Ethiopica Media

Ethiopica Media ኢትዮፒካ - የኢትዮጵያ ቀለም! ይህ ገጽ የኢትዮፒካ ትሬዲንግ አ.ማ. እኀት ኩባንያ የኾነው የኢትዮፒካ ሚዲያ የፌስቡክ ገጽ ነው።

ከኢትዮጵያ ፋኖ በደቡብ የተሰጠ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት
17/01/2026

ከኢትዮጵያ ፋኖ በደቡብ የተሰጠ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት

17/01/2026
17/01/2026

👉 ሊቀ መንበር - ዘመነ ካሴ
👉 ተቀዳሚ ም/ሊ- መከታው ማሞ
👉 ም/ሊቀ መንበር ለወታደራዊ ዘርፍ- ሀብቴ ወልዴ
👉 ወታደራዊ አዛዥ - ብ/ጀ ተፈራ ማሞ
👉 ም/ወታደራዊ አዛዥ ኦፕሬሽናል -ዋርካው ምሬ ወዳጆ
👉 ም/ወታደራዊ አዛዥ አስተዳደር - ዝናቡ ልንገረው
👉 ም/ሊቀ መንበር እና የፖለቲካ ዘርፍ - ሄኖክ አዲሴ
👉 የእስትራቴጂክ መሪ - እስክንድር ነጋ
👉 ዘመቻ መሪ- አርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ
👉 ሕዝብ ግንኙነት - አርበኛ አስረስ ማረ
👉 ፖለቲካ - ጌታ አስራደ

"እባብ ያዬ በልጥ በረዬ❗❗በዚህ በእኛ ዘመን ብአዴንን የቀበረ እንጅ ያነበረ ኃይል አልተፈጠረም።አዲሱ ትውልድና አዲሱ አስተሳሰቡ ሁለተኝነትን አይቀበልም።(አዲስ ትውልድ የሚለው አገላለጽ የአ...
27/12/2025

"እባብ ያዬ በልጥ በረዬ❗❗

በዚህ በእኛ ዘመን ብአዴንን የቀበረ እንጅ ያነበረ ኃይል አልተፈጠረም።አዲሱ ትውልድና አዲሱ አስተሳሰቡ ሁለተኝነትን አይቀበልም።(አዲስ ትውልድ የሚለው አገላለጽ የአስተሳሰብንና የፖለቲካ ርእይን እንጅ እድሜን አይመለከትም። የአማራን ብሔርተኝነትና የህልውና ትግሉን የተቀበለ የ99 ዓመት አንድ አለሙ የሚሰኝ አማራም የአዲሱ ትውልድ አባል ነው።)
እና አዲሱ ትውልድ የማንም ሁለተኛ አይደለም ፥ማንንም ሁለተኛ ማድረግም አይሻም።ተከታይም አስከታም አይደለም። በፍፁም እኩልነትና ፍቅር ያምናል። ማንንም አንበርክኮ በማንም ተንበርክኮ መኖርን ለአንድ ቀን እንኳን አይፈቅድም።
የአማራ ህዝብ ከሌሎች ኃይሎችና ህዝቦች ጋር የመስራት አዝማሚያ ባሳዬ ቁጥር "ተለጠፈ፥ ሁለተኛ ሆነ፥ ጁኔርነት ነው ወዘተ" የሚሉ ራስ ጠል ትርክቶችን መፍጠር ለአዲሱ ትውልድ አይመጥንም። ሰው እንዴት ራሱን ይዘልፋል!?ሰው እንዴት ራሱን በውርደት ጅራፍ ይገርፋል!?

ጁኔርነትን፥ ሁለተኛነትን፥ የመብት ተመጽዋችነትንና ሽራፊ እጣፋንታ ለማኝነትን፥ ብአዴንን ስናስወግድ አነጣጥረን መተን በአንድ ገንዘን ቀብረናቸዋል። ይህን ማረጋገጥ የሚፈልግ ቢኖር ምናልባት እዛ አካባቢ አሁንም ጠረናቸው ይኖራልና ከጠቀመው ሂዶ ይፈልግ።

