Ethiopian News Agency

Ethiopian News Agency ENA is the sole national wire service of Ethiopia.
(433)

The 84 years old ENA gathers and disseminates text news, audio and video stories about local and international events to media enterprises and the public. The Ethiopian News Agency (ENA) is the sole national wire service of Ethiopia.

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ከ1934 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 82 ዓመታት በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ውስጥ የዜና አገልግሎት ተግባር በማከናወን ላይ የሚገኝ ብቸኛው ተቋም ነው፡፡

11/07/2026

ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የሰላም ግንባታ የምታበረክተው ትልቁ ስጦታና ተሞክሮ ነው - በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህርና የህግ ባለሙያ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

#ኢዜአ

የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በአዲስ አበባ ይካሄዳል አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የ2026ቱን የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በመጪው ሐምሌ 6 እና 7 ቀን 201...
11/07/2026

የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የ2026ቱን የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በመጪው ሐምሌ 6 እና 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ያዘጋጀው ይህ ኤክስፖ፤ “በትምህርት ዘርፍ የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠንና ለአፍሪካ የክህሎት ዘመን የአዳዲስ መፍትሔዎችን ተደራሽነት ማስፋት” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ታውቋል።

ይህ አህጉራዊ ኤክስፖ በአፍሪካ የትምህርትና ክህሎት ሥርዓት ውስጥ ያሉ የጥራት፣ የተደራሽነትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ክፍተቶችን በቴክኖሎጂ አማካኝነት ለመፍታት ያለመ ነው።

መድረኩ በተለይም አዳዲስ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን በማስተዋወቅ የአፍሪካን የትምህርት ዘርፍ ማዘመን በሚቻልባቸው ስትራቴጂዎች ላይ ይመክራል።

በኤክስፖው በትምህርት፣ በከፍተኛ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በሮቦቲክስ ዘርፎች ከፍተኛ ተፅዕኖ ማምጣት የቻሉ ከ20 በላይ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች ለዕይታ ይቀርባሉ።

በተጨማሪም በዲጂታል ትምህርት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ በአረንጓዴ ክህሎቶች፣ በምርምርና በኢንዱስትሪ አጋርነት ላይ ያተኮሩ ውይይቶች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ውይይቶቹም ከአህጉራዊ የትምህርትና የሳይንስ ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተገልጿል።

በኤክስፖው ከ300 በላይ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ የፈጠራ ባለቤቶች፣ ተመራማሪዎች፣ የልማት አጋሮች እና የቴክኖሎጂ መሪዎች በአካል እንደሚገኙ ይጠበቃል።

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ታዳሚዎችም በበይነ መረብ አማካኝነት በሁነቱ ላይ እንደሚሳተፉ ኢዜአ ከአፍሪካ ኅብረት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ኤክስፖው በአጠቃላይ በአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ የዲጂታልና የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።

#ኢዜአ

11/07/2026

ቀደምት አባቶቻችን ዓድዋ ላይ ዋጋ ከፍለው ነጻ ሀገር እንዳስረከቡን ሁሉ፣ የአሁኑ ትውልድም በምክክር የፀናች ሀገር ለትውልድ ማሸጋገር ይጠበቅበታል -ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

#ኢዜአ

የፋይናንስ አካታችነት የሀገራዊ ሪፎርሙ ቁልፍ አጀንዳ ነው- የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)
11/07/2026

የፋይናንስ አካታችነት የሀገራዊ ሪፎርሙ ቁልፍ አጀንዳ ነው- የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንከ በሁሉም ባንኮች ዘንድ ያለውን የሴቶች የፋይናንስ አካታችነት በየጊዜው መሻሻሉን ለ...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞሪሺየስ የጀመረው አዲስ ቀጥታ በረራ ለንግድ፣ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት አዳዲስ ዕድሎችን ይፈጥራል አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር ...
11/07/2026

