
30/07/2023
ዩክሬን ከሩሲያ ትውፊቶች ራሷን ለማራቅ የገና በዓልን ዕለት ቀየረች!
ዩክሬን የገና በዓል መላው ሩሲያን ጨምሮ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ከሚያከብሩበት ታህሳስ 29 ወደ ታህሳስ 16 ወይም ወደ ጎሮጎሳውያኑ ታህሳስ 25 እንዲዛወር ወሰነች።
ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ “ ከሩስያ የተወረሰውን የገና በዓል አከባበር ትውፊት” ለማስወገድ ያለመ የፓርላማ ህግን ፈርመዋል።
ዩክሬን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሩሲያ ጋር ያላትን ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ሌሎች ግንኙነቶችን በመቁረጥ ከምዕራቡ ዓለም ጋር አጋርነትን መርጣለች።
በተለይም ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ወረራም ተከትሎ የበለጠ እንዲፈራቀቁ አድርጓቸዋል።
የገናን በዓል የሚቀይረው ይህ ህግ ከጸደቀ ከሁለት ሳምንታት በኋላም ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ አርብ ዕለት ፈርመውበታል።
ህጉ በተጨማሪም ሌላ ሁለት የመንግሥት በዓላትንም ቀን አዛውሯል። የዩክሬን የአገር ምስረታ የተባለው ክብረ በዓልን ከጎሮጎሳውያኑ ሐምሌ 28 ወደ ሐምሌ 15 እንዲሁም የቀድሞ የጦር ዘማቾች የሚከበሩበት ዕለትም ከጥቅምት 14 ወደ ጥቅምት 1 እንዲዛወር መደረጉም ተገልጿል።
ሩሲያ እስካሁን ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠችም።
ምንጭ Bbc