24/09/2026
#ለወገን ደራሽ ወገን ነው !!!
የእርዳታ ጥሪ ለወንድማችን መሀመድ አሊ እንድሪስ ህይወትና ተስፋ እንድረስለት!
በጥንካሬውና በጠንካራ ሰራተኝነቱ የሚታወቀው ጎበዝ መሀንዲስ ወንድማችን መሀመድ አሊ እንድሪስ በስራ ገበታው ላይ እያለ ባጋጠመው ድንገተኛ አደጋ ህይወቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። በተሰማራበት የስራ ቦታ ቤት ተንዶበት በደረሰበት ከባድ የአካል ጉዳት ምክንያት አሁን ላይ ተንቀሳቅሶ መስራትና ቤተሰቡን መደገፍ የማይችልበት ደረጃ ላይ ወድቋል።
አቶ መሀመድ የሁለት ህጻናት ልጆች አባት ሲሆን አደጋው ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እሱም ሆነ ህጻናት ልጆቹ ለቀን ጉርስ እንኳን ተቸግረው ይገኛሉ። ወንድማችን በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ሆኖ እግሬ ሳይቆረጥ በፊት ድረሱልኝ ህይወቴንና የልጆቼን መፃኢ እድል አድኑልኝ ሲል በ አጣዳፊ የእርዳታ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ለህክምናው አስፈላጊ የሆነውን ቅድመ ሁኔታ ለማሟላት ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ የሚጠየቅ ሲሆን ይህንን ወጪ አቅም በማጣቱ ምክንያት በብቸኝነት መሸከም አልቻለም።
ቸርነት ለራሱ ነውና አቅማችን የፈቀደውን ያህል በመደገፍ የወንድማችንን እግርና ህይወት እንታደግ የሁለቱን ህጻናት ልጆች እንባ እናብስ።
የባለቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ [1000579826391
ሰሚራ ሰይድ መኮነን]
የስልክ ቁጥር፡ [0984305523] [ሰሚራ ሰይድ መኮነን