ADBAR MEDIA አድባር ሚዲያ

ADBAR MEDIA አድባር ሚዲያ በቅድሚያ likeን ይጫኑ በዚህ ፔጅ ስለ እናት በስፋት ይዳሰሳል..?

 #የአፍሪካ ቢሊየነር ዝርዝር ወስጥ የገቡ ኢትዮጵያውያን #እስኪ ስማቸውንና የተሰማሩበትን ዘርፍ ፃፍ ብዙ ያወቀ ይሸለማል
06/08/2025

#የአፍሪካ ቢሊየነር ዝርዝር ወስጥ የገቡ ኢትዮጵያውያን
#እስኪ ስማቸውንና የተሰማሩበትን ዘርፍ ፃፍ ብዙ ያወቀ ይሸለማል

 #ከባድሚዛኑ #ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን (ዶ/ር) ሐምሌ  2 ቀን 2017 ዓ.ም በሚኖርበት አሜሪካ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።ሥርዓተ ቀብሩ ነገ ቅዳሜ  ሐምሌ 19 ቀን 2017...
25/07/2025

#ከባድሚዛኑ
#ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን (ዶ/ር) ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በሚኖርበት አሜሪካ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።

ሥርዓተ ቀብሩ ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ቤተሰቡ እና ወዳጆቹ በተገኙበት አራት ኪሎ በሚገኘው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል::

ቤተሰቦቹ
ነፍስን በአፀደ ገነት ያኑራት🙏

 #አስቸኳይ3 ወንድም እና እህታማቾች ጠፍተዋል::እባክዎ ያጋሩ!እነዚህ ሦስት ቆንጆ ህፃናት – * ሊሊ፣ * ሊዲያ እና * ዮሲ የ5 ዓመት፣እና የሰባት ዓመት ወንድም እና እህት ሲሆኑ ሐምሌ 8...
18/07/2025

#አስቸኳይ
3 ወንድም እና እህታማቾች ጠፍተዋል::
እባክዎ ያጋሩ!

እነዚህ ሦስት ቆንጆ ህፃናት –
* ሊሊ፣
* ሊዲያ እና
* ዮሲ

የ5 ዓመት፣እና የሰባት ዓመት ወንድም እና
እህት ሲሆኑ

ሐምሌ 8 ማክሰኛ ከቀኑ 6 ሰዓት ተኩል አካባቢ ለቡ አካባቢ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ጀርባ የከንቲባ ቤትወደድ መታሰቢያ በሚባል የሚታወቀው (Public Park) የህፃናት መጫወቻ ጠፍተዋል

እናታቸው እባካችሁ ኢትዮጵያውያን አፋልጉኝ እያለች እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ሲሆኑ፣

እነርሱን ለማግኘት ማንኛውም አይነት እገዛ በአስቸኳይ ያስፈልጋል። ካያችኋቸው ወይም ማንኛውም መረጃ ካላችሁ፣

እባክዎ ወደዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ፡
📞 0982410715 እናታቸው

እባክዎ ይህን መልዕክት በስፋት በማጋራት ህፃናቱ በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያድርጉ።

የእርስዎ አንድ ሼር ትልቅ ለውጥ
ሊያመጣ ይችላል።

እናመሰግናለን!

Via እናታቸው ነኝ

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

በማድረግ ብዙዎች ጋር እናድርሰው

   #ምንተማራችሁበትድግሱ ሲያልቅ እንግዶቹ ይሄዳሉ  | "ከማንችስተር ዩናይትድ ከፍተኛ ደሞዜን ስቀበል በጣም ደስተኛ ነበርኩ" አባቴም በዛ ወቅት "ልጄ ሆይ ገንዘብህን አታባክን ድግሱ ሲያል...
05/07/2025


#ምንተማራችሁበት
ድግሱ ሲያልቅ እንግዶቹ ይሄዳሉ

| "ከማንችስተር ዩናይትድ ከፍተኛ ደሞዜን ስቀበል በጣም ደስተኛ ነበርኩ" አባቴም በዛ ወቅት "ልጄ ሆይ ገንዘብህን አታባክን ድግሱ ሲያልቅ እንግዶቹ ይሄዳሉ አንተ ብቻህን ትቀራለህ" አለኝ.....

