Addis Condo Winners

Addis Condo Winners List of Addis Ababa City Condominium Winners of the year 2015 who were registered in 2005. Use Id and Name for Searching the winners.

This page and the website is designed to help people to check the list of the winners of the condominium programs of Addis Ababa. It provides the easiest method to use names or ID numbers. It also delivers some latest news and information about condominium. Telegram - https://t.me/condowinnersethio
Website - https://www.condowinners.com
YouTube - https://www.youtube.com/channel/UCY5DYycb3HCuK0G-FeO0lHA
Follow our Facebook , YouTube and Telegram Channel

አዲስ አበባ ጀሞ:አራብሳ፣ ሰሚት፣ ኢምፔርያል፣ ፊጋ፣ አያት 49፣ ሰሚት፣ ኮዬ ፈጬ በመሬት መንቀጥቀጡ ስጋት ነዋሪው ውጭ ላይ ነው::
06/10/2024

አዲስ አበባ ጀሞ:አራብሳ፣ ሰሚት፣ ኢምፔርያል፣ ፊጋ፣ አያት 49፣ ሰሚት፣ ኮዬ ፈጬ በመሬት መንቀጥቀጡ ስጋት ነዋሪው ውጭ ላይ ነው::

Most places in Addis also there were some shock !
06/10/2024

Most places in Addis also there were some shock !

ማስታወቂያበአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከዚህ ቀደም በ70/30 በማህበር ለመደራጀት ተመዝግባችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ የ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢዎች  ከሚያ...
13/04/2024

ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከዚህ ቀደም በ70/30 በማህበር ለመደራጀት ተመዝግባችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ የ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢዎች ከሚያዝያ 8/2016 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 6ኛ ፎቅ የጋራ መኖሪያ እና ህብረት ስራ ማህበር ዳይሬክቶሬት ዘውትር በስራ ሰአት በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ቀደም ሲል 70 ፐርሰንት በባንክ አካውንት ገንዘብ አስገብታችሁ ከሆነ የባንክ እስቴትመንት ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ 70 ፐርሰንቱን ገቢ ያላደረጉ ከሆነ ለተመዘገቡበት የቤት አይነት ከሚያዝያ 8/2016 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን በቀድሞ የ40/60 ወይም የ20/80 ቤት ቁጠባ አካውንት ላይ ገቢ በማድረግ እና እስቴትመንት ይዛችሁ በመቅረብ ብቁ መሆኑን በአካል ቀርበው ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ጨረታ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነየአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አስገንብተው ለጨረታ ያቀረቧቸው ...
03/04/2024

የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ጨረታ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አስገንብተው ለጨረታ ያቀረቧቸው የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል።

ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ የመጋቢት 25/2016 እትም ማየት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን

ሙሉ ዝርዝሩን
https://t.me/c/1175658184/295

 በአዲስ አበባ ከተማ   እና   ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ይህን ጉ...
02/04/2024



በአዲስ አበባ ከተማ እና ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ለሁሉም ክ/ከተሞች የአፈፃፀም መመሪያ መጻፉን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

በከተማዋ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተብሎ በገዥ እና ሻጭ መካከል የሚደረግ ውል ላይ የሚቀርበው ዋጋ እጅግ በተጋነነ መልኩ ዝቅተኛ በመሆኑ እና በባለሙያ የሚወሰድ የቤት ግምት ዋጋ ወቅታዊ ባመሆኑ መንግስት ከቤት ሽያጭ ተገቢውን ገቢ እየሰበሰበ እንዳልነበረ ቢሮው ገልጿል።

ይህንን ችግር ለመፍታት እንዲቻል ካለፈው ዓመት ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ወቅታዊ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተግባራዊ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ በከተማ ደረጃ ተጠንቶ ተግባራዊ የተደረገ የቤት ሽያጭ ዋጋ እና አሰራሩ ላይ ከህብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎች እየቀረቡ በመሆኑ በመሬት ልማትና አስተዳደተር ቢሮ እና የመሬት ይዞታ ምዝገበና መረጃ አጄንሲ በጋራ ጥናት በማድረግ የተለዩ ክፍተቶችና እና የቤት ሽያጭ ግምት ላይ ማሻሻያ ተደርጓል ብሏል።