አንዳንድ ወገኖች "እባብ ያዬ በልጥ በረዬ "
ሆኖባቸው ልጥ ሲያዩ እባብ መስሏቸው ቢደነግጡ እንረዳለን። የብአዴን ተንበርካኪነት የፈጠረው ጠባሳ አሁንም ግንባራችን ላይ ስላለ መስጋቱ ጤናማ ነው። ከልክ በላይ መፍራት ግን ነውር ነው። እኛ እኮ ጠላቶቻችን እንደ እባብ ቀጥቅጠን ጥለን በዲሽቃ እየቀበርን ያለን ጀግኖች እንጅ የግራር ልጥ ባየን ቁጥር እባብ መስሎን የምንደነግጥ ከንቱዎች አይደለንም።የትም ቦታ ደረታችን ነፍተን ቀና ብለን እንሄድ ዘንድ በደም የተገዛ ክብር አለን። በአደባባይ ቀስቅሰንና ተቀሳቅሰን፥ በአደባባይ አደራጅተንና ተደራጅተን፥ በአደባባይ ታጥቀን፥ በኮረብቶቻችን ስር ጠላቶቻችን ቀብረን በኩራት የቆምን ነን። ሁለተኝነት የተሸናፊዎች እንጅ የእኛ የሸናፊዎች እጣ አይደለም። ጁኒየርነትንና ገባሪነትን እንኳን ለአማራ ህዝብ ለሌሎች ወገኖችም አንመኝም፥ አናወርስም።
ፋኖ የቀይ ባህር ቀጠና አዲሱ የጅኦ ፖለቲካ ኮኮብ እንደሚሆን ዛሬ ሳይሆን ትናንት በቃልም፥በወረቀትም፥ በካሴትም በድፍረትና በርግጠኝነት ስሜት ቀድመን ነግረናል። በአርቲስት ሃብቴ አብረሃም ጉረሮ
"ቀይ ባህር ሰፈር ታዬ አዲስ ኮኮብ፥
ይንቦገቦጋል ሰማይ ሊረከብ።
እንግዲህ አድማስ ተራ በተራ
ገለል በሉለት ለመጭው አውራ።") ስንል የአማራን ህዝብ መጭ የክብርና የኩራት ዘመን በጥበብ እየገለጽን ነበር።

አንድ ዘመን ያነጠረው ሐቅ አለ! ከዚህ በኋላ ከእኩልነት ውጭ መበላለጥን፥ አንበርካኪና ተንበርካኪነትን እንኳን የኛ የድል አድራጊዎች ትክሻ የኢትዮጵያ መሬት መሸከም አይችልም። ይፈነዳል። ያለነጻነትና ፍትሕ መሬት ተንቀጥቅጦ እንደ ቆርበት ይጠቀለላል፥ አድባር እንደ ቅቤ ይቀልጣል።
ይህን በውል የምንረዳው የአዲሱ ትውልድ አብዮተኞች እኛም አንገብርም ሌላውንም አናስገብርም። አቻ ብቻ!! ሁሉም ህዝቦች አቻ ናቸው።ሁሉም ኃይሎች የሚያስጠብቁት ጥቅም አላቸው። የኛንም አንሰጥም፥ የሌላውንም አንወስድም።አቻ ብቻ!!

ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!
አንድ አማራ!
እስከ ምጽአት አማራ!
አዲስ ትውልድ፥ አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ!

20/11/2025

ማዳጋስካር በውቅያኖስ የተከበበች ደሴት ናት። 360 ዲግሪ የሚለካ የባህር በር ያላት መሆኗ ለእድገቷ ዋስትና አልሆናትም። ስዊዘርላንድ የባህር በር የላትም። በዓመታዊ ጥቅል ምርት ወይም በነፍስ ወከፍ ገቢ አሊያም በህዝቧ የኑሮ ደረጃ ስትመዘን ካደጉት አገሮች ምድብ የምትገኝ ናት። የዘርፉ ምሁራን ወረቀቶች ዳሰሳ የባህር በር ለእድገት ዋስትናም ሆነ ቅድመ-ሁኔታ አለመሆኑን በተረጋገጠ አኳኃን ይነግሩናል። ኢትዮጵያ የዚህ ልዩ ሁኔታ የምትሆንበት ምክንያት የለም። የባህር በር ለኢትዮጵያ እድገት ቅድመ-ሁኔታ እና/ ወይም ዋስትና አይደለም። በተሟላ ችጋር ውስጥ የዘለቅነው፣ ወደ ቅርቃርም የገባነው የባህር በር ስላልኖረን አይደለም፤ የባህር በር ቢኖረንም ሁለንተናዊ እድገት የምናገኝ ስለመሆኑ ማረጋገጫ አይሆንም። ይህ ማለት ግን የባህር በር ለማናቸውም አገር እድገት ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የለውም ማለት ከቶ አይደለም። የባህር በር ለአንድ አገር እድገት ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ላይ ልዩነት የለም። ይህ የኃለኛውም ድምዳሜ ለኢትዮጵያም እውነት ነው።

