16/09/2026
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 " የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላትን በፅዱ አዲስ አበባ!" በሚል መሪ ሐሳብ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ::
───
መስከረም 6 - 2019 ዓም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት በጋራ በመሆን ከወረዳው ወጣት ማህበር እና በጎ ፍቃደኞች ጋር በመቀናጀት ፤ የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት በማስመልከት በጎጃም በረንዳ የቀላል ባቡር የሚተላለፍበትን መስመሮች የፅዳት ፕሮግራም አከናውኗል።:
የወረዳ 6 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ግዛቸው ይበልጣል እንዳስተላለፉት በአደባባይ የሚከበሩትን የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ስናከብር አንድነታችንን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በማስቀጠል ውብና ፅዱ አካባቢዎችን መፍጠር ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ይህንን የጽዳት ንቅናቄ ስናካሂድ የለውጥ መንግስታችን በዓለማቀፍ ደረጃ በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገብንበት ወቅት ላይ ሆነን ነው፡፡ በተለይም ከ7 ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ ከገባችበት የኢኮኖሚና የማህበራዊ ስብራት ወጥታ የተሻለ ማንሰራራትና በአለማቀፍ ደረጃ ከፍ ያለችበት እንዲሁም በእንጉርጉሮና በቁጭት ለዘመናት አብሮን የቆየውን አባይን በመገደብ ግድባችን ጨርሰን ፊታችንን ወደ ቀይ ባህር ያዞርንበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
የወረዳው የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ጽ/ቤት እንዲሁም የወረዳው ወጣቶች ክንፍ ፤ወጣቶች ማህበር ፣ሴት ማህበር እንዲሁም በጎፍቃደኞች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