በተደረገው ማሻሻያ ለአፓርትመንት ቤቶች እና ኮንዶሚኒየም ቤቶች የሽያጭ ዋጋ ተመን አምና በሰኔ ወር ከነበረው 34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

በተሻሻለው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦

➡️ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣
➡️ በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣
➡️ የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣
➡️ G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡

የቦታው መገኛ ዋጋ ('location value') ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል።

የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከ ከመጋቢት17 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንዲከፈልም ቢሮ አዟል።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን #መሻሩንም ቢሮ ጠቅሷል።

በፍርድ ቤት እና በባንክ ሃራጅ ሽያጭ የስም ንብረት ዝውውር የሚጠየቅባቸው ይዞታዎችን በተመለከተ ይዞታ አገልግሎትና መብት ፈጠራ ደንብ ላይ በተቀመጠው አግባብ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።

ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።

ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለሁሉም ክ/ከተሞች የፃፈውን የአፈፃፀም መመሪያ ዋቢ በማድረግ ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

የጨረታ ማስታወቂያ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያለበትን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቶ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ  እንዲችል ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋ...
04/02/2024

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያለበትን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቶ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲችል ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው የተጠናቀቁ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን እና 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከ27/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20/06/2016 ዓ.ም ድረስ ቅዳሜን እስከ 11፡00 ሰአት እና እሁድ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ማታ 1፡30 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00(አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱ መግዛት የሚቻል መሆኑን እየገለጽን የሰነድ መሸጫ ቦታ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል

21/06/2023

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል

ቢሮው በከተማዋ ላለፉት አምስት ዓመታት ቆሞ የነበረውን መሬትን በሊዝ ጨረታ የማስተላለፍ ተግባር ዳግም መጀመሩ አስታውሷል።

ከግንቦት 24/2015 ዓ/ም ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎቹ የተለየውን የ1ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ መደረጉን አሳውቋል።

በዚህ ጨረታ ዝቅተኛ ዋጋ የተመዘገበው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሲሆን፣ ይህም በካሬ ሜትር 20 ሺህ ብር ነው፡፡

ከፍተኛው በአራዳ ክፍለ ከተማ ሲሆን በካሬ ሜትር 414 ሺህ ብር እነደሆነ ተገልጿል።

ለ21 ሺህ 636 ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የተሸጠ ሲሆን ከእነዚህ ወስጥ 11 ሺህ 437 ሰነዶች ተሞልተው ሳጥን ውስጥ ገብተዋል።

ሙሉ የጨረታውን አሸናፊዎች ስም ዝርዝር ከላይ በተያያዘው PDF ፋይል ቴሌግራም ላይ ይመልከቱ https://t.me/housinginaddisababa/10070

19/05/2023

የቤት እድለኞችን ውል የማዋዋል ጊዜ እስከ ግንቦት 30/2015 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ

የ14ኛው ዙር የ20/80 እና የ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች ውል የማዋዋል ሂደት እሰከ ግንቦት 30/2015 ባሉ የስራ ቀናት /ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ/ መራዘሙን በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቤሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አሳወቀ።

ከጥር 1 ጀምሮ እስከ ግንቦት 7 ተጠቃሚውን ሲያዋውል መቆየቱን ኮርፖሬሽኑ ባወጣው ማስታወቂያ የገለፀ ሲሆን አሁንም በተለያየ ምክንያት ያልተዋዋሉ የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞችን የመጨረሻ እድል ለመስጠት ሲባል እሰከ ግንቦት 30 ማራዘሙን ገልጿል።

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ያልተዋዋለ የቤት እደለኛ ቤቱን እንዳልፈለገው ተቆጥሮ ለኮርፖሬሽኑ ተመላሽ እንደሚሆንም በማስታወቂያው ተገልጿል።

_______________________
በገጻችን የምናቀርባቸውን መረጃዎች በአማራጭነት በቴሌግራም ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇
t.me/housinginaddisababa
እንዲሁም፦

Address

Addis Ababa
<<NOT-APPLICABLE>>

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Condo Winners posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Addis Condo Winners:

Share