16/09/2025
━━━◇የብርቱካን ልጣጭ◇━━━━
☛ በሰውነት ውስጥ ያለን የማይፈለግ ኮሌስትሮል ያስወግዳል፡፡
☛ በልጣጩ ላይ ያሉ ንጥረ ነገሮች የካንሰር ህዋስ እድገትንም ለመግታት ያግዛሉ፡፡
☛ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ እንዲሁም የልብ ህመም ስጋትን ለመቀነስም የሚጫወተው ሚና የላቀ ነው፡፡
☛ ለመተንፈሻ አካላት ጤንነት በተለይም ሳምባን ንፁህ ለማድረግ እና አስምን
ለማከም አጋዥ ነው::
☛ የምግብ መፈጨት ስርአትን ለማስተካከል ቃርን፣ማስመለስን ለማስታገስም ይጠቅማል፡፡
☛ ማስቲካን ከማኘክ በበለጠ የብርቱካን ልጣጭን ማኘክ መጥፎ የአፍ ጠረንን ያስወግዳል፡፡
☛በቤት ውስጥ መልካም ጠረን እንዲኖር ለማድረግ የደረቀ የብርቱካን ልጣጭን ከቅርንፉድ ጋር አድርገን ብናፈላ እንፋሎቱ ግሩም መአዛ ይሰጥልናል፡፡
☛ የተፈጨ የብርቱካን ልጣጭን ከጥቂት ውሀ ጋር ደባልቆ የራስ ቅልን መቀባት ፎሮፎርንም ያስወግዳል፡፡
☛ ለ20 ደቂቃ ያህል በፈላ ውሀ ውስጥ የብርቱካን ልጣጭንና ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨውን ጨምሮ ማፍላት ማዋሀድና መጠጣት የመጠጥ ያደረ ስሜትን (hangover) ለማሻልም ያግዛል፡፡