EthioPost

EthioPost Ethiopian News,information & Entertainment portal Entertainment ....

ነብስ ይማር 😭😭😭እህታችን ወገኔበዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሕይወቷ ያለፈውየአራት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ ወገኔ ደበሌ የቀብር ስነስአት ከሰአታት በፊት ተፈፅሟል።በድ...
26/04/2020

ነብስ ይማር 😭😭😭

እህታችን ወገኔ

በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሕይወቷ ያለፈው

የአራት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ ወገኔ ደበሌ የቀብር ስነስአት ከሰአታት በፊት ተፈፅሟል።

በድጋሚ ነፍስ ይማር እያልን ለቤተሰቦቿ መፅናናትን እንመኛለን።

ምንጭ voa

በኢትዮጵያ ዛሬ ተጨማሪ 12 ስዎች:-* 12ቱ ከአዲስ አበባከኮሮናቫይረስ የተሻላቸው ሲሆን* በአጠቃላይ ከ123ቱ ስዎች ውስጥ* 41 ስዎች ከኮሮና ቫይረስ በሽታ አገግመዋልእስቲ ይሄ መልካም ዜ...
26/04/2020

በኢትዮጵያ ዛሬ ተጨማሪ 12 ስዎች:-

* 12ቱ ከአዲስ አበባ

ከኮሮናቫይረስ የተሻላቸው ሲሆን

* በአጠቃላይ ከ123ቱ ስዎች ውስጥ

* 41 ስዎች ከኮሮና ቫይረስ በሽታ አገግመዋል

እስቲ ይሄ መልካም ዜና ሼር አድርጉት

ምንጭ :- የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

ምከሩት ከማፈያ ቡድን ጋር አንሶላ እየተጋፈፈ ነው ተባለ ሲሉ ምንጮቻችን አስታወቁ"ምከሩት!!! ከስር ያለውን ፎቶ ያገኝሁት ከSintayehu Chekol ገጽ ላይ ነው፣ ከእስክንድርን ጋር በፎ...
26/04/2020

ምከሩት ከማፈያ ቡድን ጋር አንሶላ እየተጋፈፈ ነው ተባለ ሲሉ ምንጮቻችን አስታወቁ

"ምከሩት!!! ከስር ያለውን ፎቶ ያገኝሁት ከSintayehu Chekol ገጽ ላይ ነው፣ ከእስክንድርን ጋር በፎቶ የሚታየው ዘርፉ ነው፣ ዘርፉ ቦክሰኛው ይባላል፣ የፈንሳይ ልጅ በሚገባ ያውቀዋል!! ህግ የማይመልሰው እጅግ አደገኛ የማፍያ ቡድን መሪ ነው፣ ህዝብን ደም እንባ ያስለቀሰ!! don't take my words! ጌታቸው ሽፈራው በደንብ ያውቀዋል፣ ጌታቸው ፈረንሳይ እንደኖረ አውቃለሁ፣ ስለዚህ እሱን ጠይቁት!! እረ ፈረንሳይ መኖር አይጠበቅብህም ዘርፉን ለማወቅ፣ he is famous for wrong reasons!!!

ከዚህ በፊት የስድስት ኪሎ፣ የ05 እና የፈረንሳይ ማጅራት ቆልማሚዋችን የባልድራስ መስራች ብሎ በፎቶ ይዟቸው ወጥቷል፣ እነዚህን ሰዋች እስር ቤት እንደተዋወቃቸው መጠርጠር ይቻላል፣ ሰውየው ለነዚህ ሰዋች ሽፋን እየሰጠ ነው፣ ወንጀለኛን እያበረታታ ነው፣ empower እያደረጋቸው ነው፣ ነገ ጠዋት ሰው ገለው በቁጥጥር ስር ቢውሉ የባልድራስ አባላት በፖለቲካ አመለካከታቸው ታሰሩ መባሉ አይቀርም፣ this is so personal to me as my whole families are in the visinity!!!"