አገዛዙ የባህር በርን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ እንዲሁም ለኢትዮጵያ እድገት የሚኖረውን ፋይዳ በሚመለከት በብዙ ማሳሳቻዎችና ማጭበርበሮች ሊፈጥረው የሞከረው ስምምነት የባህር በር ማምጣት የሚል ነው። ይህ እልም ያለ ውሸትና ዓይን ያወጣ ማጭበርበር ነው። የአራት ኪሎው የፖለቲካ አማተሮች የወደብን ጉዳይ እያቀነቀኑ ሊፈጥሩት የሞከሩት ህሊናዊ ሁኔታ ፈጽሞ እውን ሊሆን የማይችል ነው። ምክንያቱ ደግሞ ይህ ትውልድ ያ ትውልድ አይደለም፤ ይህን ትውልድ ማወቅ በሚመስል ልፈፋ፣ እውነት በሚመስል ኡኡታ ልታሳስተው አትችልም። መንግስት የመረጃ ሞኖፖሊውን ብቻ ሳይሆን የተረክ የበላይነቱን ከተቀማ ብዙ ዘመን ያለፈው ፣ የመረጃ አብዮት ፈንድቶ እልፍ አቅሞችን የፈጠረ ቢሆንም እነ አብይ አህመድ አሊ ገና ድሮ በጥራዝ ነጠቅነት በለቃቀሙት የእነ ማኪያቬሊ ምክሮች በእጅጉ የተለወጠውን ሁኔታ ለመምራት የሚዳክሩ ሆነዋል። በውጤቱም ሁኔታውን የሚከተሉ እንጅ ሁኔታ መምራት የማይችሉ ሆነው አንዱ ቀላል ችግር ሌሎች ውስብስብ ችግሮችን እየፈጠሩ የችግሮች ድር የተከመረባት አገር አድርገዋታል።

ይህ ትግል የግለሰብ ወይም የቡድን ወይም የኃይሎች ትግል አይደለም። ትግሉ የትውልድ ትግል ነው- የትግሉ አሳቢዎች፣ ተላሚዎች፣ ፈጻሚዎች እና ገምጋሚዎች የአዲሱ ትውልድ ዋኖች ናቸው። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ ማለት የአንድ ግለሰብ ወይም የአንድ ቡድን ጥሪ አይደለም።በዚህ ልክ የሚባል የእድሜ ገደብም የለውም። መደመር እንደሚባለው መፈክር የጨበጣ ልፈፋ ሳይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ የችግር ትንተና እና የመፍትሄ ትልም የታጨቀበት የዘመኑ ትውልድ ስምምነት ነው። መዋቅራዊና ስርዓታዊ ለሆነው የአማራ ህዝብ በደል፣ የህልውና አደጋ ውስጥ ገብቶ ለፈጽሞ መጥፋት የተዳረገ ህዝብ ልጆች መሰረታዊ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት በተካሄደ ማማጥ የተገኘ የትውልዱ አዋጅ ነው። ይህ ትውልድ በከረሙ ስልቶች ልትሸውደው የማትችል ከመሆኑ እኩል የሚያውጀውን ትግልም የማትገዳደረው ብርቱ ነው። ይህ ብርታቱ የትግሉን የስር ምክንያቶች፣ ዓላማዎችና ግቦች በጥልቀትና በጥራት ከመገንዘቡ የተነሳ በያዘው የሞራል ልዕልና ምክንያትም ነው።

