Yohannes Eshetu

Yohannes Eshetu በዚህ ገፅ ላይ መንፈሳዊ ትምህርቶችና የቴክኖሎጂ ዕውቀቶች ይተላለፋሉ።

👉 ሰሉስ የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ አርብ ደግሞ ቅኔ ዘአርብ በሚል ስያሜ የቅኔ ቀን ነው።

22/07/2025

በረከተ ቅዱስ
ኤፍሬም ሶርያዊ ወኤፍሬም ለብሀዊ
የሀሉ ምስለ ኩልነ ህዝበ ክርስቲያን

ከቅዱስ ኤፍሬም በረከት ይክፈለን!

14/07/2025

እምነት
እግዚአብሔርን እንግዳ አድርጎ ወደ ቤትህ የሚያስገባ ሀይል ነው።

የሥላሴ በረከት ከቤታችን ይግባ!

11/07/2025

ጌታውን የካደ የጴጥሮስ እጅ የሰማይ መንግስትን መክፈቻ ተቀበለ። አሳዳጁ ጳውሎስም የወንጌል መምህር ሆነ!

10/07/2025

እውነት ነው! ኃጢአትን ለህሊናህ ከባድ እስክትሆንብህ ድረስ ደጋግመህ ልትሰራት ትችላለህ። ራስህን ልትጠየፈውና ልትጠላው ብሎም የማትለወጥ እንደሆንክ ሊሰማህ ይችላል።

ይህ ነገር ሲደጋገም ተስፋ ወደ መቁረጥ ያደርስሃል። የሰይጣን አሰራር ደግሞ ከምታስበው በላይ በጥናትና በድግግሞሽ ላይ የተመሰረተ ነውና አንተን ተስፋ ማስቆረጥ ዋነኛ ዓላማው ነው።

መድኃኒቱ ምንድነው?

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአብዛኛው ጻድቃን ፣ ቅዱሳን ብላ የምትዘክራቸው ሰዎች በዚህ የኃጢአት መንገድ ላይ ሳያልፉ ቀርተው አይደለም። ልዩነቱ በወደቁ ቁጥር ይነሳሉ። በበደሉ ቁጥር ንስሐ ይገባሉ። ተስፋ መቁረጥን ፈጽመው አያውቁትም።

ስለዚህ ተነስ ፣ ተመለስ ፣ ከኃጢአት አልጋ ላይ ውረድና እንደ ትናንቱ ጸሎትህን አድርስ። መሐሪውን አምላክ "አበስኩ እግዚኦ አበስኩ" እያልክ ለምነው። ቸር የሆነውን አምላክ በአንተ የህሊና ሚዛን አትመዝነው። ዘኢይትረአይ ወዘኢይትአወቅ እንዲል ካንተ የህሊና መለኪያ በላይ ነው።

አምላክ የሚቆጥረው ያንተን የንስሐ ጊዜያት ነው እንጂ ያንተን የኃጢአት ብዛት አይደለም። የቆሸሸው ነጭ ልብስህ ታጥቦ ስታየው እንደሚያስደስትህ በኃጢአት የቆሸሸው አንተነትህ በማየ ንስሐ ሲታጠብ ፈጣሪና ፍጡራን ባንተ ደስ ይላቸዋል።

ባለ ቅኔው

ወዕሩያነ ግብር ኮኑ በሳምናዊት ዕለት
ሰብእ በዓመጻ ወእግዚአብሔር በምህረት

ብሎ በኋለኛው ዘመን ሰው በበደሉ እግዚአብሔር ደግሞ በምህረቱ እኩል መሆናቸውን ይናገራል።

አስተውል! ነገም ልትበድል ትችላለህ ግን በንስሐ ተመለስ። ፍጹም እስክትሆንና ከኃጢአት እስክትርቅ ድረስ ክርስትና በንስሐ ድግግሞሽ ውስጥ ያለ ህይወት ነውና።

የእግዚአብሔርን ዕለት ጠብቅ!እግዚአብሔር እስኪመጣ ጠብቅ። የእርሱን ጊዜ በራስህ ጊዜ ለመለወጥ አትጣር። እግዚአብሔርን መጠበቅ ዘለዓለማዊ ትርፍ አለው።ዘካርያስና ኤልሳቤጥ የእግዚአብሔርን ቀን...
07/07/2025

የእግዚአብሔርን ዕለት ጠብቅ!

እግዚአብሔር እስኪመጣ ጠብቅ። የእርሱን ጊዜ በራስህ ጊዜ ለመለወጥ አትጣር። እግዚአብሔርን መጠበቅ ዘለዓለማዊ ትርፍ አለው።

ዘካርያስና ኤልሳቤጥ የእግዚአብሔርን ቀን ጠብቀዋል። ልጅ አልነበራቸውም። ነገር ግን አላማረሩም። ለእግዚአብሔር ያላቸው ተገዥነት በደስታውም በሀዘኑም ጊዜ ያው ነው።

ቀኑ ሲደርስ ፣ ይሆን ዘንድ በማይቻልበት ጊዜ ኤልሳቤጥ ጸነሰች። ያውም በዘጠና ዘመን ደም ባለቀበት ፣ ልምላሜ በደረቀበት ፣ ዘር በራቀበት ፣ ሁሉም ነገር ባዶ በሚመስልበት!