የጣረ-ሞት ስም የያዙ ህፃናች >>> አጀብ ነው ዘንድሮ------በህንድ የተወለዱ ሴትና ወንድ መንትዮች ኮሮና እና ኮቪዲ የሚል ስም እንደወጣላቸው ተሰማ።በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ህዝባችን...
05/04/2020

የጣረ-ሞት ስም የያዙ ህፃናች >>> አጀብ ነው ዘንድሮ
------
በህንድ የተወለዱ ሴትና ወንድ መንትዮች ኮሮና እና ኮቪዲ የሚል ስም እንደወጣላቸው ተሰማ።

በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ህዝባችን ከቤት እንዳይወጣ በመታዘዙ እኛም በዚህ ጭንቅ ሰአት ልጆች ስለወለድን ልጆቻችን የተወለዱበትን ግዜ ለማስታወስ ኮሮና እና ኮቪዲ በማለት ሰይመናቸዋል ሲሉ በማእከላዊ ህንድ ቻቲስጋሪ ግዛት የሚኖሩት የመንትዬዎቹ ወላጆች መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

ህንድ ከቤት በኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከቤት አለመውጣት ባዘዘች ከሁለት ቀን በኋላ ባለፈው ሳምንት የተወለዱት መንትዬዎቹ ከወጣላቸው ስም በፊት ሌላ ስም የወጣላችው ቢሆንም ባልና ሚሰቱ ቪናይ ቬርማ እና ፕሪቲ ቬርማ ስማቸውን አስቀይረውታል።

እናት ፕሪቲ ቬርማ እንዲህ አለች " በኮሮና ምክንያት ህንድ ጭንቀት ውስጥ ናት የልጆቻችን ስም ነገ በሽታው ሲጠፋ ሀገራችን የነበረችበትን ጭንቀት ያስታውሰናል " ብላለች።

አባት ቪናይ ቬርማ በበኩሉ " የልጆቻችን ስም ከኮሮና መጠበቅ ንፅህናንና እጅ መታጠብን እንደሚጠይቀው ይሄን ተግባር በሽታው ቢጠፋም የሁል ግዜ ተግባር እንድናደረገው ያስተዋስናል " ብሏል።

በኮሮና ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው የ60 ዓመት እናት : -ነብስ ይማር ->> RIP
05/04/2020

በኮሮና ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው የ60 ዓመት እናት : -ነብስ ይማር ->> RIP

እህተ-ማርያም...በእሷና በተከታዮቿ የቀን አቆጣጠር መሰረት የፋሲካን በዓል   በዛሬው እለት ስታከብር ምንጭ፣ አሉ .....ተባለ እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሰሽ እህተ ማሪያም --------...
05/04/2020

እህተ-ማርያም...

በእሷና በተከታዮቿ የቀን አቆጣጠር መሰረት የፋሲካን በዓል በዛሬው እለት ስታከብር

ምንጭ፣ አሉ .....ተባለ
እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሰሽ እህተ ማሪያም
--------
የዝግጅት ክፍሉ

ሟቿ የጋዜጠኛዋ አክስት ነበሩ!----------------------->>የኮሮና ሟች ኑዛዜ " የሃገሬ ህዝቦች ሆይ እራሳችሁን ከአስከፊው ቫይረ ስጠብቁ "•••••በአሁኑ ስዓት በኦሮሚያ ቴሌቭዥን...
05/04/2020

ሟቿ የጋዜጠኛዋ አክስት ነበሩ!
----------------------
->>የኮሮና ሟች ኑዛዜ " የሃገሬ ህዝቦች ሆይ እራሳችሁን ከአስከፊው ቫይረ ስጠብቁ "
•••••
በአሁኑ ስዓት በኦሮሚያ ቴሌቭዥን ውስጥ እየሰራች የምትገኘው ጋዜጠኛ ቢሊሴ ኢሬና የ60 ዓመት አዛውንት አክስቷ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የኮሮና ቫይረስ ሟች መሆኗን ተከትሎ በፌስቡክ ገጿ የሚከተለውን አስፍራለች።

“Biyya France turtee gara biyyaati Kan deebite adaadaankoo dhukuba koronaan qabamtee biyya keessati yaalamaa erga turtee booda hara boqoteetii. Waan jeenuu hinqabnuu nagaan boqodhu.
Yaalamiikoo maaloo dhukuba kanairraa of eegaa.”

