LELA News

LELA News Amharic News Media

ጋዜጠኛዋ ቢሊኒየሩን ቃለመጠይቅ እያደረገችለት ነው... "የስኬትህ ሚስጥር ምንድነው?"ቢሊየነሩ ባዶ ቼክ ለጋዜጠኛዋ አቀበላትና "የፈለግሽውንያህል ገንዘብ ፃፊበት" አላት!ጋዜጣኛዋ በእንቢታ ቼ...
19/09/2025

ጋዜጠኛዋ ቢሊኒየሩን ቃለመጠይቅ እያደረገችለት ነው... "የስኬትህ ሚስጥር ምንድነው?"
ቢሊየነሩ ባዶ ቼክ ለጋዜጠኛዋ አቀበላትና "የፈለግሽውን
ያህል ገንዘብ ፃፊበት" አላት!
ጋዜጣኛዋ በእንቢታ ቼኩን እየመለሰች ‹‹አይ እኔ እንደሱ
አይነት ነገር ፈልጌ አይደለም የስኬት ሚስጥሮን መጠየቅ ፈለጌ እንጂ›› አለች።
ቢሊየነሩ ድጋሚ ቼኩን መልሶ ሰጣትና ‹‹የፈለግሽውን ያህል ገንዘብ ፃፊ›› አላት።
ጋዜጠኛዋ እንቢ አሻፈረኝ አለች።
ቢሊየነሩ ቼኩን እያሳያት ‹‹የስኬቴ ሚስጥር አሁን አንቺ ያጋጠመሽን አይነት እድል አሳልፌ አለመስጠቴ ነው... የስኬቴ ሚስጥር ያገኘሁትን እድል ሁሉ መጠቀሜ መው፡፡
አሁን አንቺ እንድልሽን ተጠቅመሽ ቢሆን ኖሮ የአለማችን ሃብታሟ ጋዜጠኛ ትሆኚ ነበር... እኔ ሁለቴ እድል እንደሰጠሁሽ አለም ሁለት እድል አትሰጥሽም አንዴ ያጋጠመሽን እድል መጠቀም የስኬት ሚስጥር ነው››
[Book_for_all]

17/09/2025

እራስህ በቀረጽከው ስርዓት ትምህርት ( Curriculum)ና ባዘጋጀኸው የማስተማርያና የመማርያ ግብአት ላይ ተመርኩዘህ ለአራት ዓመት ያስተማርከው ሀገር ተረካቢ ትውልድ በአምስት መቶ ሺዎች ፈተና ሲወድቅ ድንኳን ጥለህ ማቅ ለብስ በራስህ ውድቀት ማዘንና መጸጸት ሲገባህ በትውልዱ ኪሳራ ላይ መዘባበትና ማላገጥ በውስጥህ የሰረጸ የጥላቻ መንፈስ ካልኖረህ በስተቀር ታዳጊ ልጅ ባለው ሰው አንጀት የሚቻለው አይደለም።

ላለፉት አራት ዓመታት በቢሊዮኖች የወጣበትና በየመድረኩ ሲደለቅለት የከረመው የትምህርት ስርዓት ኩረጃን ከመከላከል ባሻገር እስከ አሁን አንዳችም የፈየደው ነገር እንደሌለ ዘንድሮም አስረግጦ አልፏል። ፈተና ያለፉት ተማሪዎች የፐርሰንትም ሆነ የቁጥር እድገትም በየዓመቱ በሚሊየኖች የሚጨምረው የተማሪዎች አንጻራዊ የተፈታኝ ቁጥር እድገት ተጽኖ እንጂ መሬት የወረደ ወሳኝ የቁጥር ለውጥ እንዳልሆነ ተራ ስሌት የሚያስረዳን ሆኗል።

