ሎዛ ሚዲያ-Loza Media

ሎዛ ሚዲያ-Loza Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሎዛ ሚዲያ-Loza Media, Media/News Company, Addisababa, Addis Ababa.

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በምሥራቅ አርሲ የተፈጸመውን የንፁሐን ወገኖቻችንን ግድያ በጽኑ እንደሚያወግዝ ገለጸ። ሎዛ ሚዲያ - Loza Media
30/10/2025

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በምሥራቅ አርሲ የተፈጸመውን የንፁሐን ወገኖቻችንን ግድያ በጽኑ እንደሚያወግዝ ገለጸ።

ሎዛ ሚዲያ - Loza Media

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ አርሲ...
30/10/2025

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ

የተሰጠ መግለጫ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ አርሲ ዞን አስተዳደር በጉና፣ በመርቲ፤ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ላይ ጥቅምት 14 ለ15 ቀን 2018 ዓ.ም በጉናና መርቲ ወረዳዎች 17 ክርስቲያኖች፣ ጥቅምት 17 ለ18 ቀን 2018 ዓ.ም. በሸርካ ወረዳ 3 ክርስቲያኖች እንዲሁም ጥቅምት 18 ለ19 ቀን 2018 ዓ.ም. በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 5 ክርስቲያኖች በድምሩ በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም. ብቻ 25 ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን አገራችንና ምድራችን ብለው በሰላም በተኙበት በድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉና ግድያውም ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መሆኑን የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የላከውን ሪፖርት ቋሚ ሲኖዶሱ የተመለከተው በከባድና ጥልቅ የኃዘን ስሜት ነው ፡፡

በመሆኑም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት እንዲህ ዓይነቱ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸም የቆየው በተደጋጋሚ እንደመሆኑ መጠን እንዲህ ዓይነቱ አስነዋሪ ድርጊት በቅዱሳት መጻሕፍት ሆነ በሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ በነጻነት የማምለክ ሕገ መንግሥታዊ መብትን የሚጋፋ፣ ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር መንፈሳዊ ዕሴቶቻችንን የሚያጠፋ፣ ክብረ ነክና ሊወገዝ የሚገባው ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል።

በመሆኑም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላትም ይህን ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ተግባር በጽኑ በማውገዝና በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን በሕይወት የመኖርና የእምነት ነጻነት መብትን እንዲያስከብሩልንና ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙትን ሕገ ወጥ ግለሰቦች ለሕግ በማቅረብ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪም በቀጣይ እንዲህ ዓይነቱ ሕገ ወጥ ተግባር እንዳይደገም አስፈላጊውን የሕግ ከለላ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በመጨረሻም በደረሰው ጉዳት የተሰማንን ከፍተኛ ኃዘንበድጋሚ እየገለጽን ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን በመመኘት በግፍ ሕይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችንም እግዚአብሐር አምላክ ዕረፍተ ነፍስን እንዲያድልልን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትፀልያለች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ቋሚ ሲኖዶስ

ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም

 #የአርሲ  ሰማዕታት
30/10/2025

#የአርሲ ሰማዕታት

  የቅዱስ ይምርሀነ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንሎዛ ሚዲያ - Loza Media
30/10/2025


የቅዱስ ይምርሀነ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
ሎዛ ሚዲያ - Loza Media

“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።” ሮሜ ፰፥፴፮በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ፲፬ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል።ከቅርብ ጊዜ ...
30/10/2025

“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።” ሮሜ ፰፥፴፮

በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ፲፬ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዝተን እየተለማመድነው የመጣነው የኦርቶዶክሳውያን ሞት ሊበቃ እና የሰው ልጆች ሁሉ የመኖር ሰብዓዊ መብት ሊረጋገጥ ይገባል።

በአካባቢው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በተደጋጋሚ በአማኙ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ሊያስቆሙ እና መፍትሔ ሊያበጁለት ይገባል።

በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስን ያድልልን፤ ለቤተሰቦቻቸው አጽናኝ ቅዱስ መንፈስን ይላክላቸው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !

29/10/2025

ሎዛ ሚዲያ - Loza Media

እንኳን አደረሳችሁ
29/10/2025

እንኳን አደረሳችሁ

28/10/2025

ተጋበዙልኝ

Address

Addisababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሎዛ ሚዲያ-Loza Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share