በከበረች በጌታ ዕለት ጌታውን የሚያጠምቅ ፣ የምድረ በዳው ባህታዊ ፣ በእናቱ ሆድ ለአምላኩ የሰገደ ፣ ነቢይ ወሐዋርያ ፣ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ።

በመጠበቅ ውስጥ ድካም ሊኖር ይችላል። መጨረሻው ግን ደስታ ነው። አባቱ "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ" ብሎ ሲመርቀው የወለደችው እናቱ ደስታዋ ቢሆን "ዮሐንስ ይሰመይ" ስትል ፤ ጎረቤቶቿ ሁሉ በሀሴት ተሞልተው ነበር።

እግዚአብሔር የሚመጣው ሁሉ ነገር ሲፈጸም ፣ ተስፋ ያደረግነው ሰዋዊ ሀሳባችን ባዶ ሲሆን ፣ የሀሳብ ልምላሜያችን ሲደርቅ ነው። ያሰብነውን ሳይሆን ያሰበውን ሲሰጠን ደስታው ከእኛ አልፎ ለሁሉ ይሆናል። እናም እንደ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ዮሐንስን እናገኝ ዘንድ የጌታን ዕለት በተስፋ እንጠብቅ። የጌታ ዕለት ባላሰብናት ፣ ባልጠበቅናት ጊዜ ትሆናለችና።

ሰላም ለፅንሰትከ እንበለ ኃጢዓት ወግማኔ
ወለልደትከ ሰላም አመ ሠላሳሁ ለሰኔ
ዮሐንስ ዘኮንከ ደመና ሰማይ ኮናኔ
አዝንም መና አዕምሮ ወኅብስተ ጥበብ ኩነኔ
ኀበ ሕዝበ ልብየ ኀብሩ ወገብሩ ኩርጓኔ

ሰኔ 30፣ 2017 ዓመተ እግዚእ

04/07/2025

እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ድንቅ ስም መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ!

01/07/2025

የኢትዮጵያን መንበር በስሙ ያስጠራ ፣ አምሳሊሆሙ ለሱራፌል አባ ተክለ ሃይማኖት!

በረከቱ አይለየን!

30/06/2025

በጭንቅ ጊዜ ፈጥኖ ደራሹ ፤ ባለ ነጭ ፈረሱ ሰማእት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁልጊዜም በረድኤት አይለየን።

26/06/2025

ገብርኤል ዘትቀውም ለእግዚአብሔር ውሳጤ ቤቱ
ኢኮነ በምግባርየ ዳዕሙ በከንቱ
እምኀቤከ ዘልፈ ረድኤተከ እፈቱ

አላዋቂው ባህራንባህራን የሞቱን ደብዳቤ ይዞ እየተጓዘ እንደሆነ አያውቅም። የላከውን ሰው በታማኝነት እያገለገለ ነው። ቅዱስ ሚካኤል በፈረስ ላይ ተቀምጦ ደብዳቤውን ሲለውጥለት ባህራን የተለወጠ...
19/06/2025

አላዋቂው ባህራን

ባህራን የሞቱን ደብዳቤ ይዞ እየተጓዘ እንደሆነ አያውቅም። የላከውን ሰው በታማኝነት እያገለገለ ነው። ቅዱስ ሚካኤል በፈረስ ላይ ተቀምጦ ደብዳቤውን ሲለውጥለት ባህራን የተለወጠው ነገር የሞት ይሁን የህይወት አያውቅም። መንገዱን ቀጠለ። ሞቱ ወደ ህይወት ተለወጠ።

በህይወታችን እንደ ባህራን ሳናውቃቸው የተለወጡ የመከራና የሞት ደብዳቤዎች አሉ። ከምንጠፋበት ወጥመድ ሳናውቀው ድነናል። የተደገሰልን የጥፋት ድግስ ሳናውቀው ከሽፏል። ይህ ሁሉ የሆነው በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት በእግዚአብሔር ቸርነት ነው!

እኛም እንደ ደራሲው እንዲህ እያልን እንለምነዋለን።

ሚካኤል ኢታንትግ ዘኂሩትከ ልማደ
በጊዜ ምንዳቤ ኀበ ሀሎኩ እንዘ አመለትህ እደ
ለረዲኦትየ ነዓ ከዊነከ ነግደ

ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ልማድህ የሆነውን የቸርነት ስራ እንዳታጎድል ፤ በጭንቅ ሰዓት እጆቼን ዘርግቼ ሳለሁ ትረዳኝ ዘንድ እንግዳ ሆነህ ወደኔ ና!

ሰናይ መልእክትብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልእ ያስተላለፉት ግሩም መልእክት!በረከታቸው ይድረሰን!
10/06/2025

ሰናይ መልእክት

ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልእ ያስተላለፉት ግሩም መልእክት!

በረከታቸው ይድረሰን!

09/06/2025

ሰናይ ወርኃ ጾም!
የበረከት ያድርግልን!

Address

Addis Ababa

Telephone

+251921625794

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yohannes Eshetu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yohannes Eshetu:

Share