ከዚህ በላይ የሚያሳስበው ነገር በቀረበው ግርድፍ መረጃ መሰረት ኢንተርናሽናል ት/ቤቶች 85%፣ የግል ት/ቤቶች ከ50% በላይ አዳሪ ት/ቤቶች 100% ማሳለፋቸውና በተቃራኒው በርካታ የአርሷ አደርና የአርብቶ አደር ልጆች የሚማሩባቸው የመንግስት ት/ቤቶች 5% ገደማ ተማሪ ማሳለፋቸው ጉዳይ ነው።

ይህ የሚስረዳን ነገር ቢኖር ስርዓት ትምህርቱ ና የፈተናው ውጤት ከዓመት ወደ ዓመት ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃና በንጽጽር በኑሮ ደረጃቸው አቅመ ደከማ የሆኑ የማህበረሰባችን አካላት ልጆችን ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መገለላቸው ተጠናክሮ የመቀጠሉ ክስተት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ነው።

በዚህ መሰረትም "አዲስ" የተባለለት ስርዓተ ትምህርት ድሃና ሀብታምን ሳይለይ ትምህርትን በአንጻራዊነት በእኩል ደረጃ ለሁሉም ማዳረስ፣ ማስፋፋትና ሚዛናዊ ዉጤትን ማስጠበቅ ሲኖርበት በአጼ ሐይለ ስላሴ ዘመን እንደ ተዘመተበት (Secter Review) ትምህርት በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የአርሶ አደርና የአርብቶ አደር ልጆችን ዳር በማስያዝ ከፍተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ወላጆች ልጆችን ቀጣይነት ባለው መንገድ ባለመብት የሚያደርግና በዚሁ መንገድ ውጤቱ እየተዛባና እያገለለ እንደሚቀጥል እየተዘገበ አለማስደንገጡና አለማወያየቱ አስደማሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

በአጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱ የአራት ዓመት ግምገማ የተማሪ ጥራትና የቁጥር እድገት ያልታየበት፣ የመማር ማስተማር፣ የተማሪና መምህር ጥመርታ ያልተሰናሰለበት፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የአርሶ አደር፣ የአርብቶ አደር ልጆች በከፍተኛ ደረጃ ከከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚነት ያገለለ፣ ጥግ ያስያዘና በ4 ዓመት ውስጥ ከ2 ሚሊየን በሚበልጡ ወጣቶችን መነሻና መዳረሻ ያሳጣ ሆኗል።

እንደዚህ ዓይነት የትውልድና የሀገር ተስፋን ጥያቄ ላይ የሚጥል ስርዓት ትምህርት ለምን፣ እንዴትና ወዴት በሚሉ መሰረታዊ መስፈርቶች በገለልተኛ አካለትና በባለሙያዎች ኦዲት ተደርጎና ተገምግሞ ወደ ተገቢው አቅጣጫ እንዲያመራ በማድረግ ወጣቱን ከመደናበርና ተስፋ ከመቆረጥ ቤተሰብን ከጭንቀትና ከሐዘን መታደግ ይገባል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ።

በተለይ ደግሞ በየዓመቱ መጨረሻ ላይ በከፍተኛ እርካታና አጀብ ተማሪና ሕዝብን በሚያሳዝን መልኩ የሚዘገበው ከ500 ሺህ የሚልቁ ታዳጊ ልጆች ወድቀትና ኪሳራ ከስሜዊነት ተላቆ ሙያዊ በሆነና በሰከነ መንገድ በጥንቃቄ እንዲዘገብ ሙያ ከባለሙያው ጋር እንዲገናኝ ክንዋኔው ወደ ሚኒስትሩ የሕዝብ ግንኙነት ሊመለስ ይገባዋል።
(ከሙሼ ሠሙ)

Charlie Kirk has passed away at the age of 31 following the sho*ting in Utah Valley University.
11/09/2025

Charlie Kirk has passed away at the age of 31 following the sho*ting in Utah Valley University.