በከረመው ስሪት እና በአሁኑ አገዛዝ ላይ ያመጸው ትውልድ ከሌሎች አገራት አቻዎቹ የሚወስደው ትምህርትም የሚያቀብለው ቁም-ነገርም አለው። አገዛዝን የሚነቀንቁ እና የሚያስወግዱ የዚህ ትውልድ አመጾችን በብዙ መልክእ፣ በልዩ ልዩ አቅጣጫ፣ በመንታ ስልቶች የሚመራ እንጅ በነጠላ ጉዳይ እና በአንድ ዘንግ ብቻ የሚቆም አይደለም። የትጥቅ ትግል መሪዎች የህዝባዊ አመጽና ተቃውሞ ጥሪ ሲያደርጉ እንግዳ የሚሆነውም የትውልዱን የመግባባት ጥልቀት ካለማወቅ፣ የተለወጠውን ህሊናዊና ነባራዊ ሁኔታ ካለመገንዘብ እንዲያውም የትጥቅ ትግል እና የህዝባዊ አመጽ ትግል የሚጠፋፉ መሆናቸውን ከሚያምን የአስተሳሰብ ውቅር የሚመነጭ ነው።
የብሄር ማንነት እና ኢትዮጵያዊነት የሚጠፋፉ አስመስሎ የሚተነትንን ብሄርተኝነት ሲያቀነቅን የኖረ ሁሉ የትጥቅ ትግል እና የህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል የሚሞላሉ ናቸው ሲባል ግራ መጋባቱ የማይጠበቅ አይደለም። ይህ ትውልድ የትግሉ ርዕዮተ-ዓለማዊ ቅኝት ብሄርተኝነት ሲሆን ብሄርተኝነቶቹ በአዎንታዊ የታሪክ ትንተና እና በበጎ የህዝቦች መስተጋብር እይታ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ የብሄርተኝነት ብያኔ የተባሉትን እና የሚባሉትን የጸረ-አገዛዝ ትግሉን ልዩ ልዩ ኃይሎችና ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የሚጠፋፉና አብረው የማይቆሙ ተደርገው የሚታዩትን የትግል ስልቶችም የሚያመጋግብበትን የትግል ቀመር አበጅቷል።
የማዳካስካር ወጣቶች ለባህር በር ሳይሆን ለነጻነትና ለዴሞክራሲ ወደ አደባባይ የወጡት የባህር በር ያላቸው በመሆናቸው ሳይሆን እጣ ፈንታቸውን የሚወስነው የመንግስታቸው ተፈጥሮ፣ የአስተዳደሩም ዘይቤ እነሱን የሚመስል ሲሆን ብቻ መሆኑን ስላወቁ ነው። በኢትዮጵያ ሁኔታም ከአገዛዝ ተላቅቆ በእኩልነት፣ በነጻነት፣ በአንድነት እና በፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ የህዝቦችን ህልውና፣ መብቶች እና ጥቅሞች የሚያከብርና የሚያስከብር ስርዓትና መዋቅር መፍጠር እና መገንባት ለእድገት ቅድመ-ሁኔታ እና ዋስትናም ነው። ገዥ ስልት ሆኖ እየተተገበረ ግዙፍ ድሎችን እያስመዘገበ ባለው የትጥቅ ትግል ማዕቀፍ የሚመራ የህዝባዊ አመጽና ተቃውሞ አስፈላጊና ተገቢ ነው።
*******
1. የዘርፉ ተንታኞች እና ምሁራን የዛሬውን ትውልድ የሰላማዊ አመጽና ተቃውሞ የትውልድ ዜድ አብዮት(GEN Z REVOLUTIONS) እያሉ የሚጠሩት ነው።

ሀጅ ሁሴን ሀሰን
ህዳር 11/2018 ዓ.ም

25/10/2025
የብርሃኑ ነጋ ታናሽ ወንድም እስክንድር ነጋእጅግ ከፍተኛ ትዕግሥትንና በሳል አእምሮን የሚጠይቁ ብዙ ሂደቶች ከታለፉ በኋላ የመግባቢያ ሰነድ፣ አሠራርና ሕግ ሁሉ ተዘጋጅቶ ከተጠናቀቀም በኋላ የ...
27/07/2024

የብርሃኑ ነጋ ታናሽ ወንድም እስክንድር ነጋ

እጅግ ከፍተኛ ትዕግሥትንና በሳል አእምሮን የሚጠይቁ ብዙ ሂደቶች ከታለፉ በኋላ የመግባቢያ ሰነድ፣ አሠራርና ሕግ ሁሉ ተዘጋጅቶ ከተጠናቀቀም በኋላ የአመራር አመራረጥን በተመለከተ መሥፈርቶች ላይ ውይይት ተደርጎና ስምምነት ላይ ተደርሶ ዐሥራ አራት ለእጩነት መመልመያ መሥፈርቶችን በማጽደቅ የእጩዎች ምልመላ ተጀመረ። በመግባቢያው መሠረትም ለእጩነት የሚቀርቡ ሦስት ሰዎች ሲሆኑ እነዚህም በዐሥራ አራቱ መመልመያ መሥፈርቶች ተመዝነው መሥፈርቶቹን አሟልተው ከተገኙ ብቻ ለእጩነት የሚቀርቡ መሆኑ ስምምነት ላይ ተደርሶ ወደመመልመል ተገባ። በመጀመሪያ አርበኛ ዘመነ ካሤ ለዕጩነት ተጠቁሞ በመሥፈርቶቹ መሠረት ሁሉንም አሟልቶ በመገኘቱ ያለአንዳች ተቃውሞ እጩ ሆኖ ተመረጠ። በኹለተኛነት ደግሞ ገዳማት ለገዳማት ሲያውደለድል የሚውለውና የደብረ ኤልያስ ገዳም መነኮሳትን ያስጨረሰው እስክንድር ነጋ ተጠቆመ። በመሥፈርቱ መሠረት ሲመዘን ግማሾቹን እንኳን የማያሟላ ሆኖ ተገኘ። ከዚያም አብሮ ያጸደቀውን መመሪያና መግባቢያ ሽሮ እኔ ካልተመረጥሁ ሞቼ እገኛለሁ በማለት ማወክ ጀመረ።

