በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል
https://t.me/aac_pshrdb
ያለዎትን ሀሳብ አስተያት እንዲሁም ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ

ማስታወቂያ።።።።።።።።።።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ በመሬት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ለሚገኙ ክፍት የስራ መደቦች ለመ...
22/09/2025

ማስታወቂያ
።።።።።።።።።።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ በመሬት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ለሚገኙ ክፍት የስራ መደቦች ለመወዳደር ያመለከታችሁ በሙሉ ለፅሁፍ ፈተና መመልመላችሁን ለማየት ከታች በተቀመጠው ሊንክ ገብታቹ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለፅሁፍ ፈተናው የተለያቹ ተፈታኞች ብቻ ፈተናው የሚሰጠው ሀሙስ መስከረም 15/2018 ከቀኑ 7፡30 በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) የሚሰጥ ሲሆን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትገኙ እናሳሰባለን፡፡

www.aacapsjobs.gov.et

ቢሮው በመንግስት ሠራተኞች አዋጅ 87/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለቢሮው ሰራተኞች ሰጠ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ምበአዲሱ ...
22/09/2025

ቢሮው በመንግስት ሠራተኞች አዋጅ 87/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለቢሮው ሰራተኞች ሰጠ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም

በአዲሱ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ 87/2017 አተገባበርና አፈፃፀም ዙሪያ ለቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በመድረኩ እንደተገለፀው አዋጁ የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደርና አደረጃጀት ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ እና ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ የተገልጋዩን ማህበረሰብ ፍላጎትና ጥያቄ በአጥጋቢ ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል፣ የመንግሥትን የመፈፀም ብቃት በማጎልበት፣ የዜጎችን ፍላጎት የሚያረካ እና ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ ሊያሸጋግር የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በቢሮው የሰው ሀብት ስራ አመራር ክትትል፣ ድጋፍ እና ኦዲት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተመስገን እንደገለፁት አዋጁ በመንግሥት መሥሪያ ቤት፣በመንግሥት ሠራተኛ እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን በመሆኑ አመራሩም ሆነ ባለሙያው ጠንቅቆ ማወቅ እና ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ መንገዶች መፈጠር እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በአዋጁ በዝርዝር ከተቀመጡት መካከል የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም ሠራተኛ ሊከተል የሚገባው መሠረታዊ ዕሴቶች እና መርሆዎች ፣ መዋቅራዊ አደረጃጀት ፣ የሰው ኃይል ዕቅድ እና የሥራ ምዘና ዘዴን መምረጥ፣የደመወዝ ስኬል፣ አበል ክፍያ እና ጥቅማ ጥቅም፣ የሠራተኞች ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ፣ ሥልጠና አሰጣጥ፣ የሥራ ስምሪት እና ነፃ ገለልተኛ ሥርዓት፣ቀጣይነት ያለው የለውጥ ዝግጁነት እና የሥራ አፈፃፀም አመራር ሥርዓት፣የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር እና ድልድል አፈፃፀም፣የሥራ ሰዓት እና ፈቃድ ተጠቃሾች ናቸውም ብለዋል፡፡

በቢሮው ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚያካሄደው አብሮነት ለለውጥ   የ11ኛ ዙር መርሀ ግብር ተካሄደ።፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ፤ መስከረም 12 ቀን  2018ዓ.ም የአዲስ አ...
22/09/2025

በቢሮው ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚያካሄደው አብሮነት ለለውጥ የ11ኛ ዙር መርሀ ግብር ተካሄደ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ፤ መስከረም 12 ቀን 2018ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚያካሄደው አብሮነት ለለውጥ መርሀግብር የ11 ኛ ዙር ፕሮግራሙን የቢሮው አመራርና ሰራተኞች በተገኙበት አካሂዷል፡፡

የእውቀት ሽግግር እና የህይወት ልምዳቸውን ያካፈሉት በቢሮ የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሰው ሀብት ባለሙያ ወንድወሰን ሞገስ "ልህቀት/Excellence/ " በሚል ሀሳብ ላይ የእውቀት ሽግግራቸውን አካፍለዋል ።

ልህቀት ሲባል Quality -out standin or excle ማንነትን በስራ በተቻለ መጠን በሁሉም ስራ ልቆ መገኘት እንዲሁም ከራስ ጋር በራስ ማሳደግ እና ከፍታ ማለት ከማህበረሰቡ ከአቻ ልቆ መገኘት መሆኑን አቶ ወንድወሰን አብራርተዋል።