አቶ ማሞ  ምህረቱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ም/ ፕሬዚዳንት ሆኑ  | ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን ያገለገሉት አቶ ማሞ  ምህረቱ፤ የአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ፕ...
05/09/2025

አቶ ማሞ ምህረቱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ም/ ፕሬዚዳንት ሆኑ

| ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን ያገለገሉት አቶ ማሞ ምህረቱ፤ የአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆኑ፡፡

አቶ ማሞ ምህረቱ በትላንትናው ዕለት ከብሔራዊ ባንክ ኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ያስታወቁ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

አቶ ማሞ በአሜሪካ ከሚገኘው የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ኬኔዲ ትምህርት ቤት በአመራር፣ በፐብሊክ አስተዳደርና በኢኮኖሚ ልማት ማስተርስ አግኝተዋል።

ከፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲና ከአምስተርዳም ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በንግድና ኢንቨስትመንት የማስተርስ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ሲመረቁም የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ እንደነበሩ ተጠቁሟል፡፡

አሳዛኝ መርዶ:-ታላቋ ጋዜጠኛና ደራሲዋ የምወድሽ በቀለ አረፈች።የምወድሽ በቀለ የፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆና ረጅም አመታት አገልግላለች። በድርሰትና በስነ ግጥም ስራዎቿም በርካታ...
30/08/2025

አሳዛኝ መርዶ:-

ታላቋ ጋዜጠኛና ደራሲዋ የምወድሽ በቀለ አረፈች።

የምወድሽ በቀለ የፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆና ረጅም አመታት አገልግላለች።

በድርሰትና በስነ ግጥም ስራዎቿም በርካታ አበርክቶዎች የነበሯት ነበረች። በ1979 ዓ.ም አብዮታዊ ግጥሞች ከሚለው ስራዋ ጀምሮ ወደ 16 መፃሕፍትን አሳትማለች።

የኢትዮጵያ ሴት ደራሲያት ማሕበርን በፕሬዘደንትነት ዘለግ ላሉ አመታት መርታለች።

የኢትዮጵያ ሴቶች ማሕበራት የቦርድ ሰብሳሰቢ ሆና አገልግላለች።

ሴቶች ይችላሉ Women can do it የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት መስራችና ዋና ዳይሬክተር ነበረች።

እጅግ በርካታ የበጎ ስራ ማሕበራት ውስጥ መስራችና አመራር ሆና ስታገለግል ኖራለች።

በሴቶች፣ በሕፃናት እና ማሕበረሰብ አቀፍ የበጎ ስራዎች ላይ ከፊት ተሰልፋ ሙሉ ጊዜዋን ስትሰራ ቆይታለች።

በአሐዱ ሬዲዮ ላይ ከምወድሽ ገፆች የተሰኘ በሴቶች ላይ ያተኮረ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ነበረች።

በአሻም ቴሌቪዥን የሚተላለፍም የምወድሽ ገፃች አዘጋጅ ናት።

በሕይወት ዘመኗ በርካታ ሽልማቶችንም ባበረከተቻቸው አስተዋፅኦዎች አግኝታለች። የ2016 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማትን ጨምሮ ሌሎችንም አግኝታለች።

ነሐሴ 19 ቀን 1951 ዓ.ም አዲስ አበባ የተወለደችው የምወድሽ በቀለ የአራት ልጆች እናትና የ5 የልጅ ልጆች አያት ነበረች።

የብዙ አቅመ ደካሞች ጧሪ እና ደጋፊ የነበረችው ደራሲዋ ጋዜጠኛዋ የምወድሽ በቀለ ለአጭር ጊዜ ባጋጠማት ሕመም በሕክምና ስትረዳ ቆይታ ዛሬ ነሐሴ 23 ቀን ሌሊት አርፋለች። የቀብር ስነስርአቷም ነገ የሚፈፀም ሲሆን ቦታውንና ሰአቱን እንደደረሰን እንገልፃለን።
ቀብር
የአንጋፋዋ ደራሲ የምወድሽ በቀለ የቀብር ሥነ ሥርዐት ነገ፣ እሁድ ነሐሴ 25 ቀን 2017ዓ.ም አየር ጤና ኪዳነ ምህረት ቤተክርሲትያን ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ይፈፀማል ።