"ፈረንሳይ ሐገር ቆይታ በቅርቡ ወደ ሐገር ቤት የተመለሰችው አክስቴ በኮሮና ቫይረስ ተይዛ የህክምና ርዳታ ሲደረግላት ከቆዬች በኋላ በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ሰዎች ሆይ እባካችሁ ከዚህ ገዳይ ቫይረስ ራሳችሁን ጠብቁ"

በኮሮና ቫይረስ  ምክንያት  በኢትዮጵያ የመጀመሪያው  ሞት  ተመዘገበ ->>ሁለት ሰዎች ዛሬ ተቀበሩ->>43 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው አይሲዩ ውስጥ ናቸው*******************የጤና ሚኒ...
05/04/2020

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ ->>ሁለት ሰዎች ዛሬ ተቀበሩ->>43 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው አይሲዩ ውስጥ ናቸው
*******************
የጤና ሚኒስቴርና ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና በሽታ (ኮቪድ-19) በቻይና ውሃን ከተማ ከተቀሰቀሰበት ግዜ አንስቶ ወደ ሀገራችን ቫይረሱ እንዳይገባ እንዲሁም ከገባ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረጉ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ቫይረሱ ወደ ሀገራችን ከገባ ጀምሮ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ቅስቀሳዎችን እያደረገና የተጠቂዎችን ቁጥርና የጤና ሁኔታቸው እያሳወቀ ነው፡፡ አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡

ህብረተሰቡ በዚህ ሳይደናገጥ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን (ቢያነስ አንድ ሜትር) ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

በኮሮና አይሲዩ(ICU) ውስጥ የገባው የመጀመሪያው ከብት ምንጭ:- ፌክ ኒውስ አለርት ፣ከአለርት ሆስፒታል
05/04/2020

በኮሮና አይሲዩ(ICU) ውስጥ የገባው የመጀመሪያው ከብት
ምንጭ:- ፌክ ኒውስ አለርት ፣ከአለርት ሆስፒታል

መሃል አዲስ አበባ ኮሮና ተብሎ የተበደበ ነጫጭባ ( ኩርድ ነጭ ካውካሺያን ስላልሆነ ነው; ) ) =>> መልእክት ተመልከቱ ወገንይህ ወጣት ኢትዮጵያውያን ውስጥ የሚኖር የቱርክ ኮርዳዊ ነው ስሙ...
02/04/2020

መሃል አዲስ አበባ ኮሮና ተብሎ የተበደበ ነጫጭባ ( ኩርድ ነጭ ካውካሺያን ስላልሆነ ነው; ) ) =>> መልእክት
ተመልከቱ ወገን

ይህ ወጣት ኢትዮጵያውያን ውስጥ የሚኖር የቱርክ ኮርዳዊ ነው ስሙም ሞ ጃርክስ ይባላል

በዩኒት ዩኒቨርስቲም በሲቪል ኢንጀርነት እየተማረ ይገኛል

ዛሬ በፌስብኩ ፔጅ ይህን አለ:-

መብራት ይዞኝ መኪና አቆሜ ነበር ከዛ ስዎች መጥተው በብረት አንተ ኮሮና እያሉ ጭንቅላቴን ፈነከቱኝ

እንደምታዩኝ ደም በደም ሆኛለው ግን ደሞ ፈጣሪ አትርፎኛል

እኔ አማረኛ እናገራለው የኢትዮጵያ ባህልም አውቃለው እዚህ ሀገርም ነው የምኖረው

ነገር ግን ነጭ ስለሆንኩ ብቻ ኮሮና ቫይረስ አንተ ነህ ያመጣህብን እያሉ ፈነከቱኝ

ምንም ያደረጉትን ነገር የለም ግን እንዲዚ አደረጉኝ

ምንጭ : - Mo Jarkas

ስለኮሮና ጥንቃቄ ምክር የለገሰው ግለሰብ ደመ ከልብ ሆነ♦ መሸለም የነበረባቸውን ሰው ደበደቡት !!!ያሬድ አማረ ፦ ሰፈሩ ብሔረ ጽጌ አካባቢ ሲሆን ፤ በትላንትናው ዕለት ሰፈሩ አካባቢ ሲንቀሳ...
02/04/2020

ስለኮሮና ጥንቃቄ ምክር የለገሰው ግለሰብ ደመ ከልብ ሆነ

♦ መሸለም የነበረባቸውን ሰው ደበደቡት !!!

ያሬድ አማረ ፦ ሰፈሩ ብሔረ ጽጌ አካባቢ ሲሆን ፤ በትላንትናው ዕለት ሰፈሩ አካባቢ ሲንቀሳቀስ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ባሉ መጠጥ ቤቶች ተሰባስበው፣ ሳይራራቁ ሲጠጡ በማየቱና ለሁሉም ስጋት የሆነው ኮሮናን ለማስተላለፍ ምቹ መሆናቸውን በማየትና በመታዘብ ፤ ይሄ ድርጊት መታረምም እንዳለበት በማኅበራዊ ሚዲያ በራሱ ገጽ ላይ በመግለጽ ፣ እንዲሁም የሚመለከተው አካል የመፍትኄ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አስተላልፉ ነበር።

