ሔኖክ ሚዲያ - Henok Media

ሔኖክ ሚዲያ - Henok Media #ኢትዮጵያ

https://youtu.be/npvEaLHBecM?si=z9FuKERM4480LlwZ
15/09/2025

https://youtu.be/npvEaLHBecM?si=z9FuKERM4480LlwZ

ሔኖክ ሚዲያ - Henok Mediaእንኳን ወደ ሔኖክ ሚዲያ በደህና ነጣችሁ፡፡ ሔኖክ ሚዲያ ታሪካዊ፣ ትውፊታዊ፣ ባሕላዊ፣ ማህበራዊ እና ኪነ-ጥበባዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰራ you tube channel ሲሆን ሰብስክራይብ...

11/09/2025
"ቀጥቅጠን ትግራዋይ የምናደርገው አካል እንደሌለ ልናውቅ ይገባል።”ሰመሀል መለስ ሰምሃል መለስ ዜናዊ ትላንት ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከ‘Landa Report’ ሚዲያ ጋር በነበራት ቆይታ...
06/09/2025

"ቀጥቅጠን ትግራዋይ የምናደርገው አካል እንደሌለ ልናውቅ ይገባል።”
ሰመሀል መለስ

ሰምሃል መለስ ዜናዊ ትላንት ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከ‘Landa Report’ ሚዲያ ጋር በነበራት ቆይታ ወልቃይትን አስመልክቶ ስትጠየቅ፤ ወልቃይት ላይ ‘Nation Building Failure’ አጋጥሞናል ብላለች።

ሰምሃል፤ ትግርኛ የሚናገሩ ኤርትራውያን እና ትግርኛ የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ገልጻ፤ ቋንቋ የማንነት መገለጫ አለመሆኑን በገደምዳሜም ቢሆን አስረድታለች።

የወልቃይትና የጎንደር መሳፍንት ግንኙነት ጠንካራ ነበር ያለችው ሰምሃል፤ የወልቃይት ገበሬን ያጣነው ግን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን ባለማረጋገጣችን ምክንያት ነው ብላለች።

አክላም፤ ቀደም ሲል በነበረው የህወሓት አስተዳደር፤ በሌላ የትግራይ አካባቢ ያልነበረውን ግዙፍ የፀጥታ ኃይል ወልቃይት ላይ እንደነበር ገልጻ፤ በዚህም እያስገደድክና እየደበደብክ ትግራዋይ ማድረግ አይቻልም ስትል አብራርታለች።

በምሳሌነት ስትጠቅስም “በፍላጎታችን ካልሆነ ቀጥቅጣችሁ ኢትዮጵያውያን አታደርጉንም እንዳልነው ሁሉ፤ እኛም ቀጥቅጠን ትግራዋይ የምናደርገው አካል እንደሌለ ልናውቅ ይገባል።” ስትል አስረድታለች።

አርቲስት ደበበ እሸቱ በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ አንጋፋው የመድረክ ፈርጥ፣ ደራሲ፣ ተርጓሚ፣ ተዋናይ፣ አዘጋጅ፤ መድረክ መሪ፣ ፖለቲከኛና  የሆኑት አርቲስት ደበበ እሸቱ በዛሬው...
17/08/2025

አርቲስት ደበበ እሸቱ በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አንጋፋው የመድረክ ፈርጥ፣ ደራሲ፣ ተርጓሚ፣ ተዋናይ፣ አዘጋጅ፤ መድረክ መሪ፣ ፖለቲከኛና የሆኑት አርቲስት ደበበ እሸቱ በዛሬው እለት 83 ዓመታቸው በሞት ተለይተዋል።

ታሪክ አድምጡ
15/08/2025

ታሪክ አድምጡ



"የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሩሲያ አዉሮፕላኖችን በኪራይ የመስጠት እቅድ የለዉም" አቶ መስፍን ጣሰዉየኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ አየር መንገዱ ለሩሲያ አው...
06/08/2025

"የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሩሲያ አዉሮፕላኖችን በኪራይ የመስጠት እቅድ የለዉም" አቶ መስፍን ጣሰዉ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ አየር መንገዱ ለሩሲያ አውሮፕላኖችን በኪራይ ለመስጠት በውይይት ላይ ነው የሚለው መረጃ ፍፁም ሐሰት ነዉ ሲሉ አስተባብለዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ይህን የገለጹት፣ አየር መንገዱ ከሩሲያ ጋር ስለአውሮፕላን ኪራይ እየተነጋገረ ነው በሚል የካፒታል ጋዜጣ ዘገባ ተከትሎ ነው።

Feta Daily - ፈታ ዴይሊ

የኦርቶዶክስን ንዋያተ ቅድሳት በየጭፈራ መድረኩ የማርከስ እንቅስቃሴ ተራ ብሽሽቅ ይምሰል እንጂ ተልእኮ እና ድጋፍ ያለው ነውብዙ ነገሮችን እና ጭካኔዎችን የተለማመድነው እንዲህ ነው። ሰዉ ጭራ...
06/08/2025