አያይዘውም ልቆ ለመገኘት ማድረግ የሚገቡ ነገሮች ራስን ማወቅ፣ ራስን መመዘን ፣ራስን ማሻሻል ፣ራስን ማሳደግና ራስን መለውጥ ትላልቅ ለውጦችን ማሳደግና ሙሉ ለውጥ ማድረግ እንዳለበት ጭምር ገልፀዋል።
ስለ ታላላቅ ሰዎች እና አንፀባራቂ ስራዎቻቸውም ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።

21/09/2025
21/09/2025
"ዛሬ በ46 የተለያዩ  የሞያ አይነቶች ስልጠናቸውን በውጤታማነት ያጠናቀቁ 7 ሺህ 149 የቴክኒክና ሞያ ሰልጣኞችን በታላቅ ድምቀት አስመርቀናል። ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!ባለፉት 2 ዓ...
20/09/2025

"ዛሬ በ46 የተለያዩ የሞያ አይነቶች ስልጠናቸውን በውጤታማነት ያጠናቀቁ 7 ሺህ 149 የቴክኒክና ሞያ ሰልጣኞችን በታላቅ ድምቀት አስመርቀናል። ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

ባለፉት 2 ዓመታት በቴክኒክና ሞያ ስልጠና ዘርፍ ነባር ችግሮችን በመቅረፍ ለአገራዊ ብልፅግና የሚጠበቅበትን ጉልህ ሚና እንዲወጣ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአጭር ጊዜ አበረታች ውጤት እያስመዘገብን እንገኛለን። በተለይም በዘርፉ የሚሰጡ ስልጠናዎች የአገሪቱን የብልፅግና አቅጣጫ የተከተሉ እና የገበያው ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ማድረግ ችለናል።

ሰልጣኞች በቆይታቸዉ 70 በመቶ የተግባር እንዲሁም 30 በመቶ የንድፈ ሃሳብ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉ ክህሎትን በማላቅ፣ ፈጠራን በመጨመር አበረታች ውጤት እያመጣ ይገኛል።

ውድ ተመራቂዎች፤ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ ያለንበትን የውድድር ዓለም ከግምት በማስገባት ምንጊዜም ራሳችሁን በእውቀት፣ በክህሎት በተለይም በቴክኖሎጂ በማበልፀግ ፈጠራና ፍጥነትን የህይወታችሁ መርህ በማድረግ ስራ ፈጣሪ መሆን ይጠበቅባቹሀል። አስተዳደራችንም ይህን ለመደገፍ እንደ እስካሁኑ ሁሉ ከጎናችሁ መሆኑን ዳግም አረጋግጥላቹሀለሁ"።

መልካም የስራ ዘመን !

ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

20/09/2025
ቢሮው  የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበርን አስመልክቶከአመራርና አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር"በእምርታናማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላትን በጋራ እናክብር" በሚል መሪ ቃል ወይይት አካሂዷል።።።...
19/09/2025

ቢሮው የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበርን አስመልክቶ
ከአመራርና አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር"በእምርታናማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላትን በጋራ እናክብር" በሚል መሪ ቃል ወይይት አካሂዷል።
።።።።።።።።።።።።።።
ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ፤ መስከረም 9 ቀን 2018ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበርን አስመልክቶ ከአመራር እና አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር "በእምርታ እና ማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላትን በጋራ እናክብር" በሚል መሪ ቃል ወይይት አድርጓል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር እንደተናገሩት የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት በወንድማማችና እህትማማችት የምናከብራቸው በዓላት እንደመሆናቸው ገልፀው ሀይማኖታዊ እሴታቸውንና ትውፊታቸውን ጠብቀው በአብሮነትና በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ ሁሉም የድርሻውን በቁርጠኝነት በጋራ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡

ሰነዱን ያቀረቡት የቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጠይባ ሹክሬ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መኖሪያና የብዝሀ ሀይማኖቶች ማህደረ የአብሮነት እና የመቻቻል እንዲሁም ብል ጽግናን እውን ለማድረግ የምትታትር የብዝሀ ፀጋ ምድር እንደሆነች ገልፀው አብዛኞች የሀገራችን ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ ታላቅ በዓላቸውን በምስጋና የሚያከብሩት በመስከረም ወቅት ነው ያሉ ሲሆን መስቀልና ኢሬቻ ለሀገራችን ልዩ ድምቀት የሚፈጥሩ የአደባባይ በዓላት መሆናቸው በህዝቦች መካከል የወንድማማችነትና እትማማችነት መንፈስ የሚፈጥሩ መሆናቸውም ጭምር ተገልጿል።