"ችግር እስኪገጥመኝ ድረስ እነዚህን ቃላት አልገባኝም ነበር እና ብዙ ጓደኞቼ በየግዜው ይመጡ ነበሩ:: ጓደኞቼ ግን እኔን ለማየት እንዳልመጡ አስተውል ነበር። በችግሬ ወቅት ግን አጠገቤ የነበሩ ሰዎች የቅርብ ቤተሰቤ ብቻ ናቸው። ይህ ሕይወት ነው!!

"ሚስቴ እንኳ ልክ ከእግርኳስ ጨዋታ ስታገድ እና ዝናዬም ሲጠፋ ከእኔ ራቀች። ሚስቴ ከእኔ ጋር የነበረችው ለገንዘብ እና ለዝና ብቻ ነበር።"

ፖል ፖግባ






ትርጒምና እረፍት መፈለግ (የሰንበት ዳረጎት)ሙሉ ካላነበባችሁ አትጀምሩት(አደራ ይጠቅማችኋል ዝለቁት)  እሑድ የድባቴና እየታረፈ የሚደከምበት ቀን እየሆነ ነው። አዎ የምላችሁ እውነት ነው። እ...
04/07/2025

ትርጒምና እረፍት መፈለግ (የሰንበት ዳረጎት)
ሙሉ ካላነበባችሁ አትጀምሩት
(አደራ ይጠቅማችኋል ዝለቁት)

እሑድ የድባቴና እየታረፈ የሚደከምበት ቀን እየሆነ ነው። አዎ የምላችሁ እውነት ነው። እሑድ የድብርት ቀን ነው። ማኅበራዊ ሳይንስ አጥንቶ የደረሰበት እውነታ ነው። ለምን እና በየት ሀገር በእነማን ዘንድስ የሚለውን ልንገራችሁ። አብዛኛው የምዕራቡ ዓለም ሕይወት በሥራ ሥራም በሕይወት ብሎ የሚኖር ነው። ሕይወቱን የሚመለከተው ከራሱ ግለሰባዊ ነፃነትና ሥራ ጋር ብቻ ነው። ለማኅበራዊ አንድነት፣ ለመንፈሳዊ ሕይወት፣ ለቤተሰባዊ ኅብረት የሚተጉት እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው።

ታዲያ እነዚህ በሰባቱ ዕለታት ዑደት ልክ እየተሽከረከሩ በዓመት አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ እረፍት የሚወጡበትን ብቻ ተስፋ እያደረጉ የሚኖሩ የምዕራቡ ዓለም ሕዝቦች ከሰኞ እስከ አርብ አብዝተው ይሠራሉ። ቅዳሜ ገበያ ወጠው ሲሸምቱ ይውላሉ። ወደማታ ወጣ ብለው ይበላሉ ይጠጣሉ ወጣቶች ደግሞ ወደ ጭፈራ ቤቶች ዘልቀው እንዳልሆነ ሲሆኑ ያድራሉ።

አንዳንድ ቀን ሌሊት 11 ሰዓት ወደ ቤተ ክርስቲያን ስሄድ ብዙዎች ተበላሽተው በየመንገዱ ወድቀው ሳያቸው እጅጉን አዝናለሁ። ለእኛ ሲነጋ ለእነርሱ መሸ እላለሁ። እነዚህ በየጭፈራና መጠጥ ቤቱ ያመሹትም ሆኑ ጠንካራ ቤተሰባዊ ጉድኝት የሌላቸው የምዕራቡ ዓለም ሰዎች (አሁን አሁን እኛም ሀገር እየገባ ይመስለኛል) ቅዳሜን ካለ ልክ በመባለግና በመጠጣት ገንዘባቸውንም በማውጣት እሑድ ደግሞ የቅዳሜው ድካም፣ ስካር፣ ዱካክ ያለ አግባብ ያጠፉት ገንዘብ ጸጸት ቀናቸውን ያጨልምባቸዋል። በዚያም ላይ አብዛኛው ነገር ስለሚዘጋና ጸጥ ስለሚል ሥራም ስለሌለ በውስጣቸው ያለው ባዶነት መገለጥና የሕይወታቸው ከንቱነት ይታያቸዋል። የሚይዙት የሚጨብጡት ይጠፋቸዋል።