ሲጀመር የአማራ ፋኖ እስክንድርን እንደአንድ ታጋይ ቆጥሮ ለውይይት እንዲቀርብ ማድረጋችን በራሱ ትልቅ ስሕተት ነው። ምክንያቱም እስክንድር በአማራ ጥላቻ የናወዘ ገና ከመዐሕአድ ጀምሮ አማራው አማራ ሆኖ እንዳይቆም ሲታገል የኖረ፣ በሰንደቅዓላማ ተሸፍኖ የአማራን ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ስም ሲበዘብዝና ሲከፋፍል የኖረ ይህ ጸረአማራነቱም በጊዜ ሂደት የተጋለጠበት የብርሃኑ ነጋ ታናሽ ወንድም ነው። እስክንድር ማለት የተከበረ ሙያውን ትቶ ከነበረበት ማማ ላይ ወርዶ ዛሬ የዐቢይ አሕመድ ገረድ ከሆነው ብርሃኑ ነጋ ጋር በአካሄድና በዓላማ የሚመሳሰል ታናሹ ብርሃኑ ነጋ ነው። ለአማራ ሕዝብ ያላቸው ጥላቻና ድብቅ ሴራ፣ በኢትዮጵያዊነት ስም እየማሉ ዐማራን የሚያስጨፈጭፉና የሚከፋፍሉ መሆናቸው እንዲሁም በሥጣን ጥም የናወዙ መሆናቸው አንድ ያደርጋቸዋል። የአማራ ፋኖ እስክንድርን እንደአንድ ታጋይ ቆጥሮ ለውይይት መጋበዙ ውርደትም ስሕተትም ነበር። የሆነው ሆኖ አቶ እስክንድር ውይይቱና የእጩዎች ምልመላ ሳይጠናቀቅ በቅጽበት ራሱን መሪ አድርጎ በአማራ ሕዝብ ስም አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሦስተኛውን ድርጅቱን መመሥረቱን ይፋ አደረገ። በእርግጥ የባልደራስ መሪነቱን ጎዳና ላይ በደቂቃ የጠቀለለው ግለሰብ ራሱን በቅጽበት ሾሞ መከሠቱ የሚያስገርም አይሆንም። የጨረቃ ፋኖ ለሦስተኛ ጊዜ አቋቁሜያለሁ ያለው አቶ እስክንድር ለመሪነት የማይበቃ፣ ፖለቲካን የማያውቅ ጽፎ አዳሪ ጋዜጠኛ ብቻ ነው። ይህም በጊዜ ለሁሉም እየተገለጠ መጥቷል።

ብርሃኑ ነጋን አምኖና ተከትሎ ሲታለል የኖረው አማራ ዛሬ እስክንድር ነጋን ነቅቶበታል። በየገዳማቱ እያውደለደለ ገዳማዊያንንና ንጹሐንን ከማስጨፍጨፍ የዘለለ በትግሉ ውስጥ አንዳች ሚናና አበርክቶ የሌለው ጸረ አማራ መሆኑን ኹሉም አውቆበታል። ጥላቻው በአማራ ሕዝብ ላይ ብቻም አይደለም በሌሎችም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይም እንጂ። ኢትዮጵያዊነትን እኔ ልስጣችሁ የሚል ርዕዮትን የሚከተል፣ በአማራ ሕዝብ ላይ ተንጠላጥሎ ሥልጣን በመያዝ ኢትዮጵያዊነት ብሎ የሚጠራውን የማያምንበትን ሐሰተኛ ሐሳብ በሌሎች ሕዝቦች ላይ አስገድዶ ለመጫን የሚሠራ ጸረ ሕዝብ ነው እስክንድር ነጋ። ይህም ስለታወቀበት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እርሱን ትቶ ከአማራ ፋኖ ጎን ከቆመ ሰነባብቷል። ብቸኛ የእስክንድር ነጋ ደጋፊዎች እድሜያቸውን በከንቱ የጨረሱ የሥልሳዎቹ ብኩን ትውልዶችና የብአዴን አባላት ብቻ ናቸው። አማራ ሆኖ እስክንድርን የሚደግፍ የለም፣ ካለ ደግሞ አማራነቱን የካደና በገንዘብ ፍቅር የታወረ ሆዳም ዐማራ፣ የዐማራ ሕዝብም ቁጥር አንድ ጠላት በመሆኑ ከብአዴን ተለይቶ አይታይም።