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞሪሺየስ የጀመረው አዲስ ቀጥታ በረራ ለንግድ፣ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት አዳዲስ ዕድሎችን ይፈጥራል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞሪሺየስ የጀመረው አዲስ ቀጥታ በረራ ለንግድ፣ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት አዳዲስ ዕድሎችን እንደሚፈጥር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞሪሺየስ ዋና ከተማ ፖርት ሉዊስ የቀጥታ በረራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞሪሺየስ የጀመረው አዲስ ቀጥታ በረራ የአፍሪካን ተደራሽነት በማስፋት የትስስር ጥረቱን የሚያጠናክር ስኬታማ ምዕራፍ ነው ተብሏል፡፡

የበረራው ማስጀመሪያ የመርሐግብር ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ በኢትዮጵያ የሞሪሺየስ ሪፐብሊክ አምባሳደር ኢንድራርጂት ባምቦዋ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርሐግብሩ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ እንዳሉት፣ አዲሱ የበረራ አገልግሎት የሁለቱ ሀገራት የአፍሪካ ውህደትን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል።

ይህ ድልድይ ለቀጠናዊ ትስስር፣ ለንግድ፣ ለቱሪዝም፣ ለኢንቨስትመንትና ለባሕል ልውውጥ አዳዲስ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

በሞሪሺየስ እና በአዲስ አበባ በኩል ወደ ቀሪው ዓለም የሚደረገውን ጉዞ በማቀላጠፍ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው፣ አዲሱ መስመር አየር መንገዱ በአፍሪካ ያለውን ትስስር ለማሳደግ ያለውን ስትራቴጂያዊ እቅድ ያሳያል ብለዋል።

ሞሪሺየስ የአየር መንገዱ 41ኛዋ የአፍሪካ መዳረሻ መሆኗን የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ ይህ በረራ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ዓላማዎችን በመደገፍ የኢኮኖሚ ትብብርን እንደሚያሻሽል አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ የሞሪሺየስ አምባሳደር ኢንደራርጂት ባምቡዋ፣ ይህ የበረራ መጀመር በሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን የአፍሪካ ልቀት፣ ጽናትና ፈጠራ ምልክት ሲሉ ያደነቁ ሲሆን፣ አዲሱ መስመር በአፍሪካ እና በሕንድ ውቅያኖስ ቀጠና መካከል ያለውን ትስስር በእጅጉ እንደሚያሳድግም እምነታቸውን ገልጸዋል።

ይህ አዲስ የበረራ አገልግሎት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከዓለም ጋር የሚያገናኝበትን መረብ ይበልጥ ያጠናክራል።

#ኢዜአ

11/07/2026

ኢትዮጵያውያን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በእኩልነት የሚመክሩበት መድረክ ተፈጥሯል - ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

#ኢዜአ

ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል የአሰራርና የቴክኖሎጂ አቅም ገንብታለች አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል የህግ፣...
11/07/2026

ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል የአሰራርና የቴክኖሎጂ አቅም ገንብታለች

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል የህግ፣ የአሰራርና የቴክኖሎጂ አቅም መገንባቷን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ገለፀ።

ከትናንት ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው ዓለም አቀፉ የፓርላማ የመረጃ ደኅንነት ፎረም ተጠናቋል።

በመድረኩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም፣ የሳይበር ደኅንነት፣ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና መሰል ዓለም አቀፍ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ በስፋት ተመክሮባቸዋል።

በዚህ ወቅት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል ጉታ እንዳሉት፤ የሳይበር ደህንነት ስጋቶች ድንበር የለሽ በመሆኑ ስጋቶችን ለመከላከል ዓለም አቀፍ ህጎችን የማጣጣምና የቅንጅት ስራ ወሳኝ ነው።

ሀገራት የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅና የሚቃጡ ጥቃቶችን ለመከላከል ተናባቢ ህጎች ሊኖራቸው እንደሚገባ አንስተው፣ ኢትዮጵያም በዚህ አግባብ እየሰራች መሆኗን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚያስችል የህግ፣ አሰራርና ቴክኖሎጂ አቅምን ገንብታለች።

ፎረሙ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መድረኮችን ለማዘጋጀት ያላትን አቅም ለማሳየትና ለገጽታ ግንባታ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑንም ተናግረዋል።

የናይጄሪያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፎረሙ አባል አግበዲ ዬቲዬኔ ፍሬድሪክ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ በተዘጋጀው ፎረም መሳተፋቸው ከተለያዩ ሀገራት ልምድ ለመለዋወጥ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።

በህንዱ በሚገኘው የካሊንጋ የኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ቫሩን ሱትራ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ፎረሙን ሙያዊ በሆነ አግባብ መምራቷ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ የተገነቡ የኮሪደርና የመንገድ መሠረተ ልማቶች ለትራፊክ ፍሰት መሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነውአዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የተገነቡ የኮሪደርና...
11/07/2026

በአዲስ አበባ የተገነቡ የኮሪደርና የመንገድ መሠረተ ልማቶች ለትራፊክ ፍሰት መሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የተገነቡ የኮሪደርና የመንገድ መሠረተ ልማቶች ለትራፊክ ፍሰት መሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ አስተያየታቸውን የሰጡ አሽከርካሪዎች ተናገሩ።

የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ በማስዋብ እና ዘመናዊ የመንገድ መሰረተ-ልማቶችን በመዘርጋት፣ የትራፊክ ፍሰትን ከማቀላጠፍ ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ቀልጣፋ አካባቢን መፍጠር አስችሏል፡፡

አስተያየታቸውን የሰጠ አሽከርካሪዎች በከተማዋ የተሰሩት አዳዲስ መንገዶች እና የኮሪደር ልማት የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ አዎንታዊ ለውጥ አምጥተዋል ብለዋል።

አሽከርካሪ ኃይሌ ዘመድኩና ጤናዬ ጠንክር እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማቱ ለትራፊክ ፍሰት አመቺ እና ዘመናዊ መንገዶችን በመፍጠር ስጋት የለሽ የማሽከርከር ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።

የከተማዋን ገጽታ በእጅጉ የቀየሩት እነዚህ ውብና ሰፋፊ መንገዶች፣ የዲዛይን ጥራታቸውና የተሟላ የመንገድ ምልክቶቻቸው ለትራፊክ አደጋ መቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ ብለዋል።

የኮሪደር ልማት ለአሽከርካሪዎች የላቀ የደህንነት ስሜትና የጉዞ ቅልጥፍናን ማስገኘቱንም ጠቅሰዋል።

አሽከርካሪ ብሩክ ግሩም የኮሪደር ልማቱ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በመቅረፍ ተሽከርካሪዎች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ በማድረጉ የጉዞ ጊዜን በአጭርና በአስተማማኝ ሁኔታ ማከናወን ተችሏል ብለዋል።

የመንገድ አቅም መጨመሩ ለትራፊክ ፍሰቱ መሻሻል ብቻ ሳይሆን፣ አደጋዎችን በእጅጉ በመቀነስ ለአሽከርካሪ ትልቅ የደህንነት እፎይታን የፈጠረ ልማት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ለከተማው ነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ እና የመንቀሳቀሻ አካባቢን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አበርክቶ አላቸው።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ዘርጋ እንደገለጹት፤ የተከናወኑት የኮሪደር ልማት ስራዎች የትራፊክ ፍሰቱን በማቀላጠፍና የከተማዋን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሰላማዊ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው።

ይህ ዘመናዊ የመንገድ አውታር እግረኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታን በመፍጠሩ በሰውና በንብረት ላይ ይደርስ የነበረውን የመንገድ አደጋ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ተችሏል ብለዋል።

ወጣቶች ዓመቱን ሙሉ በሚያከናውኗቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉአዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ ወጣቶች በክረምትና በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶ...
11/07/2026

ወጣቶች ዓመቱን ሙሉ በሚያከናውኗቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ ወጣቶች በክረምትና በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በመሳተፍ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ አባተ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በማስመልከት የደም-ልገሳ መርሐግብር አከናውነዋል፡፡

አባላቱ ይህንን አርዓያነት ያለው ተግባር በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ አባተ እንደገለጹት፤ ወጣቶቹ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዓመቱን ሙሉ በተለያዩ የልማትና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