ይሁን እንጂ ፤ ጠዋት ላይ ከዚህ በፊት የሚያውቃቸው ሁለት ወጣቶች ዛቻና ማስፈራሪያ አድርሰውበት የሄዱ ሲሆን ፤ አመሻሽ ላይ ደግሞ በድጋሚ መጥተው ደብድበውት ሄደዋል። እሱም የደረሰበትን በደል አካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ አመልክቷል ።

እህታችንን እናድናት........(ሁሉም ሰው   በማድረግም ይተባበር) ይህቺ በፎቶ ላይ የምትመላከቷት ወጣት ትግስት ፋንቱ ትባላለች በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ኩላሊቶቿ የመስራት አቅማቸው ስለተዳከ...
02/04/2020

እህታችንን እናድናት........

(ሁሉም ሰው በማድረግም ይተባበር)

ይህቺ በፎቶ ላይ የምትመላከቷት ወጣት ትግስት ፋንቱ ትባላለች በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ኩላሊቶቿ የመስራት አቅማቸው ስለተዳከመ የኩላሊት ንቅለ ተከላ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ማድረግ እንዳለባት ተግሯታል ቢሆንም ንቅለ ተከላው እስኪደረግላት ድረስ ቢያንስ እስከ ከስድስት ወር በላይ ስለሚቆይ እስከዛ ዲያሌስስ በሳምንት ሶስት ጊዜ እያደረገች መቆየት አለባት ወጪውም በአጠቃላይ 250.000 ብር በላይ ስለሚያስፈልጋት እባካችሁ በእግዚአብሔር ስም ከጎኗ እንቁም እላለው?ትግስት በተማረችበት ሙያ ሀገርዋን እና ወገንዋን የማገልገል፣ ህልም አላት ህልሟን ከእግዚአብሔር ጋር እውን እናድርገው።ተባረኩ።

ለመርዳት ምትሹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000174062823 ትግስት ፋንቱ ብላችሁ ማስገባት ትችላላችሁ።በአካል ለማግኘት ለምትሹ 0920707352 ካሌብ ብላችሁ መደወል ትችላላችሁ።

ለግንዛቤ*♦♦የኮቪድ19 በሽታ የየቀኑ ምልክቶች ♦♦******************************************👉 ከ1-3 ቀን• በነዚህ የመጀመሪያ ቀናት ቀላል ጉንፋን መሰል ሆኖ ቀለል...
31/03/2020

ለግንዛቤ
*
♦♦የኮቪድ19 በሽታ የየቀኑ ምልክቶች ♦♦
******************************************
👉 ከ1-3 ቀን

• በነዚህ የመጀመሪያ ቀናት ቀላል ጉንፋን መሰል ሆኖ ቀለል ያለ ትኩሳት እና
ጉሮሮ ህመም ብቻ ሲኖር የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ጥሩ ነው ።
• የሰውነት መከላከያ ደከም ያለባቸው ስዎች ቀለል ያለ ተቅማጥ እና ማቅለሽለሽ
ሊኖራቸው ይችላል ።

👉 በ 4 ኛው ቀን

• የጉሮው ህመም ይጨምራል እንደዚሁም የድምፅ መወፈር ይኖራል ።
• ብዙ ጊዜ ትኩሳት አይኖርም 36.5 degree ብቻ ይሆናል
• ቀለል ያለ እራስ ምታት እና የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ሊስተገዋጎል ይችላል ።

👉 በ 5 ኛው ቀን

• ስሜቶች የበለጠ ይጨምራሉ ፦ የጉሮሮ ህመም ይጨምራል ፣ ድምፅ የበለጠ
ይጎረንናል ።
• በእንቅስቃሴ ወቅት የስውነት ህመምና ቁርጥማት ይኖራል ፤ የሰውነት ድካም ይኖራል ።
👉 በ 6 ኛው ቀን

• ትኩሳት ይጀምራል
• ደረቅ ሳል ከጉሮሮ ህመም ጋር ይበረታል
• ምግብ በመመገብ ፣ የሚጠጣ ነገር ሲወስድ እንደዚሁም በንግግር ጊዜ የጉሮሮ
ህመም ይኖራል ።
• ተቅማጥና ማቅለሽለሽ የበለጠ ይጨምራል ።

👉 በ 7 ኛው ቀን

• ትኩሳት ከ 38 ድግሪ በላይ ይሆናል
• ደረቅ ሳል ይኖራል ፣ ይጨምራል
• የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ፣ ተቅማጥና ማቅለሽለሽ ይጨምራል ።
👉 በ 8 ኛው ቀን