የኦርቶዶክስን ንዋያተ ቅድሳት በየጭፈራ መድረኩ የማርከስ እንቅስቃሴ ተራ ብሽሽቅ ይምሰል እንጂ ተልእኮ እና ድጋፍ ያለው ነው

ብዙ ነገሮችን እና ጭካኔዎችን የተለማመድነው እንዲህ ነው።

ሰዉ ጭራሽ በጨዋታ እያዋዛ፣ ለmeme አውሎት ቀልድ እየፈጠረበት የሚቀባበለው ነውር፣ ነገ በብዛት ሲታይ ማስደንገጡ ይቀንሳል።

ጧት ማታ በተለይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትን በማጣጣል ሥራ የተጠመዱ የአገርን መሠረቶች "ኋላ ቀር" በሚል ታርጋ ለማናጋት የሚጥሩ "ተራማጆች" ሳይቀር አሁን "እኛም ስንሰማ ደንግጠናል" ብለዋል።

ጭራሽ የእሱ "እምነታችሁን ተዉ" ማለትና ስንት አገር እንዳጠና ሰው ሕዝብን በጅምላ ማንኳሰስ፣ ለባህል መበረዝ እና ለነውር መብዛት አስተዋጽኦ የሌለው ይመስል፣ "ቅድስት አገር የምትሏት" ሁሉ ብሎ ለማሸማቀቅ የሚሞክር አለ።

ኋላ ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን እንጂ፣ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እስካለች የምዕራቡን ዓለም አጀንዳ በይፋ መዘርገፍ ከባድ ነው፤ ብለው በገንዘብ ድጋፍ ጭምር ከጀንደር እስከ ሀይማኖት አጀንዳ ይዘው የሚሰሩ እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

እንኳን ሌላው በማርያምና ተዋሕዶ ስም ወደ ድሮ ሄደናል የሚሉት harmless ቀውስ መስለው የሚታዩት እነ እህተ ማርያም ሳይቀር እምነት የማዳከምና አገርን በመጠበቅ ስም መሰረት የመሸርሸር ተልእኮ አያጡም። የኦርቶዶክስን ንዋያተ ቅድሳት በየጭፈራ መድረኩ የማርከስ እንቅስቃሴ ተራ ብሽሽቅ ይምሰል እንጂ፣ ተልእኮ እና ድጋፍ ያለው ነው።

በውስጡ የተደበቀውን የጥቃት ፍላጎትም ይህን ታክኮ የሚተነፍስ አለ። በነውር ብዙ ዓመት ወደፊት፣ በጨዋነት ብዙ ዓመት ወደ ኋላ ነው የተወረወርነው ብቻ። የሴቶችን ጉዳይ መነገጃ ባደረጉ ሰዎች ነውር ነገ ወላጅ ሴት ልጁን ከጥቃት ለማስጣል ቢሞክር እንኳን፣ መሸማቀቅ እንዲያተርፍ ያደርጋል። ነገ ያስፈራኛል።

ሁሌ እጠይቃለሁ። ራዲካል ፌሚኒስት ነን ባይ ሴቶች ላይ በዚህ ልክ ሴቶች ላይ መጨከን ለምን ይፈልጋሉ?

Yeneta tube የኔታ ቲዩብ

በስደት ላይ ሳሉ በጀልባ መስጠም ባጣናቸው ወጣቶች ሞት በጥልቅ አዝነናል - ባልደራስ"በሀገረ የመን አብያን በተባለ ግዛት አንዲት ጀልባ ሰምጣ ግምታዊ ቁጥራቸው አንድ መቶ ሰላሳ የሚደርሱ ኢት...
06/08/2025

በስደት ላይ ሳሉ በጀልባ መስጠም ባጣናቸው ወጣቶች ሞት በጥልቅ አዝነናል - ባልደራስ

"በሀገረ የመን አብያን በተባለ ግዛት አንዲት ጀልባ ሰምጣ ግምታዊ ቁጥራቸው አንድ መቶ ሰላሳ የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን ሕይወታቸው አልፏል።

የጦርነትና የሞት ቀጠና ከሆነችው ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተሰደው በጀልባ ሲጓዙ ከነበሩ 154 ኢትዮጵያዊያን ውስጥ 12 ሰዎች በሕይወት መትረፋቸው ተሰምቷል። በአሰቃቂው የስደት ጉዞ ሕይወታቸው ካለፉት ኢትዮጵያዊያን መካከል 68ቱ አስክሬናቸው የተገኘ ሲሆን፤ ሌሎች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም።

ባልደራስ ባህር በበላቸው ኢትዮጵያዊን ነፍስ መሪር ሀዘን የተሰማው መሆኑን እየገለፀ፤ የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል።

1. በሕይወት ለተረፉት ዜጎች ሁሉን አቀፍ እርዳታ እንዲደረግላቸው ለሁሉም ሰብዓዊ ፍጡር ጥሪ እናቀርባለን።

2. አስክሬናቸው የተገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መጥተው ስርዓት ቀብራቸው በሀገራቸው እንዲፈፀምላቸው ለሁሉም አካላት ጥሪ እናቀርባለን።