በዚህም ሂደት ውስጥ አማራ ግን ያሸንፋል። በአራቱም ክፍላተ አገር የሚታገለው ፋኖም አንድነቱን በቅርቡ ይፋ ያደርጋል።

ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ሕዝብ!
ዐዲስ ትውልድ፣ ዐዲስ አስተሳሰብ፣ ዐዲስ ተስፋ!
አማራ!💪

በሥልጣን ፍላጎት ያበደ፣ እልፍ ድርጅቶችን ያፈረሰ፣ እልፍ ትግሎችን ያሰናከለ፣ በመጨረሻም በአማራ ሕዝብ ትከሻ ላይ ተራምዶ ዐራት ኪሎ ለመግባት በማሰብ የመነኮሳትን ቀሚስ ለብሶ ፋኖ ነጻ ባወ...
26/07/2024

በሥልጣን ፍላጎት ያበደ፣ እልፍ ድርጅቶችን ያፈረሰ፣ እልፍ ትግሎችን ያሰናከለ፣ በመጨረሻም በአማራ ሕዝብ ትከሻ ላይ ተራምዶ ዐራት ኪሎ ለመግባት በማሰብ የመነኮሳትን ቀሚስ ለብሶ ፋኖ ነጻ ባወጣቸው የዐማራ ገዳማት ውስጥ ሲያውደለድል የሚውል፣ በአንድ ዓመት ውስጥ በአማራ ሕዝብ ስም ሦስት ድርጅቶችን የመሠረተና ያከሰመ፣ የአማራ ሕዝብ ስላልተቀበለው የሥልጣን ሕልሙ ከመነሻው የከሸፈበት፣ ጸረ አማራነቱ በይፋ የተገለጠበት እንጭጩ አምባገነን ታናሹ እስክንድር!

በአማራ ሕዝብ ላይ ተንጠላጥሎ ሥልጣን በመያዝ 'ኢትዮጵያዊነት' ብሎ የሚጠራውን የማያምንበትን ሐሰተኛ ሐሳብ በብሔር ብሔረሰቦች ላይ ለመጫን፣ መነሻዬ አማራ መዳረሻየ ኢትዮጵያ በሚል ቅዠት የሚናውዝ ጸረ ብሔር ብሔረሰብ የሆነው ጩጬው አምባገነን ታናሹ እስክንድር!

ኢትዮጵያ በሁሉም ሕዝቦቿ መልካም ፈቃድ የምትገነባ፣ ኢትዮጵያዊነትም በሕዝቦች ነጻ ፈቃድ ከፍ የሚል ክቡር ማንነት እንጂ በአማራ ስም ሥልጣን ላይ ወጥተህ በሌሎች ሕዝቦች ላይ አስገድደህ የምትጭነው ፖለቲካዊ ማንነት አይደለም። ለዚህም ገና ከጅምሩ ሐሳብህን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተቃውሞታል። ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የእስክንድርን ሐሰተኛ ትርክት ጥለው ከአማራ ሕዝብ ትግል ጎን ከቆሙ ሰነበቱ!💪

ድል ለአማራ ሕዝብ!
ድል ለፋኖ!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
አማራ!💪

ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ!______________***_____________አርበኛ አሰግድ መኰንን የሚያደርገው የእንቅስቃሴ መረጃ የነበራቸው በእስክንድር ነጋ የሚመሩ ቅጥረኛ አማራ...
24/07/2024

ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ!
______________***_____________
አርበኛ አሰግድ መኰንን የሚያደርገው የእንቅስቃሴ መረጃ የነበራቸው በእስክንድር ነጋ የሚመሩ ቅጥረኛ አማራዎች ለጠላት መረጃ በመስጠትና ጠላትን በመተባበር በጠላቶቻችን እንዲታፈን አድርገዋል።
______________***_____________