በታላቋ ደራሲት እና ጋዜጠኛዋ የምወድሽ በቀለ ዜና ዕረፍት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልፃለን።

ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) አዲስ ዋና/ሥ/አስፈጻሚ ተመደበ   #ቢንያምኤሮ የማህበረሰብ ሳይንስ ምሩቁ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል። #ጌትነትታደ...
27/08/2025

ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) አዲስ ዋና/ሥ/አስፈጻሚ ተመደበ

#ቢንያምኤሮ የማህበረሰብ ሳይንስ ምሩቁ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።

#ጌትነትታደሰ ባለፋው ሳምንት ነሐሴ 14 /2017 ከኢቢሲ ኃላፊነት ተነስተው ነው በምትካቸው - የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የክትትል፣ ኢንስፔክሽንና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ናቸው የተተኩት።

ተወዳጅ ሚድያ እንዳጋራው አቶ ቢንያም ኤሮ በኢንሳ እና በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገለገሉ እና በ2013 ደግሞ EBCን ተቀላቅለው የሳይበር ክፍል ኃላፊ ሆነው ሰርተው ነበር።

አቶ ቢንያም ኢንሳ 4 አመት ያገለገሉ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውንም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነው ያጠናቀቁት።

ፓርላማው ሥራ ሲጀምር አቶ ቢንያም ኤሮ የኢቢሲ ዋ/ሥ/አስፈጻሚ ሆነው ቃለ መሀላ እንደሚፈጽሙ ይጠበቃል።

እሸቱ ገለቱ

ባሳለፍነው ሳምንት ታፍነው ተወስደው የነበሩ ሶስት ጋዜጠኞች ማምሻውን ተፈቱ !መሠረት ሚድያ ዛሬ ማምሻውን የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው ታፍነው ተወስደው የነበሩት ጋዜጠኞች አብዱልሰመድ መሐመ...
23/08/2025

ባሳለፍነው ሳምንት ታፍነው ተወስደው የነበሩ ሶስት ጋዜጠኞች ማምሻውን ተፈቱ !

መሠረት ሚድያ ዛሬ ማምሻውን የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው ታፍነው ተወስደው የነበሩት ጋዜጠኞች አብዱልሰመድ መሐመድ፣ ዮናስ አማረ እና ሐሰን ሰይድ ከእስር ተለቀው በተለያዩ የአዲስ አበባ ስፍራዎች ተለቀው ተገኝተዋል።

በፍርድ ቤት ችሎት ውስጥ ከህግ አንቀጾች ይልቅ የሰውን ልጅ ሰብዓዊነት ያስቀደሙትና በሚሊዮኖች ዘንድ "ርህራሄ ሙሉው ዳኛ" በሚል ስያሜ የሚታወቁት  ፣ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለ...
21/08/2025

በፍርድ ቤት ችሎት ውስጥ ከህግ አንቀጾች ይልቅ የሰውን ልጅ ሰብዓዊነት ያስቀደሙትና በሚሊዮኖች ዘንድ "ርህራሄ ሙሉው ዳኛ" በሚል ስያሜ የሚታወቁት ፣ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የእሳቸው ህልፈት፣ ለ40 ዓመታት ያህል ባገለገሉበት የፕሮቪደንስ ማዘጋጃ ቤት ፍርድ ቤት ብቻ ሳይሆን፣ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድናቂዎቻቸው ልብ ውስጥም ትልቅ ክፍተት ጥሎ አልፏል።