• መተንፈስ መቸገር
• የደረት መክበድና ህመም
• ደረቅ ሳል ይኖራልም ይጨምራልም
• የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ይቀጥላልም በጣም ይጨምራል ።
• ትኩሳት ይቀጥላል ፣ ይጨምራል

👉 በ 9 ኛው ቀን እና በሚቀጥሉት ቀናት

• ሁልም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በጣም ይጨምራሉ ።

👉 👉 ማንኛው ስው የሚከተሉት አደገኛ ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና
ተቁአም መሄድ ያስፈልጋል ።

 የተራዘመ ድረቅ ሳል
 የትንፋሽ ማጠር
 የደረት ህመም
 ከፍተኛ ትኩሳት

እነዚህን ምልክቶች በሚያዩበት ወቅት ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደውል ያመልክቱ መጠንቀቅ ለራስ ነው የጤና ባለሙያዎች የሚያስተላልፉትን መልክቶች በአግባቡ መስማትና ስራ ላይ በማዋል ራሶትንና የቤተሰቦትን ጤና ይጠብቁ !

የኮሮና ቫይረስን ከምድር አጠፋለው ብሎ ወደ ቻይና የተጓዘው ናይጄሪያዊው ፓስተር/ነብይ እራሱ በኮሮና ተይዞ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ እያለ ነው በሚል የተለያዩ የናይጄሪያ የዜና አውታሮች እየዘገ...
23/03/2020

የኮሮና ቫይረስን ከምድር አጠፋለው ብሎ ወደ ቻይና የተጓዘው ናይጄሪያዊው ፓስተር/ነብይ እራሱ በኮሮና ተይዞ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ እያለ ነው በሚል የተለያዩ የናይጄሪያ የዜና አውታሮች እየዘገቡ ነው

ጥንቃቄ_ይደረግ...! አስቸኳይ ስለሆነም  እባካችሁ እባካችሁ ....ጥንቃቄ ይደረግኮሮናን ለመከላከል በሚል አልኮል የተቀባ እጅ እሳት ያለበት አካባቢ መገኘቱ አደገኛ ነው።ከታች የምትመለከቷት...
23/03/2020

ጥንቃቄ_ይደረግ...! አስቸኳይ ስለሆነም

እባካችሁ እባካችሁ ....ጥንቃቄ ይደረግ
ኮሮናን ለመከላከል በሚል አልኮል የተቀባ እጅ እሳት ያለበት አካባቢ መገኘቱ አደገኛ ነው።

ከታች የምትመለከቷት እህታችን አልኮል የተቀባ እጇን ባለማወቅ እሳት አካባቢ በማስጠጋቷ ጉዳት ደርሶባታልና እባካችሁ ላልሰማ አሰሙ ጥንቃቄም አድርጉ!
-----
ሼር_ሼር_ሼር

በአመት 10.2 ሚሊየን ዶላር የሚያገኘው የሊቨርፑሉ የፊት አጥቂ ማኔ የተሰነጣጠቀ, ዱቄት የሆነና የተጫጫረ አይፎን ይዞ መታየቱ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር፤ ስለሁኔታው የተጠየቀው ማኔ የሰጠው መልስ...
23/03/2020

በአመት 10.2 ሚሊየን ዶላር የሚያገኘው የሊቨርፑሉ የፊት አጥቂ ማኔ የተሰነጣጠቀ, ዱቄት የሆነና የተጫጫረ አይፎን ይዞ መታየቱ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር፤ ስለሁኔታው የተጠየቀው ማኔ የሰጠው መልስ ግን አስደናቂ ነበር
*
"10 ፌራሪ፣ 20 የዳይመንድ ሠአት እና 2 ጄት ፕሌንስ ምን ይሠሩልኛል? ለአለምስ ትርፋቸው ምንድነው? ተርቤ አቃለሁ፣ በባዶ እግሬም እጫወትም ነበር፣ ወደ ት/ቤትም አልገባሁም፡፡ አሁን ግን ሰዎችን መርዳት ችያለሁ፤ የኔ ምርጫ ት/ቤቶችን መገንባት እና የተቸገሩትን ማልበስና መመገብ ነው፡፡ ቅንጡ ቤት፣ መኪና እና ፕሌን አያስደስቱኝም፤ ለህዝቤ ህይወት ከሠጠቺኝ ማካፈሉ ነው የኔ ደስታ፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ የኮሮናቫይረስ አስደንጋጭ የስርጭት ፍጥነትን ይፋ አደረጉ======================================ዛሬ ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 354,677 ደርሷል።...
23/03/2020