አርበኛ አሰግድ መኮነን የአማራ ህዝብ የተደቀነበትን የህልውና አደጋ የተረዳና በሚደረገው የህልውና ተጋድሎ ጉልህ አበርክቶ የነበረው ጀግና መሪያችን ነው።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ከፍ ለማድረግ እና በጠራ የአማራ ብሔርተኝነት እንዲመራ የነበረው አበርክቶ ቀላል አይደለም።

ይሁን እንጅ በሂደቱ የአማራ ህዝብ ትግል መመራት ያለበት በጠራ የአማራ ብሔርተኝነት እና የአማራ ህዝብ የሚታገለው ሥርዓቱን ከሥረ መሠረቱ ለመቀየር ነው የሚለው የዕዙና የመሪያችን አቋም ያልተመቻቸው ትግል ጠላፊዎች በፈጠሩት እንቅፋት ከፍተኛ መዋከብ በመሪያችን ላይ እንደፈጠሩበት የሚታወቅ ነው። ከማዋከብም አልፈው ህይዎቴን ሰጥቼ የአማራን ህዝብ ነፃ አወጣለሁ ብሎ ለትግል የወጣን የአማራ ወጣት ሰራዊት እንዳዘመቱበትም የቅርብ ጊዜ እውነታ ነው።

ነገር ግን አርበኛ አሰግድ የአማራ የነፃነት ታጋይ እርስ በእርስ እንዲታኮስ ማድረግ የለብኝም የሚል ግልፅ ህዝባዊ አቋም በመያዝ የጦሩ ማዛዢያ የነበረውን ማጀቴን በመልቀቅ በታጋዮች መካከል ይፈጠር የነበረውን ችግር እንዳይፈጠር በማድረግ በሳል አመራር ሰጥቷል።

በዚህም ምክንያት ሁሉንም ታጋይ እንደወገን የሚመለከተው ታጋይ አሰግድ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ሥራዎችን ለመስራት ተገዷል። ሥራ ለማስኬድ የሚያደርገው የእንቅስቃሴ መረጃ የነበራቸው በእስክንድር ነጋ የሚመሩ ቅጥረኛ አማራዎች ለጠላት መረጃ በመስጠትና ጠላትን በመተባበር በጠላቶቻችን እንዲታፈን አድርገዋል።

እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ በቀን 15/11/2016 የብልፅግናው መንግስት ኮረኔል አሰግድ መኮነን እጅ ሰጠ በሚል ያወጣው መግለጫ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን ለመላው የአማራ ህዝብ እና ለትግላችን አጋሮች ለማሳወቅ እንወዳለን።

በመጨረሻም የአማራን ህዝብ ትግል ወደ ፊት በመውሰድ ግለሰቦች በጎ ሚና መጫወት እንደሚችሉ እሙን ቢሆንም የተጀመረው ትግል ግን በግለሰብ ላይ የተንጠለጠለ እንዳልሆነ እና ትግሉም የህዝብ ትግል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝም ሲመሰረት የተመሰረተው በጠንካራ መሠረት ላይ ነው። የተፈጠረውን የአመራር ክፍተት ለመሙላት ሲባል የዕዙ ሥራ አስፈፃሚ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የዕዙ ምክትል መሪ የነበሩትን ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋን የዕዙ ማዕከላዊ ኮሚቴ ተሰብስቦ ጠቅላላ ሪፎርም እስከሚሰራ ድረስ የዕዙ ዋና መሪ በማድረግ እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ እና ትግሉ ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ከሌሎች ግዛቶች የትግል ጓዶቻችን ጋር በመሆን ለማቀጣጠል ወስነናል።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ፥ ሸዋ፥ አማራ

ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!💪

ከመዐሕድ ጀምሮ በገንዘብና በጥቅማጥቅም ሳይገዛ ለአማራ ሕዝብ በጽናት ሲታገል የኖረው ጀግናው ኮማንደር አሰግድ መኰንን በOne Amhara ጠቋሚነትና በእስክንድር ነጋ ጸረአማራ ጭፍሮች መሪነት...
22/07/2024