አክለውም ኃላፊዋ ኢትዮጽያ በአያሌ ቅርሶችና እሴቶች የበለፀገች ሀገር መሆኗን ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ግንዛቤ ማሳደግና በዩዮኒስኮ ከተመዘገቡና ኢትዮጽያ ለዓለም ካበረከተቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል መስቀልእና የኢሬቻ እንደሆኑና በዓላትን ስናከብር ከከተማችን ነዋሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በጋራ በመሆን የድርሻችን መወጣት ይጠበቅብናልም ብለዋል።

የዘንድሮ የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ከሌላው ልዩ የሚያደርገው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በዜጎች አንድነት ተገንብቶ በተመረቀበትና የሀገሪቱ ታላላቅ ፕሮጀክቶች በተሰሩበት ዘመን የሚከበሩ መሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል ያሉት የቢሮው የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጠይባ ሹክሬ ተናግረዋል።

ቢሮው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የስምምነት ሰነድ ፊርማ  ተፈራረመ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ መስከረም 8 ቀን 2018ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተ...
18/09/2025

ቢሮው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የስምምነት ሰነድ ፊርማ ተፈራረመ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ መስከረም 8 ቀን 2018ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት የስምምነት ሰነድ ፊርማ አካሂዷል፡፡

በስምምነት ሰነዱ ቢሮው የተሰጠውን ተልዕኮ በተገቢው ለመወጣት እንዲቻል ከሚሰራቸው ስራዎች ባህሪ በመነሳት በራሱ ብቻ ሊያከናውናቸው እማይቻሉ በርካታ ተግባራት በመኖራቸው እነዚህን ተግባራት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ማከናወን እንደሚገባና በበጀት አመቱ የነበሩ ክፍተቶችን በማረምና የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል በተሻለ ለመፈፀም ታልሞ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የከተማችንን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻልና የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ እንዲያስችል ቢሮው ጉልህ ድርሻ ካላቸው ተቋማት ጋር በትስስር መስራት ያለባቸውን ስራዎች በመለየት እና በተቀናጀ መልኩ በመምራት የቢሮውን ተልዕኮ ለማሳካት መሆኑ ተብራርቷል።

በመድረኩ ማጠቃለያም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቢሮው ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር እንደተናገሩት
ተቋማዊ ለዉጥ ለማምጣት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተጀመሩ ስራዎችን በማስቀጠል ለ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም በማምጣት ስራዎችን በገቡት ቃል መሰረት በመናበብ እንዲተገብሩ አሳስበዋል ።

ቢሮው  በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና በስምሪት ስራዎች ላይ  ከማዕከልና ከክ/ከተማ ከተውጣጡ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አደረገ። ::::::::::::::...
18/09/2025

ቢሮው በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና በስምሪት ስራዎች ላይ ከማዕከልና ከክ/ከተማ ከተውጣጡ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አደረገ።

:::::::::::::::::::::::::::::

ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ፤ መስከረም 8 ቀን 2018ዓ.ም

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃሳብ ልማት ቢሮ ከማዕከልና ከክ/ከተማ ከተውጣጡ የሰው ሀብት አስዳደር ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አደረገ።

ውይይቱ በዋናነት ትኩረት ያደረገው የመንግስት ሰራተኞች የትምህርት ማስረጃ ማጣራትና የስምሪት ስራዎች ለማከናወን እና የተቀናጀ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ኢስሚስ አተገባበር ፣ቅሬታዎችን በምን መልኩ መቀበል ላይ ውይይት ተደርጓል። በማዕከላትና በክ/ከተማዎች የሚገኙ ሰራተኞች የትምህርት ማስረጃዎች እያጣሩ ያለበትንና ደረጃ የመጡ ቅሬታዎችን በምን መልኩ አየፈቱ እንደሆነ ሪፓርት አድርገዋል።

በመጨረሻም የቢሮው የሃላፊ አማካሪ አቶ አቡከር ሃሽም እንደገለፁት ማስረጃ ማጥራት እና ቅሬታ መቀበል በምን መልኩ ማከናወን እንዳለባቸው እና የትምህር ማስረጃ ማጥራት ያስፈለገው የተሻለ አገልግሎት ለማግኘት አላማ ያደረገ መሆኑን ገልፀው በተቋማት የጀመሩት ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

Address

Addis Abeba, 5killo
Addis Ababa
12134568

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share