በዚሁ መሠረት የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሩ አካል የሆነ የደም ልገሳ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት የተከናወነ ሲሆን፣ ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች ደም በመለገስ አርዓያነታቸውን ማሳየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ወጣቶቹ በማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፏቸው የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ለሀገራዊ አብሮነትና ለዜግነት ግዴታ መወጣት ትልቅ ሚና ያለው በመሆኑ፣ ተሳትፏቸውን በቀጣይም በላቀ ሁኔታ እንደሚያጠናክሩት አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አባላት፣ በደም እጥረት ምክንያት የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለመቀነስ ትኩረት አድርገው በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት በተከናወነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ የተሳተፉ ወጣቶች እንደገለጹት፤ ደም መለገስ የሰው ልጅን ሕይወት የመታደግ አርዓያነት ያለው ተግባር ነው ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡት ወጣቶች መካካል ብርቱካን ገብሬ እንዳለችው ደም መለገስ መስጠት ከባድ ኃላፊነትና ሰብአዊ ግዴታ መሆኑን ተናግራለች፡፡

ወጣት ጉዲና ስሜ ደም መለገስ የዘወትር ተግባሩ እንደሆነ ገልጾ፣ ደም ከመለገስ ባለፈም በሌሎች የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

በደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ ለሰባተኛ ጊዜ መሳተፏን የገለጸችው አዲስ ሙሉጌታ በበኩሏ በጎ ፈቃደኝነት የህሊና እረፍት የሚሰጥ ተግባር መሆኑን ጠቅሳለች፡፡

ወጣቶች እያከናወኑት የሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ የዜግነት ግዴታቸውን ከመወጣት ባሻገር ለማኅበረሰቡ ደኅንነት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

#ኢዜአ

በወጪ ንግድ የተመዘገበውን ውጤት ይበልጥ ለማሳደግ በምርት ጥራትና እሴት መጨመር ላይ ትኩረት ተደርጓል - ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)ሀዋሳ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ):- በሀገሪቱ በወጪ ...
11/07/2026

በወጪ ንግድ የተመዘገበውን ውጤት ይበልጥ ለማሳደግ በምርት ጥራትና እሴት መጨመር ላይ ትኩረት ተደርጓል - ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

ሀዋሳ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ):- በሀገሪቱ በወጪ ንግድ የተመዘገበውን ውጤት ይበልጥ ለማሳደግ በምርት ጥራትና እሴት መጨመር ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክን የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን፣ በፓርኩ የአቮካዶ፣ ዘይትና ቡናን የሚያቀናብሩ ኩባንያዎችን ተመልክተዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፤ መንግሥት የወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ በእሴት መጨመር ሥራ ላይ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማጠናከር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል።

በተለይም በግብርናው ዘርፍ ያለውን አቅም በአግባቡ በመጠቀምና ገበያው በሚፈልገው መልኩ እሴት ጨምሮ መላክ ላይ የተጀመሩ ጥረቶች የሚጠናከሩ ናቸው ብለዋል።

በፓርኩም በአቮካዶና በቡና ዘርፍ በመሰማራት እሴት በመጨመር የወጪ ገቢ ግኝትና ተኪ ምርት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎችን መመልከታቸውን ጠቅሰው፤ ተግባሩን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በዘንድሮ ዓመት ከወጪ ንግድ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በማግኘት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻሏን ያወሱት ሚኒስትሩ፤ በፓርኩ የሚታዩ እንቅስቃሴዎችን ማሳደግ ይገባልም ብለዋል።

በእስካሁኑ ሂደትም ተኪ ምርቶች ላይ እንደሀገር እየተገኘ ያለውን ውጤት ለማጠናከር የሚደረጉ ጥረቶች አበረታች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

በዚህ ሂደት ደግሞ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርኮች መቋቋማቸው ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ቡናን በማቀነባበር ስራ ላይ የተሰማራው የ“መይ መይ ቡና ፕሮሰሲንግ” ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ጄይ ሰን፣ በመንግሥት በተደረገላቸው ድጋፍ ታግዘው ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቅሰዋል።

Address

Belay Zeleke
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian News Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian News Agency:

Shortcuts

Share

Category