AMN-Addis Media Network

AMN-Addis Media Network This is the official page of AMN- Addis Media Network ‘Voice of generation.’ stay connected🤳
(1)

28/07/2025

ሀገራት እያንዳንዱ የልማትና እድገት እቅዳቸውን ከምርት አቅርቦትና ከስርዓተ ምግብ መረጋገጥ ጋር የተሳሰረ ማድረግ እንዳለባቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ገለጹ፡፡ ዋና ጸሀፊው በበየነ መረብ ለ2ኛው የምግብ ስርዓት ጉባኤ ታዳሚዎች ባስተላለፉት መልእክት የምግብ ስርዓትን ለማረጋገጥ ዓለምአቀፍ የፋይናንስ አቅርቦት ፍትሃዊ ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

28/07/2025

የአፍሪካ ምርቶች ባለም አቀፍ ገበያ እንዲዳረሱ ጣሊያን ድጋፍ እንደብታደርግ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ተናገሩ፡፡
2ኛው ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ስርአት ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

28/07/2025

በመሪዎች እራት ግብዣ ላይ የቀረበ መዝናኛ

28/07/2025

ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ መክፈቻ

ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹAMN- ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከቤተሰብ ጀምሮ የምግብ ዋስትናን ለማ...
28/07/2025

ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ከቤተሰብ ጀምሮ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰደች መሆኑን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

የአየር ንብረት ለውጥና የተለያዩ ግጭቶች የዓለም የምግብ አቅርቦትና ዋጋ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተጠቁሟል።

በፈረንጆቹ 2025 የዓለም የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ሁኔታ ሪፖርት ይፋ ተደርጓል።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ የጎንዮሽ ኹነቶች እየተከናወኑ ናቸው።

ከኹነቶቹ መካከል በፈረንጆቹ 2025 የዓለም የምግብ ዋስትናና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ሁኔታን የተመለከተ ሪፖርት ይፋ ማድረጊያ አንዱ ነው።

በሪፖርቱ ይፋ ማድረጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሀመድን ጨምሮ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በሪፖርቱ ይፋ ማድረጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣውን የምግብ ዋጋ መናር የጋራ መፍትሔ ያስፈልገዋል ብለዋል።

የምግብ ዋጋ መናር በተለይም አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን የበለጠ የሚጎዳ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህን ችግር ለመፍታት ሀገራት የጋራ ትብብርና መፍትሔ ሊኖራቸው እንደሚገባ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ፣ በተለይም በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሌማት ትሩፋት መርሐ- ግብር ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።

በሴፍትኔት መርሐ-ግብርም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

በዓለም ላይ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦትን ለማረጋገጥ ሰላምን ለማፅናት ሀገራት በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባም ነው ያመለከቱት።

የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሀመድ በበኩላቸው፣ በምግብ ዋጋ እየጨመረ መምጣት በርካታ የዓለም ዜጎች የምግብ ዋስትናቸው እንዳይረጋገጥ ማድረጉን ነው ያነሱት።

የአየር ንብረት ለውጥና የተለያዩ ግጭቶች የዓለም የምግብ አቅርቦትና ዋጋ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸውንም አንስተዋል።

በዓለም በርካታ ህፃናት በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው መቅረታቸውንም ነው የገለጹት።

በዓለም ላይ ግጭትን ማስቀረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለዚህ ደግሞ የጋራ ትብብርና ተግባራዊ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የተፈጥሮ አደጋዎችና ግጭት ለጤና አስፈላጊ ምግቦች አቅርቦት ላይ እጥረት ፈጥሯል።

ይህ የምግብ ሥርዓት መዛባት በርካታ ዜጎችን ለጤና እክል ተጋላጭ ማድረጉንም አንስተዋል።

የዓለም መንግስታት የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በምግብ ሥርዓት ላይ እያደረሰ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመከላከል የበለጠ ትብብራቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ማመላከታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

28/07/2025

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካን ጋር ያደረጉት ቆይታ

28/07/2025

የሚሰሩ እጆች ወግ - ክፍል 2

28/07/2025




የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም አፍሪካ ዓለም የደረሰበትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት በራሷ መንገድ በመቀየስ የተስፋ ጎህ እየፈነጠቀባት እንደሆነ ማሳያ መሆኑን የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተ...
28/07/2025

የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም አፍሪካ ዓለም የደረሰበትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት በራሷ መንገድ በመቀየስ የተስፋ ጎህ እየፈነጠቀባት እንደሆነ ማሳያ መሆኑን የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ

AMN- ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም አፍሪካ የኋላቅርነት ትርክትን በመቀየር ዓለም የደረሰበትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት በራሷ መንገድ በመቀየስ የተስፋ ጎህ እየፈነጠቀባት የምትገኝ አህጉር ስለመሆኗ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ ጋር በመሆን የሳይንስ ሙዚየምን ጎብኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ጉብኝታቸው በቴክኖሎጂው መስክ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚረዳ አመላክተዋል።

የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም አፍሪካ የኋላቅርነት ትርክትን በመቀየር ዓለም የደረሰበትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት በራሷ መንገድ በመቀየስ የተስፋ ጎህ እየፈነጠቀባት የምትገኝ አህጉር ስለመሆኗ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

አቶ ተመስገን በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ እና ኩባ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ ጉዳዮች ዙሪያ ትብብራቸውን ለማጠናከር እና በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

አልጋ በሚያከራዩ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀAMN- ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም አልጋ በሚያከራዩ ቤቶች ላይ በተ...
28/07/2025

አልጋ በሚያከራዩ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ

AMN- ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

አልጋ በሚያከራዩ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎች ከመሰል ጥይቶች ጋር መያዙን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ሚዲያ ባደረሱት መረጃ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የከተማውን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግና አጠራጣሪ ጉዳዮች ባጋጠሙበት ወቅት ጭምር ድንገተኛ ፍተሻና አሰሳ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ልዩ ቦታው 32 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ አልጋ ቤቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ፣ አራት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከ298 ጥይቶች ጋር መያዙን ገልፀዋል፡፡

ፖሊስ ሁል ጊዜም ህብረተሰቡን የፀጥታ ስራው አጋር በማድረግ የከተማውን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ ሽፍት በማጠፍ ጭምር የወንጀል መከላከል ተግባራቱን እያከናወነ መሆኑንና የተገኘው ውጤትም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳታፊ የነበሩት ፍቃዱ ማናየ፣ አዳነች ጎበዜ፣ ዮሀንስ ፍቃዱ እና ዮናስ በቀለ ላይ ተገቢው ምርመራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን በማሰባሰብ በህግ አግባብ ለማስጠየቅ እንደሚሰራ ፖሊስ ማስታወቁን ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል፡፡

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ማዘዋወርም ሆነ መጠቀም በህግ የሚያስጠይቅ ድርጊት መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያ ለሚገኝ የፀጥታ አካል መረጃ መስጠት እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

28/07/2025

ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል እና አስተማማኝ ስርዓተ ምግብን ዕውን ለማድረግ በዘረጋችው መዋቅርና በነደፈችው እቅድ ውጤታማ ስራዎችን መስራቷን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡ 2ኛዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

28/07/2025

"ዜና አዲስ"

AMN - ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም የቀን 6፡00 ዜና

Address

5 Kilo
Addis Ababa
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AMN-Addis Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to AMN-Addis Media Network:

Share

Addis Media Network (AMN)

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤኤምኤን) አዲስ ቴሌቭዥን ለተሻለ ጥራት በመስራት ላይ ይገኛል በመሆኑም

በ satellite -NSS 12 ethio sat HD

Freq- 11165 mhz

polarization - Horizontal