የምወደው ታላቁ ሳይንቲስት ፕ/ር ቪክተር ፍራንክል ይህን ጉዳይ “Sunday neurosis is a kind of depression which afflicts people who become aware of the lack of content in their lives when the rush of the busy week is over and the void within themselves becomes manifest.፤ የእሑድ ድባቴና ጭንቀት በሕይወታቸው ውስጥ ትርጒምና እርባና የማይታያቸው ሰዎች የወከባው ሳምንት አልፎ ሁሉ ጸጥ በሚልበት ወቅት በውስጣቸው ያለው ባዶነት ሲገለጥ የሚመጣ ድብርት ነው” ሲል ገልጦታል።

በግሌ ካየኋቸው በጣም ብዙ ወደ ውጭ ሀገር የሚመጡ ተማሪዎች በተለይ ሴቶች በጣም ከፍተኛ የሆነ የብቸኝነትና የድብርት ስሜት ውስጥ የሚገቡት ከሌላው ቀን በተለየ በዕለተ እሑድ ነው። ብዙ ስዎች ራሳቸውን የሚያጠፉት ወይም የማጥፋት ሙከራ የሚያደርጉትም እንዲሁ በዕለተ እሑድ ነው።

ይህ ያልተሰላ የሰንበት የጊዜ ነጻነት (unstructured freedom of the weekend) እና ሥራ ፈትነት ባለተለመደ መልኩ ራስ ራስን እንዲፈትሽ ፋታ ይሰጠዋል። ሰው ከሥራው ውጪ ትርጒም ከሌለው ሥራ ሲቆም የሕይወት ትርጒምም አብሮ እንደሚቆም ይጠቁማል። የእሑድ ድባቴ ያለባቸው ሰዎች በጡሮታ ወቅት ወደ ባሰ ባዶነት ይወድቃሉ። እንደ ቪክተር ፍራንክል ገለጻ ይህ የሚሆነው የሰው ልጅ የሕይወት ትርጒም መፈለጉ የሕይወቱ ዋና ጉዳይ ስለሆነና ባለ አምክንዮአዊ (purpose-driven) ስለሆኑ እርሱን በመፈለግ ነው።

የእሑድ ድባቴ የሰው ልጅ ከሳምንታዊ ሥራው ውጪ በሌሎች ማኅበራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይም ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበት የሚያመለክቱና ሕይወት በአእምሯዊ ወይም ተቋማዊ ሥራ ብቻ ሙሉ እንደማይሆን የሚያሳይ ነው። ይህ ቀን ተረጋግቶ ለማሰብ እድል ስለሚሰጥ ብዙዎች ሕይወት ምንድን ነው? እንዴት እየኖርሁ ነው? የዚህ ኑሮየ ፍጻሜ ምንድን ነው? እንዳሰብሁት እየኖርሁ ነው ወይ? በሕይወቴ ምን ያክል ደስተኛ ነኝ? የሚሉና ሌሎችንም የህልውና እውነታዎች ዳሰሳ (Existential pondering) ያደርጋሉ። በተለይ ትዳር ያልያዙ ወይም የፈቱ በብዙው ይፈተኑበታል። ግብዳ የሚያክሉ የሕይወት ጥያቄዎች በዚህ ቀን በአእምሯቸው ውስጥ ይንከባለላሉ።

ከላይ ካነሣነው በተጨማሪ የእሑድ ድባቴ መንስኤ የሚባሉት ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

ማኅበራዊ መገለል፦ በራሳቸው ምርጫ፣ በክፉ ሥራቸው ወይም ሰው በማጣት ከማኅበራዊ ሕይወት የተለዩና ማኅበራዊ መገለል ያለባቸው ሰዎች እሑድ ዕለት እንዲሁ ከፍተኛ የሆነ ጫናና ድብርት ውስጥ ይወድቃሉ።

