
28/07/2025
በአለም ከመጠን በላይ የወፈሩ ሰዎች ብዛት አንድ ቢልየን አልፏል ተባለ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን በላይ መድረሱን ዘ ላንሴት በተባለ ሳይንሳዊ መጽሔት ላይ የወጣ አንድ ጥናት አመለከተ።
ትንታኔው በፈረንጆቹ 1990 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ190 በሚበልጡ አገሮች የተገኘውን መረጃ ያካተተ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከመጠን ያለፈ ውፍረት በልጆችና በአዋቂዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
ይህም በሴት ልጆች ከ1.7% ወደ 6.9% እንዲሁም በወንድ ልጆች ከ2.1% ወደ 9.3% ከፍ ብሏል።
እ.ኤ.አ. በ2022 ወደ 160 ሚሊዮን የሚጠጉ ታዳጊዎች ከመጠን በላይ ውፍረው ነበረ።
በአዋቂዎችም ዘንድ ችግሩ ተባብሷል። ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ሴቶች መጠን ከ 8.8% ወደ 18.5% ሲጨምር፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ወንዶች መጠን ደግሞ ከ 4.8% ወደ 14% ከፍ ብሏል።
በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ሼፎች ጉባኤና የስርዓተ ምግብ የፖሊሲ ምክክር ላይ የተሳተፉ አፍሪካውያን ባለሙያዎች የተጠበሱ፣ በፋብሪካ የተቀነባበሩ እና ከውጭ የሚገቡ ምግቦች ከመጠን ላለፈ ውፍረት እና ለወሰስብስበሰ የጤና ጠንቆች እንደሚዳርጉ አሳስበዋል።