ712 ሰራተኞች ውስጥ 15ቱን ሰራተኞች ለተለያዩ ስራዎች እንዲቆዩ በማድረግ በአጠቃላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት አሁን ካላቸው 1 ሺህ 544 ሰራተኞች ውስጥ 196 ማለትም 12 ነጥብ 7% በመቶ ብቻ በማስቀረት 1 ሺህ 348 ማለትም 87 ነጥብ 3 በመቶ ሰራተኞች በቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲሰሩ ውሳኔ አሳልፏል።

የጤና ሚኒስቴርም ነፍሰ ጡር የሆኑ፤ ተላላፊ ያልሆነና የታወቀ በሽታ ህክምና ክትትል እያደረጉ ያሉ ሰራተኞች፣ወደ ጡረታ እድሜ የተጠጉ ሰራተኞችና የተለያዩ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰራተኞች በቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ውሳኔ አሳልፏል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም በዋናው መስሪያ ቤት ለየዕለት የስራ እንቅስቀሴ እጅግ አስፈላጊ ናቸው ተብለው ከተለዩ 15 ሠራተኞች በስተቀር 90 በመቶ

  ቀን ተሌት ተጠንቀቁ እያልን ነው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ሊያዳምጥ አልቻለም አለም ላይ የኮሮና ቫይረስ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ሰዎችን እያጠቃ በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር በየ ሰአ...
23/03/2020

ቀን ተሌት ተጠንቀቁ እያልን ነው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ሊያዳምጥ አልቻለም አለም ላይ የኮሮና ቫይረስ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ሰዎችን እያጠቃ በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር በየ ሰአቱ እየጨመረ ነው:: ትናት አንድ ብለው የጀመሩት የአፍሪካ ሀገሮች ዛሬ የት ደረሱ 👇

በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዘ 402 የሞተ የለም
ግብፅ በቫይረሱ የተያዘ 327 የሞተ 14
ቡርኪ ናፋሶ በባይረሱ የተያዘ 99 የሞተ 4
በቱንዚያ በቫይረሱ የተያዘ 89 የሞተ 3
ሴኔጋል በቫይረሱ የተያዘ 67 የሞተ የለም
ካሜሮን በቫይረሱ የተያዘ 56 የሞተ የለም
ናይጄሪያ በቫይረሱ የተያዘ 36 የሞተ 1
ጋና በቫይረሱ የተያዘ 24 የሞተ 1
በጊኒ በቫይረሱ የተያዘ 20 የሞተ የለም
በሩዋዳ በቫይረሱ የተያዘ 19 የሞተ የለም
በቶጎ በቫይረሱ የተያዘ 18 የሞተ የለም
በኬንያ በቫይረሱ የተያዘ 16 የሞተ የለም
ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዘ 11 የሞተ የለም ወደ ጃፖን የተላኩት ካልተቆጠሩ በኢትዮጵያ 9 ማለት ነው::

በጋቦን በቫይረሱ የተያዘ 5 የሞተ የለም
በዙንቧቤ በቫይረሱ የተያዘ 3 የሞተ የለም
በኮንጎ በቫይረሱ የተያዘ 3 የሞተ የለም
በላይቤሪያ በቫይረሱ የተያዘ 3 የሞተ የለም
በናኒቢያ በቫይረሱ የተያዘ 3 የሞተ የለም
በዛንቢያ በቫይረሱ የተያዘ 3 የሞተ የለም
በጋንቢያ በቫይረሱ የተያዘ 2 የሞተ የለም
በሱዳን በቫይረሱ የተያዘ 2 ከሞተ በኃላ የታወቀ 1
በአንጎላ በቫይረሱ የተያዘ 2 የሞተ የለም
በጅቡቲ በቫይረሱ የተያዘ 1 የሞተ የለም
በኤርትራ በቫይረሱ የተያዘ 1 የሞተ የለም
በኡጋንዳ በቫይረሱ የተያዘ 1 የሞተ የለም
በሱማሌ በቫይረሱ የተያዘ 1 የሞተ የለም

  በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እ...
13/03/2020

በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!

➖ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው
አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

➖ ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ..ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡

➖ በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/Snow አትመገቡ!

➖ የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ
በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡

➖ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው::

➖አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ
ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር
በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው
ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው?

1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት
ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::
2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡ ሳምባን
በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!! በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?

1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ
መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላ በተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን
ያስገነዝበናል፡፡

< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን
ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ
ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡
< ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡

2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም
ሊቀንሰው ይችላል፡፡

3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ።

© ምንጭ : ዶ/ር ቤዛ አያሌዉ የቴሌግራም ገፅ

Address

123
Addis Ababa
123

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hulu Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hulu Media:

Share