ከሥራ ጋር የተያያዘ ጭንቀት፦ ይህ እሑድ ላይ ሁነን ነገ ሥራ እንደምንገባ ስናስብ የሚመጣ ምሬት የወለደው ጭንቀት ነው። በተለይ ሥራችን ከባድ ከሆነ ክፉ አለቃ ካለንና በአጠቃላይ መጥፎ የሥራ ከባቢ (unpleasant working condition) የሚከሰት ነው።

የእቅድ አለመሳካት፦ ሌላው ሳምንቱን አርፋለሁ ወይም በደስታ አሳልፋለሁ በሥራ ከነበረብኝ ጫና ትንሽ ትንፋሽ አገኛለሁ ብሎ ያቀደ ሰው ሳምንቱ እንዳሰበው ሳይሄድ ሲቀር ስኬት አልባ ወይም እርካታ አልባ ስሜት sense of dissatisfaction ይሰማውና ይበሳጫል፤ ይደበራል፤ አእምሯ ቀውስ ውስጥም ይገባል።

የእሑድ ድባቴ ምልክቶቹ ድካም፣ ምክንያቱ የማይታወቅ ጭንቀትና ከዚያም ያለፈ ብስጭት ወይም መነጫነጭ፣ እንቅልፍና የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ሳይራቡ አብዝቶ መብላትና (overeating) ያገኙትን ሁሉ ወደ አፍ ማለት፤ የአእምሮ መወጣጠርን በምግብ ለመርሳት መሞከር፣ በአንድ ነገር ላይ አለመጽናትና ያንንም ያንንም መነካካት፣ ቴሌቪዥንም ሆነ ዩቱብ ላይ የአንዱን መልእክት ሳያዳምጡ ጀምሮ ወዲያውኑ ወደ ሌላው መቀየርና በቀላሉ መሰላቸት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

መፍትሔዎቹ፡

1. ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ፦ ይህ እጅግ በጣም ወሳኝ ነው። በጠዋት ተነሥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ መንፈሳዊ፣ ስነ ልቡናዊ፣ አእምሯዊና ማኅበራዊ ጉዳዮችን በአንድ መንገድ እንድንፈጽማቸው ያደርገናል። ሕይወታችንንም ከምድራዊው ወደ ሰማያዊው፣ ከጊዜያዊው ወደ ዘለዓለማዊው ከሥጋዊው ወደ መንፈሳዊው በማሳረግ በሥራ ከምናገኘው ትርጉም ብዙ እጥፍ የበለጠ ትርጒም እንዲኖራት ያደርጋል። ይህ እኔን ጨምሮ ብዙዎች ሞክረውት ያረጋገጡት እውነታ ስለሆነ ሁሉም ሊያደርገው የሚገባ ነው።

እምነት ጠቀሜታው መንፈሳዊ ብቻ አይደለም። በእውነቱ ብዙ ሥጋዊ ጥቅሞች አሉት። ጾም ጸሎት ምጽዋት ከመንፈሳዊ በረከት ባለፈ ለስነልቡናዊና ስነ አእምሯዊ ትርጉምና እምርታ ያላቸው እርባና እጅግ የገዘፈ ነው። መንፈሳዊ ሰው ጠቅሎ ጎራሽ ነው። ሁሉንም በአንድ ላይ ነው የሚያገኛቸው።

2. አብዝቶ መጸለይ፦ በተለይ በውጪው ዓለም ያላችሁና ቤተ ክርስቲያን መሄድ የማትችሉ እሑድን በጸሎትና በዝማሬ ወይም መጽሐፍ ቅዱስ በማጥናት ብታሳልፉት እሑድ ብቻ ሳይሆን ቀሪው ሳምንት ሁሉ በደስታ የተሞላ ይሆንላችኋል።

3. ሰው መጠየቅ፦ ሌላው በተለይ ቤተሰብ የሌላችሁና ብቻችሁን የምትኖሩ እሑድ በአካል ከቻላችሁ ሄዳችሁ ካልቻላችሁ መጠየቅ ያለባችሁን የድሮ ወዳጅም ሆነ የእናንተን ምክን የሚፈልግ አካል በስልክ ድውላችሁ አውሩት። በአካል ባይቻል በስልክ ማኅበራዊ ሕይወታችሁን አጠናክሩ።