ዶ/ር ቴድሮስ የኮሮናቫይረስ አስደንጋጭ የስርጭት ፍጥነትን ይፋ አደረጉ
======================================

ዛሬ ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 354,677 ደርሷል።

የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊው ከደቂቃዎች በፊት በሰጡት መግለጫ የቫይረሱን ስርጭት ፍጥነት እንደሚከተለው አስረድተዋል።

“በኮሮናቫይረስ የተያዘው የመጀመሪያ ሰው ሪፖርት ከተደረገ በኋላ፤ የመጀመሪያዎቹ 100ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ለመያዝ 67 ቀናት ወስደዋል። ቀጣዮቹ 100ሺህ ሰዎች የተያዙት በ11 ቀናት ውስጥ ሲሆን፤ ሦስተኛ 100ሺህ ሰዎች የተያዙት ደግሞ በ4 ቀናት ውስጥ ነው”
ብለዋል።
---BBC

ትልቅ ተስፋ የነበረው እውቁ የ30 ዓመቱ ወጣት የዙምባብዌ ጋዜጠኛ ዞሮሮ ማካምባ ዛሬ ህይወቱ ማለፉ ተነግሯል። ... ዞሮሮ በኮሮና ቫይረስ እንደተያዘ የታወቀው ከ2 ቀናት በፊት ነበር።ዞሮሮ፤...
23/03/2020

ትልቅ ተስፋ የነበረው እውቁ የ30 ዓመቱ ወጣት የዙምባብዌ ጋዜጠኛ ዞሮሮ ማካምባ ዛሬ ህይወቱ ማለፉ ተነግሯል። ... ዞሮሮ በኮሮና ቫይረስ እንደተያዘ የታወቀው ከ2 ቀናት በፊት ነበር።

ዞሮሮ፤ ...

* ፌብሩዋሪ 29 ኒው ዮርክ አሜሪካ ሄደ።

* ማርች 9 ከኒውዮርክ ተመለሰ፤ በጆሃንስበርግ አድርጎ ሀራሬ ተመለሰ።

* ማርች 12 ጉንፋ አይነት ህመም ጀመረው።

* ማርች 19 ህመሙ ሲብስበት ዶ/ር ጋር ሄደ። ዶ/ሩም ራሱን በመለየት እቤቱ እንዲቆይ ነግሮት፤ ለምርመራ specimen ወስዶ ሸኘው።

* ማርች 20፤ ህመሙ በጣም ፀንቶ ሆስፒታል ገባ።

* ማርች 21 የዝምቧብዌ ሁለተኛው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መሆኑ ተነገረ።

* ማርች 23 ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ይሄ እንግዴህ፤ ቫይረሱ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ለማስገንዘብ ያነጠርኩት እውነታ ነው። ሌላው በጣም አሳሳቢውና አስደንጋጩ ነገር፤ ... ዞሮሮ ከኒውዮርክ ከተመለሰ ወዲህ፤ ... ሁለት የቦርድ ስብሰባዎችን ተሳትፏል፤ On the weekend, ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ ብዙ ሰው የሚዝናናባቸው ሶስት መዝናኛ ቦታዎች ላይ ተገኝቷል፤ ሽሻ ቤት እንደነበረም ተገልፆል። በዚህም ምን ያህል ሰው ሳያውቅና ሳይታወቅ ለቫይረሱ እንደተጋለጠ ያሳያል። 🙆🏾‍♂️😱 ... [Rest In Peace young man!😭 ምናልባት ሞትህ ብዙዎችን አስደንግጦ ያነቃና ያድን ይሆናል!🙏🏾]



እጅ መታጠቡ፣ ፊትን አለመንካቱ እንዳለ ሆኖ፤ ... [በፍፁም የግድ ካልሆነ በስተቀር] ከቤት አትውጡ። ምክንያቱ ምንም ቢሆን፤ ብዙ ሰው ከሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ታቀቡ። መንግስትም፤ የትኛውንም አይነት ስብሰባዎችን ማገድ አለበት። ይህንን አልፎ ስብሰባ የሚጠራ የሐይማኖትም ሰውም ይሁን ምን፤ የህዝብን ደህንነት ለአደጋ በማጋለጥ ወንጀል በህግ ሊጠየቅ ይገባል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioPost posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share