25/08/2026
🚨 በሕይወት እያሉ ለልጅ የተሰጠ ንብረት በሕግ ይመለሳል?
ብዙ ወላጆች በሕይወት እያሉ ንብረታቸውን በስጦታ ውል (Donation) ለልጆቻቸው ያስተላልፋሉ። ነገር ግን ልጅ ስጦታውን ከተቀበለ በኋላ ወላጆቹን መንከባከብቢያቆም ወይም በደል ቢፈጽም ሕጉ ምን ይላል?
1️⃣ የስጦታ ውል ማፍረስ (ፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 2456-2457)፦ ስጦታ የተቀበለው ልጅ ወላጁን ባለመጦሩ፣ ከባድ የበደል ድርጊት በመፈጸሙ ወይም ባላከበረው (Ingratitude) ምክንያት ወላጅ የተሰጠውን ንብረት በፍርድ ቤት አፍርሶ የማስመልስ መብት አለው።
2️⃣ የመጦር ሕጋዊ ግዴታ (የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 198)፦ ልጆች አቅም የሌላቸውን ወላጆቻቸውን የመጦር፣ የመመገብ እና የመንከባከብ ሕጋዊ ግዴታ አለባቸው።
3️⃣ ጥንቃቄ፦ ወላጆች ንብረት በስጦታ ሲያስተላልፉ «እስከ ሕይወት ፍጻሜ የመጦር ግዴታ አለበት» የሚል ቅድመ-ሁኔታ በውሉ ላይ ማካተት ትልቅ ሕጋዊ ጥበቃ ይሰጣቸዋል።
🔔 ለተጨማሪ ትምህርታዊ የሕግ ግንዛቤዎች «ሕግ በብርሃን» ገጽን ፎሎው ያድርጉ!
#ሕግበብርሃን #የስጦታውል #የውርስሕግ #የሕግእውቀት #የኢትዮጵያሕግ