4. በጠዋት መነሣት፦ የእሁድ ድብርት ትልቁ ምክንያት አርፍዶ መነሣት ነው። ሰውነታችን የለመደው የእንቅልፍ ጊዜ አለ እርሱን ስናሳልፍ እኛ እያረፍን ቢመስለንም ሰውነታችንን ሌላ ልማድ ውስጥ እያስገባን እያስጨነቅነው ነው። የተሻለ የሚሆነው በተለመደው ሰዓት ተነሥቶ ጸሎት ጸልዮ ወይም ስፖርት ሠርቶ ቁርስ በልቶ ጥቂት አነባቦ እንደገና ጥቂት መተኛት ይቻላል።

5. በአዘቦት ብቻ ሳይሆን ዘወትርም ሕይወትን ከሥራ ባሻገር ካሉ ጉዳዮች ጋር ማዛመድ፦ ማለትም በተገቢው መልኩ መዝናናት፣ ማንበብ፣ ስፖርት መሥራት ማኅበራዊ ተሳትፎ ማድረግ።

6. የሕይወትን ትርጒም በእንጀራና በሥጋዊ እርካታ ብቻ አለመወሰን። ለአእምሯዊና መንፈሳዊ የእድገትና የአቅርቦት ምንጮችም (sources of our spiritual supply) ማሰብ ይገባል።

እኛ በቤተክርስቲያናችን በቅዳሴው በሰንበት እናርፍባታለን፤ እረፍታችን ግን “አኮ በሰኪብ በመተኛት አይደለም” ይልቁንስ እንደ መላእክት በምሥጋና በመትጋት ነው እንጂ እንላለን። መላእክት እያረፉ ያመሰግናሉ እያመሰገኑም ያርፋሉ፤ እረፍታቸው ምሥጋናቸው ምሥጋናቸውም እረፍታቸው ነውና። እኛም ሰንበትን መተኛ ብቻ ካደረግናት በእረፍታችን እንደክማለን፤ በደስታዋ ቀንም ወደ ድባቴና የከፋ ጭንቀት ውስጥ እንገባለን። ይህን ልብ ብለን እንንቃ፤ ወደ አምልኮና ወደ ማኅበራዊ ኅብረት እንቅረብ።

ሠናይ ቀን
Banteamlak Ayalew Abate



01/07/2025

ሲዳማ ቡና ዋንጫውን ተነጠቀ
*********************

በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ወላይታ ድቻን በማሸነፍ ዋንጫውን ወስዶ የነበረው ሲዳማ ቡና ክብሩን ተነጥቋል፡፡

ሲዳማ ቡና በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ድቻን 2 ለ 1 ቢያሸንፍም ዋንጫውን እንዲመለስ ተደርጓል፡፡

በጨዋታው ቅጣት የተጣለባቸው ተጫዋቾች መጠቀሙን ተከትሎ ውጤቱ እንደተሰረዘበት የኢትጵጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አሳውቋል፡፡

#ምን ትላላችሁ

 #ነብስይማር🙏🙏🙏🙏👇👇👇👇👇👇👇👇👇 #በትላንትናው አየቃቂ አደጋ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው አልፏልበመዲናዋ በትራፊክ አደጋ የሦስት ዓመት ሕጻንን ጨምሮ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈበአዲ...
24/06/2025

#ነብስይማር🙏🙏🙏🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

#በትላንትናው አየቃቂ አደጋ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው አልፏል
በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ የሦስት ዓመት ሕጻንን ጨምሮ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በዛሬው ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሦስት ዓመት ሕጻንን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ አደጋው በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የተከሰተው፡፡

ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡስ ከከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ መግባቱን አብራርተዋል።
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

ሶሪያ 🇸🇾 በደማስቆ፣ ሶሪያ በሚገኘው የቅዱስ ኤልያስ ግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው አስከፊ የሽብር ጥቃት ከ20 በላይ ንፁሃን ምዕመናን ሲሞቱ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።ይህ...
23/06/2025