የፍራንክ ካፕሪዮ ዝና የመጣው ከተለመደው የዳኝነት ስራቸው አልፎ፣ "Caught in Providence" በተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራማቸው ነበር። ይህ ፕሮግራም፣ የሳቸውን የፍርድ ቤት ችሎት በቀጥታ ለተመልካች የሚያቀርብ ሲሆን፣ ዳኛ ካፕሪዮ ከሳሾችንና ተከሳሾችን የሚያስተናግዱበት መንገድ ግን ፈጽሞ የተለየ ነበር። በፊታቸው የሚቀርቡት ሰዎች የትራፊክ ጥሰት ፈጽመው አልያም ሌላ ቀላል ወንጀል ሰርተው ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ዳኛ ካፕሪዮ ከድርጊቱ ጀርባ ያለውን ታሪክ በጥሞና ያዳምጡ ነበር።

የኑሮ ውጣ ውረድ የጎዳውን፣ ልጁን ለማሳከም ሲል የተቸገረውን፣ ወይም በህይወት አጋጣሚ ተገፍቶ ስህተት የሰራውን ሰው ሁሉ በእናትና አባት ርህራሄ ይቀበሉ ነበር። ከቅጣት ይልቅ ምህረትን፣ ከግልምጫ ይልቅ ፈገግታን እየመረጡ፣ ለብዙዎች ሁለተኛ እድል ይሰጡ ነበር። ችሎታቸው የህግ መጽሐፍትን መተንተን ብቻ ሳይሆን၊ የተሰበረ ልብን መረዳትም ጭምር ነበር።

ይህ ሁሉ ርህራሄ የመነጨው ከራሳቸው የህይወት ተሞክሮ ነበር። በፕሮቪደንስ፣ ፌደራል ሂል ተብላ በምትጠራው አካባቢ በድሃ ቤተሰብ ውስጥ ያደጉት ፍራንክ፣ በልጅነታቸው ጫማ በመጥረግ፣ ጋዜጣ በማከፋፈልና ወተት የጫነ መኪና ላይ በመስራት ቤተሰባቸውን ያግዙ ነበር። የወላጆቻቸውን ታታሪነትና የሌሎችን ህይወት ለማሻሻል ያላቸውን ፍላጎት አይተው በማደጋቸው፣ በሰው ልጅ መልካምነት ላይ የማይናወጥ እምነት አዳብረዋል።

ከትምህርት ሳይዘናጉ፣ ከሴንትራል ሃይስኩልና ከፕሮቪደンス ኮሌጅ ተመርቀዋል። ከዚያም በቀን የአሜሪካ መንግስት ታሪክን በሆፕ ሃይስኩል ሲያስተምሩ፣ በማታ ደግሞ በቦስተን በሚገኘው የሰፎልክ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርታቸውን ይከታተሉ ነበር። ይህ የትጋትና የጽናት ጉዞ፣ በ1985 የዳኝነት ወንበር ላይ እንዲቀመጡ አበቃቸው።

ከፍርድ ቤቱ ባሻገርም፣ ዳኛ ካፕሪዮ ለማህበረሰባቸው ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። በሮድ አይላንድ የከፍተኛ ትምህርት ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን ለ10 ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን፣ በስማቸውና በአባታቸው ስም በርካታ የነፃ ትምህርት እድል ፈንድ በማቋቋም፣ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው አካባቢዎች ለሚመጡ ተማሪዎች የህግ ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን አስችለዋል።

ባለፈው ዓመት በጥር 2023፣ ለ40 ዓመታት ከቆዩበት የዳኝነት ስራቸው ጡረታ የወጡት ዳኛ ፍራንክ ካፕሪዮ፣ በህይወት ዘመናቸው የሰጧቸው ፍርዶች በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ እንደማይፋቅ አሻራ ጥለው አልፈዋል። ልጃቸው እንዳለው፣ እሳቸው የተከበሩ ዳኛ ብቻ ሳይሆኑ፣ ተወዳጅ ባል፣ አባት፣ አያትና ቅም አያትም ነበሩ። የዳኛ ካፕሪዮ መዶሻ ቢያርፍም፣ ያስተማሩት የደግነትና የርህራሄ ትምህርት ግን በብዙዎች ህይወት ውስጥ ለዘላለም ይኖራል።
(ዘ ሐበሻ)

አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አረፈአንጋፋው የኪነ ጥበብ ሰው ተዋናይ፣ ኮሜዲያን እና አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት በሙያው ሀገሩን አገልግሏል።ደበበ እሸቱ የመድረክ መሪ ፣...
17/08/2025

አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አረፈ

አንጋፋው የኪነ ጥበብ ሰው ተዋናይ፣ ኮሜዲያን እና አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት በሙያው ሀገሩን አገልግሏል።

ደበበ እሸቱ የመድረክ መሪ ፣ የሬዲዩ እና የቴሌቪዥን ድራማና ፊልሞች ተዋናይ እንዲሁም ጋዜጠኛም ነበር።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል

የአንጋፋው ሪፖርተር ጋዜጣ ባልደረባ ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ማንነታቸው ባልታወቁና ጭምብል ባደረጉ ሰዎች መወሰዱ ተጠቆመጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ላለፉት አራት ቀናት ማለትም ከነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ...
16/08/2025

የአንጋፋው ሪፖርተር ጋዜጣ ባልደረባ ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ማንነታቸው ባልታወቁና ጭምብል ባደረጉ ሰዎች መወሰዱ ተጠቆመ

ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ላለፉት አራት ቀናት ማለትም ከነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ባለመግባቱ በእጅ ስልኩ ላይ ቢደወልለትም ሆነ ከቤተሰቦቹ ለማጣራት ቢሞከርም ማግኘት አልተቻለም።

በሥራ ላይ እያለ የገባበት በመጥፋቱ የሥራ ባልደረቦቹም ሆኑ የሚቀርቡት ጓደኞቹ በእጅ ስልኩ ላይ ቢደውሉም ማግኘት አልተቻለም።

ጋዜጠኛ ዮናስ በሚኖርበት በሸገር ከተማ ኮዬ ፌጬ ኮንዶሚኒዬም በመሄድ በተደረገ ማጣራት፣ ጋዜጠኛው የተወሰደው ረቡዕ ምሽት ፊታቸውን በጭምብል በሸፈኑ ሰዎች መሆኑን ባካባቢው ካሉ የጥበቃ ሠራተኞች ለማወቅ ተችሏል።

የጥበቃ ሠራተኞቹ ተጨማሪ መረጃ መስጠት ባለመቻላቸው፣ ጋዜጠኛ ዮናስ፣ እነማን እንደወሰዱትና የት እንደተወሰደ ማወቅ አልተቻለም።

በተመሳሳይ ሁኔታ ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ ነሐሴ 5/2017 ተይዞ ቤተሰቦቹ ማግኘት አለመቻላቸውና ፍርድ ቤት አለመቅረቡ መዘገቡ ይታወሳል።
(ምንጭ:- ሪፖርተር)

የአንድ አመት ከስምንት ወር እድሜ ያለውን ህፃን በማገት ሁለት ሚሊዮን ብር የጠየቁ እና በወንጀሉ ተባብረዋል የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉወንጀሉ የተፈፀመው ሀምሌ 30 ቀን 2...
13/08/2025