3. አድራሻቸው ያልታወቁ ኢትዮጵያዊያንን አስክሬን የመፈለግ ስራ እንዲፈፀም ሁሉም ዜጋ ትብብር እንዲያደርግ።

4, ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንዲታወጅና የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ባልደራስ ይጠይቃል።

በመጨረሻም ሟች ወገኖቻችን ነፍሳቸውን ፈጣሪ በአፀደ ገነት ያሳርፍ እያልን፣ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መፅናናትን እንመኛለን።"(ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ)

አዲስ ነገር መረጃ

I’ve taught over 500 students in theatre and film. Many know me for my art management classes — the ones I’ve enjoyed te...
05/08/2025

I’ve taught over 500 students in theatre and film. Many know me for my art management classes — the ones I’ve enjoyed teaching the most.

I’ve seen far too many great talents fail, not because they lacked talent, but because they lacked the right tools.

This training is the fix.

No background? No problem. This is made for people like us.

በዓለም ላይ የሂራቁን ሳዳም ሁሴን እና የሊቢያውን መሐመድ ጋዳፊን ጨምሮ ፣ ብዙ ነገሥታት ሹግጥ እጃቸው ላይ እያለ ተማርከው ፣ እጅ ሰጥተው ፣ ተሰቃይተው ተዋርደው አገራቸውንም አዋርደው ፣ ...
04/06/2025

በዓለም ላይ የሂራቁን ሳዳም ሁሴን እና የሊቢያውን መሐመድ ጋዳፊን ጨምሮ ፣ ብዙ ነገሥታት ሹግጥ እጃቸው ላይ እያለ ተማርከው ፣ እጅ ሰጥተው ፣ ተሰቃይተው ተዋርደው አገራቸውንም አዋርደው ፣ ክብራቸውን ሁሉ የጠላት መሳለቂያ አድርገው ፥ ላይቀርላቸው ነገር በጠላታቸው እጅ መገደላቸውን እናውቃለን፦ ለምሳሌ ያህልም ከታላላቅ ነገሥታቶች ውስጥ ጦርነት ላይ እጅ ስጡ ሲባሉ እጅ ሰጥተው ተማርከው ከተገደሉት ውስጥ ጥቂቶችን ለምስክርነት እንጠራለን፦

1. King Darius III of Persia
2. King Atahualpa of the Inca Empire
3. King Richard III of England
4. King Charles I of England
5. King Louis XVI of France
6. Jugurtha King of Numidia (North Afric)
7. Vercingetorix King of the Arverni (Gaul)
8. Bayinnaung's son (Nanda Bayin) King of Burma
9. Montezuma II Aztec Emperor

እንግዲህ ነገር ሳላበዛ እነዚህ ሁሉም ጦርነት ሲሸነፉ እጃቸው ሰጥተው ወይም ሊያመልጡ ሲሮጡ ተይዘው የተገደሉ ናቸው።

ምን ለማለት ፈልጌ ነው፦

ለክብሩ ሟች፣ የአገሩን ሥም በልዕልና ከፍ አድርጎ ይኽው እስከ ዛሬ ድረስ ለሁላችንም የመንፈስ ኩራት ሆኖ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ተቀምጦ ለዘለአለም በሕይወት የሚኖረው ቴዎድሮስ ነው።
.....የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ.....

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያ2017 #መቅደላ #ቴዎድሮስ
#መስቀል #ተዋህዶ #ኦርቶዶክሳዊ
#አፍሪካ #ላሊበላ

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል ፦1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤2. ብፁዕ አቡነ  ሳዊሮስን የመንበረ ...
23/05/2025

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል ፦

1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።

መረጃው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘ ነው።

እንኳን ለአርበኞች ቀን አደረሳችሁ።በአምስት ዓመት ነፃነት ትግሉ ውስጥ የሴቶች ሚና እጅግ ትልቅ ነው። ዘወትር መዘከርና ለትውልድ መነገር ያለበት ሥራ ነው። ይህንን ምክንያት በማድረግ የሴት ...
05/05/2025

እንኳን ለአርበኞች ቀን አደረሳችሁ።

በአምስት ዓመት ነፃነት ትግሉ ውስጥ የሴቶች ሚና እጅግ ትልቅ ነው። ዘወትር መዘከርና ለትውልድ መነገር ያለበት ሥራ ነው። ይህንን ምክንያት በማድረግ የሴት አርበኞችን ተጋድሎ የሚያሳይ ዝግጀት የቀረበ በመሆኑ በማስፈንጠሪያው በመግባት እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ።

https://youtu.be/8TX2dFw1b_Y?si=HEUZdnvepCpi1hOT

Like, Subscribe; comment ያድርጉ።

share በማድረግ ለሌሎች ያድርሱልን።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251966700540

Website

https://t.me/netib_media0

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሔኖክ ሚዲያ - Henok Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሔኖክ ሚዲያ - Henok Media:

Share