ሶሪያ 🇸🇾

በደማስቆ፣ ሶሪያ በሚገኘው የቅዱስ ኤልያስ ግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው አስከፊ የሽብር ጥቃት ከ20 በላይ ንፁሃን ምዕመናን ሲሞቱ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።

ይህ አሰቃቂ ጥቃት የጸሎት አገልግሎት እየተካሄደ ባለበት ወቅት የተፈጸመ ሲሆን፣ በሶሪያ ዋና ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል።

ይህ ጥቃት በሃይማኖት ነፃነት እና በሰላማዊ አምልኮ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ሲሆን፣ የአምልኮ ቦታዎች የሰላም እንጂ የጦርነት መድረክ መሆን እንደሌለባቸው ያስገነዝባል።

የአሶሺዬትድ ፕሬስ (AP) እና ሮይተርስ (Reuters) እንደዘገቡት፣ ከ20 በላይ የሚሆኑ ምዕመናን በጸሎት ላይ እያሉ ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ 55 የሚሆኑት ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ዘገባው የAP እና የReuters ነው::

ነፍሳቸውን ይማር!

💔

በ22 ቢሊየን ብር የተቋቋመው ኬኛ ቢራ እንዴት አያችሁት
14/06/2025

በ22 ቢሊየን ብር የተቋቋመው ኬኛ ቢራ እንዴት አያችሁት

ተገናኝተዋል* በጋሻው፣ * ዘርፌ እና * ትዝታው!ተባረኩ! ዘመናችሁ ሁሉ በበረከት ይሞላ። እናንተ በወንጌል አማኞች ዘንድ በእውነትም እንቁ አገልጋዮች ናችሁ። ለአገልግሎታችሁ ከልብ እናመሰግና...
14/06/2025

ተገናኝተዋል

* በጋሻው፣
* ዘርፌ እና
* ትዝታው!

ተባረኩ! ዘመናችሁ ሁሉ በበረከት ይሞላ።

እናንተ በወንጌል አማኞች ዘንድ በእውነትም
እንቁ አገልጋዮች ናችሁ።

ለአገልግሎታችሁ ከልብ እናመሰግናለን በልልን!

?????????????

10 ደቂቃዎችን በመዘግየቷ የበርካቶችን ሕይወት ከቀጠፈው አደጋ የተረፈችው ህንዳዊት******************በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት በረራ ያመለጣት ህንዳዊት ለበርካቶች ህይወት መጥፋት...
13/06/2025

10 ደቂቃዎችን በመዘግየቷ የበርካቶችን ሕይወት ከቀጠፈው አደጋ የተረፈችው ህንዳዊት
******************

በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት በረራ ያመለጣት ህንዳዊት ለበርካቶች ህይወት መጥፋት ምክንያት ከሆነው አደጋ 10 ደቂቃዎችን በመዘግየቷ መትረፏን ኤንዲ ቲቪ ዘግቧል።

ከባለቤቷ ጋር በለንደን ከተማ የምትኖረውና ከአደጋው በኋላ ከኤንዲ ቲቪ ጋር ቃለምልልስ ያደረገችው ቦሆሚ ቻውሃን የእረፍት ጊዜዋን አህመዳባድ ከሚገኙ ቤተሰቦቿ ጋር አሳልፋ በበረራ ቁጥር 171 ለመብረር ትኬት ቆርጣ ነበር።

ሆኖም ወደ አውሮፕላን ማረፊያው እያመራች በነበረበት ወቅት ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳጋጠማት እና አስር ደቂቃ ዘግይታ አህመዳባድ አየር ማረፊያ ስትደርስ ግን ወደውስጥ እንዳትገባ በመከልከሏ መናደዷን ገልፃለች።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም እዛው አየር መንገዱ ውስጥ እያለች ወደለንደን ልትጓዝበት የነበረው አውሮፕላን መከስከሱን ማየቷን ተናግራለች።

16/03/2025

እናንተስ ምን ትላላችሁ???

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ADBAR MEDIA አድባር ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ADBAR MEDIA አድባር ሚዲያ:

Share