የአንድ አመት ከስምንት ወር እድሜ ያለውን ህፃን በማገት ሁለት ሚሊዮን ብር የጠየቁ እና በወንጀሉ ተባብረዋል የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ወንጀሉ የተፈፀመው ሀምሌ 30 ቀን 20017 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 1፡40 ሰዓት ገደማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አፍሪካ ህብረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ፋኑኤል ብርሃነ የተባለን የ1 አመት ከ8 ወር ዕድሜ ያለውን ህፃን ከመኖሪያ ቤቱ በስውር በመውሰድ ወደ ወላጅ አባቱ ስልክ ደውለው ህፃኑን እንዳገቱት በመግለፅ እና ሁለት ሚሊዮን ብር በአካውንት ገቢ እንዲያደርጉ በመጠየቅ በቤተሰብ ላይ ጭንቀትና ድንጋጤን ፈጥረዋል፡፡ አቶ ብርሃነ ገ/ፃዲቅ የተባሉት የህፃኑ ወላጅ አባትም ስለ ሁኔታው በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ በወቅቱ አሳውቀዋል።

የህፃኑ መጥፋት ሪፖርት የደረሰው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የቄራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የምርመራ እና የክትትል ክፍሉ ተቀናጅተው በተደረገ ከፍተኛ ጥረት ካህሳይ ተክላይ የተባለውን እና ከህፃኑ ወላጅ አባት ጋር ዝምድና ያለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡

የወንጀሉ አቀነባባሪ ነው ተብሎ ተጠርጥሮ በተያዘው በካህሳይ ተክላይ ላይ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ በህፃኑ እገታ ከሚገኝ ገንዘብ የጥቅም ተካፋይ ለመሆን በመስማማት ወንጀሉን የተባበሩ ፊሊሞን ገ/ማርያም፣ ተክሊት ህሉፍ እና ምህረት ዕድሉ የተባሉ ተጨማሪ ሶስት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

እነዚህ ተጠርጣሪዎች የተያዙት ወንጀሉ በተፈፀመ በማግስቱ ሳሪስ አካባቢ በሚገኘው ማራኪ በተባለ ሆቴል ውስጥ አልጋ ክፍል በመከራየት ህፃኑን ይዘው በተሸሸጉበት ወቅት ፖሊስ ባደረገው ክትትል ነው፡፡ በአጠቃላይ በወንጀሉ የተጠረጠሩት አራት ግለሰቦች በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፡፡

ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ከህግ ማምለጥ እንደማይችል ከዚህ ወንጀል በመረዳት ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ነገር በሚያጋጥመው ወቅት ለፀጥታ አካላት የመጠቆም እና መረጃ የመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ሠሞኑን በናሆም ሬከርድስ 🔥🔥 #አርካባስ     #አግራው   …..የተሠኙት የሙዚቃ ስራዎቿ  በሚልየኖች የታዩላት ተወዳጅ ድምፃዊት ናት ...  !!  በቅርቡ በአንጋፋዉ   የዩቲዩብ ቻናል ላይ...
13/08/2025

ሠሞኑን በናሆም ሬከርድስ 🔥🔥
#አርካባስ #አግራው …..የተሠኙት የሙዚቃ ስራዎቿ በሚልየኖች የታዩላት ተወዳጅ ድምፃዊት ናት ... !!
በቅርቡ በአንጋፋዉ የዩቲዩብ ቻናል ላይ የተለቀቀዉ እና በተሰኘ ስራዋም እንዲሁ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያገኘ እና በጥቂት ሳምንታት ዉስጥ ከ700 ሺህ በላይ ተመልካች አግኝቷል::
ይህች ወጣት ድምፃዊት አሁን ደግሞ #ሻደይ የተሠኘ አዲስ የሙዚቃ ቪድዮ ይዛ የመጣች ሲሆን ሠሞኑን የዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል!


(የናሆም ሬከርድስን የማህበራዊ ሚድያዎችን በመቀላቀል አዳዲስ ስራዎችን ቀድመው ይመልከቱ 🤩🤩) ሊንክ እዚህ አለ 👇👇
ዩቲዩብ 👇
https://YouTube.com/c/NahomRecordsIncMusic
ቴሌግራም 👉 https://t.me/nahomrecords
ቲክቶክ 👉 https://www.tiktok.com/
https://youtu.be/JzVF6EsQewk

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when LELA News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to LELA News:

Share