13/07/2026
ከነዓን ማርክነህ የኩዌቱን ክለብ ተቀላቀለ
***********
ኢትዮጵያዊው ሁለገብ ተጫዋች ከነዓን ማርክነህ ወደ ኩዌት በማምራት በሊጉ አራተኛ ሆኖ ላጠናቀቀው አል አረቢ ክለብ የአንድ አመት ውል ፈርሟል።
የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ አዳማ ከተማ ፣ መቻል እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአማካይ እና የመስመር ተጫዋች ከነዓን ማርክነህ በተጠናቀቀው አመት በኦማን ፕሪምየር ሊግ 21 ጎሎችን በማስቆጠር የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ መጨረሱ በከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር ወደ ኩዌቱ ክለብ እንዲያመራ ምክንያት ሆኗል።