Liyu Sport

Liyu Sport is a dedicated sports website, entertaining professional opinions and news about/from Ethiopia.

! www.liyusport.com

ናይጄሪያ አሰልጣኟን አሰናበተችየ ናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጌርኖት ሮህር ከሃላፊነት ተሰናብተዋል።የ 68 አመቱ ጀርመናዊ በ አለም ዋንጫ ማጣሪያ ናይጄሪያን ወደ መጨረሻው ዙር ማጣሪያ ...
18/11/2021

ናይጄሪያ አሰልጣኟን አሰናበተች

የ ናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጌርኖት ሮህር ከሃላፊነት ተሰናብተዋል።

የ 68 አመቱ ጀርመናዊ በ አለም ዋንጫ ማጣሪያ ናይጄሪያን ወደ መጨረሻው ዙር ማጣሪያ ማሳለፍ ችለው ነበር።

ጌርኖት ሮህር ከ ነሃሴ 2016 ጀምሮ የ ናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሲሆኑ: በ 2019 ኙ የ አፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ 3ኛ ደረጃን እንድታገኝ አድርገዋል።

04/02/2020
08/01/2019

... and now its Confirmed
08/01/2019

... and now its Confirmed

በጣም ረጅም ነገር ግን: አየርላንዳዊዉ ጋዜጠኛ ኬን ኧርሊ በማራኪ ስነጽሑፋዊ አቀራረብ፡ ታሪክ ትስስር እና ነገራ በተለያዩ ዘመናት ስለተፈጠሩ እና በሁለት የተለያዬ መስክ ግን ደግሞ ተቀራራቢ...
23/12/2018

በጣም ረጅም ነገር ግን: አየርላንዳዊዉ ጋዜጠኛ ኬን ኧርሊ በማራኪ ስነጽሑፋዊ አቀራረብ፡ ታሪክ ትስስር እና ነገራ በተለያዩ ዘመናት ስለተፈጠሩ እና በሁለት የተለያዬ መስክ ግን ደግሞ ተቀራራቢ በሚመስል የአሸናፊነት መንገድ ራሳቸውን ከምንም አንስተው አንቱ ያስባሉ ግለሰቦችን ታሪክ የሚዳስስ ፅሁፍ ነው፡፡

ለመሆኑ ፈረንሳያዊው የጦር ሊቅ ናፖሊዮን ቦናፓርት እና ፓርቹጋላዊው ውጤታማ የእግርኳስ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሬንሆ ምን የሚያመሳስላቸው ነገር ይኖር? ጥሩ ጊዜ ከተከታዩ ጽሁፍ ጋር... [ 1,678 more word ]

በጣም ረጅም ነገር ግን: አየርላንዳዊዉ ጋዜጠኛ ኬን ኧርሊ በማራኪ ስነጽሑፋዊ አቀራረብ፡ ታሪክ ትስስር እና ነገራ በተለያዩ ዘመናት ስለተፈጠሩ እና በሁለት የተለያዬ መስክ ግን ደግሞ ተ.....

Opinion: School Football, a fertile ground for the development of African Football Haileegziabher Adhanom, AIPS Member, ...
21/12/2018

Opinion: School Football, a fertile ground for the development of African Football

Haileegziabher Adhanom, AIPS Member, Ethiopia

NAKURU, December 20, 2018 - It was in the evening of December 7th 2018 that my phone rang. It was a familiar name displayed on my screen, Ms. Tigist Getu, Coca Cola's Brand Manager for Ethiopia and East Africa, who I met while covering the Copa Coca Cola annual national tournaments, for years. [ 917 more words ]

A spotkick is taken at the Coca Cola U-16 African Cup Final Match in Nakuru, Kenya. (Photo by Haileegziabher Adhanom, AIPS Member, Ethiopia) Haileegziabher Adhanom, AIPS Member, Ethiopia NAKURU, De…

ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም - ታህሳስ 11/2011 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በነበሩት አመታት እንደሚያደርገው ሁሉ፡ ከሚያከናውነው አመታዊ የታላቁ ሩጫ የ10ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ...
20/12/2018

ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም - ታህሳስ 11/2011 ዓ.ም

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በነበሩት አመታት እንደሚያደርገው ሁሉ፡ ከሚያከናውነው አመታዊ የታላቁ ሩጫ የ10ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውድድር ጎን ለጎን የበጎ አድራጎት ስራ የሚያከናውኑ ድርጅቶችን በገንዘብ ለማገዝ፡ 'ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ' በሚል መርህ፡ ከተለያዩ ድርጅቶች እና አላማውን ከሚደግፉ ግለሰቦች ያሰባሰበውን የ1.8 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ለአራት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በዛሬው እለት አበርክቷል፡፡