ከመዐሕድ ጀምሮ በገንዘብና በጥቅማጥቅም ሳይገዛ ለአማራ ሕዝብ በጽናት ሲታገል የኖረው ጀግናው ኮማንደር አሰግድ መኰንን በOne Amhara ጠቋሚነትና በእስክንድር ነጋ ጸረአማራ ጭፍሮች መሪነት በጠላት እጅ ገብቷል። ይህም በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ውስጥ በአማራ ስም ተደራጅተው የቀረቡ የእስክንድር ነጋና መንጋዎቹን የጸረአማራነት ሥራና ሴራ ያጋለጠ ነው። ጀግና በትግል ሂደት ውስጥ በጠላት እጅ ሊወድቅ፣ ሊቆስል፣ አካሉ ሊጎድል፣ ሊሰዋም ይችላል። ይህ ኹሉ ግን ታሪኩን አያደበዝዘውም። አሰግድ የአማራ ጠላቶችን ሲያርበደብድና ሲያሰግድ የኖረ፣ ሕይወቱን ሙሉ ለአማራ ሕዝብ ሲታገል የኖረ አማራዊ ጀግና ታጋይ ነውና እናከብረዋለን። ሌላው በጊዜ ሂደት ይጠራል! የከሃዲው የእስክንድር ነጋን "የጨረቃ ፋኖዎች" እንጸየፋቸዋለን፣ እንታገላቸውማለን።

ድል ለአማራ ሕዝብ!
ድል ለፋኖ!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ አስተሳሰብ!
አማራ!💪

እስክንድር የዓላማ ጽናት ያለው ሰው ነው!ዓላማውም ሥልጣን መያዝ ነው። ለዚህም ያልገባበት የፖለቲካ ድርጅት የለም። አሁን እንኳን በአማራ ሕዝብ ስም በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ሦስት ድርጅት እ...
18/07/2024

እስክንድር የዓላማ ጽናት ያለው ሰው ነው!
ዓላማውም ሥልጣን መያዝ ነው። ለዚህም ያልገባበት የፖለቲካ ድርጅት የለም። አሁን እንኳን በአማራ ሕዝብ ስም በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ሦስት ድርጅት እስከመመሥረት የደረሰ ጽኑ ሰው ነው። የሚናፍቀውን ሥልጣን ለማግኘት ከአሜሪካ አዲስ አበባ፣ ከአዲስ አበባ ደግሞ ወጥቶ በአማራ በረሃዎች ወርጃለሁ ብሎ በየገዳማቱ ሲዞር የሚውል ለሥልጣን የመነነ ሰው ነው። ፋኖ ነጻ ባወጣቸው ቀጠናዎች እየተዘዋወረ የሚኖር አንዲት ጥይት ያልተኮሰ ነገርግን ራሱን ''ፋኖ'' አድርጎ ያቀረበ ሰው። በእርግጥ እርሱ የገባበት ድርጅት ጸንቶ ስለማይዘልቅ በአማራ ስም ለሦስተኛ ጊዜ መሠረትሁት ያለው ድርጅትም በጣም በቅርቡ ይከስማል። ድርጅት የአመራር ብቅት ይፈልጋል! Populist መሆን ለመሪነት አያበቃም። እስክንድር በቀደመ ታሪኩ በብዕሩ የሚታገል ታላቅ ሰው ነበረ። የሚያምርበትም ያ ሙያው ብቻ ነው። እስኬው ለጋዜጠኝነት የተፈጠረ ሰው ነው። የአማራን ሕዝብ ለመምራት ግን ዐቅሙም፣ ሥነልቡናውም አይመጥንም! ከአሁን በኋላ አማራን የሚመሩት አማራዎቹ ብቻ ናቸው። በሰንደቅ ዓላማ ተጀቡኖ አማራውን በማጭበርበር በአማራ ትከሻ ታዝሎ አራት ኪሎ የሚገባበት ዘመን አክትሟል። በቃ ዐማራ አማራ ሆኖ ተነሥቷል!

ድል ለአማራ ሕዝብ!
ድል ለፋኖ!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ ሐሳብ፣ አዲስ ተስፋ! አማራ!

ብሔር የሚል ቃል እንደሯንዳ በሕግ አግዶ፣ የብሔር ፌደራሊዝሙን ቀይሮ፣ ሕገ መንግሥቱን (ሕገ ትሕነግን) አሻሽሎ፣ ሁሉንም የሚያስማማ ሁሉም የሚሳተፍበት ሥርዓት ዘርግቶ፣ በኢትዮጵያዊነት ከፍታ...
13/11/2020

ብሔር የሚል ቃል እንደሯንዳ በሕግ አግዶ፣ የብሔር ፌደራሊዝሙን ቀይሮ፣ ሕገ መንግሥቱን (ሕገ ትሕነግን) አሻሽሎ፣ ሁሉንም የሚያስማማ ሁሉም የሚሳተፍበት ሥርዓት ዘርግቶ፣ በኢትዮጵያዊነት ከፍታ የጋራ የሆነች አገርን የሚገነባ መንግሥት ያምጣልን።

Address

Belay Zeleke Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopica Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopica Media:

Share