ስለ እናት ማህበር፡ ጆይፉል ላይፍ፡ የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር እና የኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማህበር፡ የተሰኙት ተቋማት ባቀረቡት ፕሮፖዛል ምክንያት ተመርጠው ለእያንዳንዳቸው የ450,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው ድርጅቶች ናቸው፡፡

ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ በሚገኘው ስለ እናት ማህበር በተከናወነው የድጋፍ ርክክብ ፕሮግራም ላይ፡ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ ኃይሌ ገብረስላሴ፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች እና ህጻናት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሜሮን አራጋው እንዲሁም ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት አምባሳደር የሆኑ አርቲስቶች እና የተቋማቱ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዚህ የድጋፍ ርክክብ እና ገቢውን በማሰባሰብ ሂደቱ ወቅት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እውቅና የመስጠት ስነስርአት ላይ፡ " ለሀገር መስራት፡ የተቸገሩ ወገኖችን በራስ አቅም ማገዝ እና ዛሬ ድጋፍ የተደረገላቸውንም ሆነ ሌሎች የበጎ አድራጊ ተቋማትን አቅም በፈቀደ ሁሉ ማገዝ" የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀገራዊ የዜግነት ግዴታ መሆኑን የተለያዩ አካላት አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዚህ ፕሮጀክቱ ስም እስከ አሁን ድረስ 13.3 ሚሊዮን ብሮችን ከለጋሽ አካላት በማሰባሰብ ለ40 ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረጉም በእለቱ ተገልጿል፡፡

ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም – ታህሳስ 11/2011 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በነበሩት አመታት እንደሚያደርገው ሁሉ፡ ከሚያከናውነው አመታዊ የታላቁ ሩጫ የ10ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የአ...

  RO16... 2018/19 - see you in two months time
17/12/2018

RO16... 2018/19

- see you in two months time

By: Haileegziabher AdhanomNakuru, Kenya, December 15, 2018 –Hosts Kenya became Champions of the first Copa Coca Cola U-1...
15/12/2018

By: Haileegziabher Adhanom

Nakuru, Kenya, December 15, 2018 –

Hosts Kenya became Champions of the first Copa Coca Cola U-16 Africa Cup, defeating continental football powerhouse Nigeria 3-2 on penalty, after a highly contested and entertaining 0-0 draw, during the normal time.

Kenya, were arguably the best side of the tournament, which begins on Monday in Nakuru, County. Kenya Beat Neighbouring Ethiopia 11-1, in the opening match, and record a 3-0 victory against Botswana, 1-0 against Uganda and Zambia on there way to the Final, earlier Botswana won the bronze, after beating Zambia on penalties 4-3, the normal time was finished 1-1.

[ 213 more words ]

By: Haileegziabher Adhanom Nakuru, Kenya, December 15, 2018 – Hosts Kenya became Champions of the first Copa Coca Cola U-16 Africa Cup, defeating continental football powerhouse Nigeria 3-2 on pena…

በኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም - ታህሳስ 06/2011 ዓ.ም በኬንያ አስተናጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ በተከናወነው እና አዘጋጇ ኬንያ ናይጀሪያን መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አቻ ከተጠናቀ...
15/12/2018

በኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም - ታህሳስ 06/2011 ዓ.ም

በኬንያ አስተናጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ በተከናወነው እና አዘጋጇ ኬንያ ናይጀሪያን መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አቻ ከተጠናቀቀ በሗላ በመለያ ምት 3 ለ 2 አሸንፋ የውድድሩ ቻምፒዮን በሆነችበት የ2018 የኮፓ ኮካ ኮላ ከ16 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎውን ያደረገው የኢትዮጵያ ቡድን በምድብ አንድ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች፡ በኬንያ 11ለ1 ተሸንፎ ከቦትስዋና ጋር ደግሞ ከጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴ ጋር ያለ ግብ አቻ ቢለያይም በቦትስዋና በግብ እዳ ልዩነት ተበልጦ ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፍ ሳይችል ከምድቡ መሰናበቱ ይታወሳል፡፡

ይሁንና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተመዘገበው ውጤት ደስተኛ ባይሆንም ከውድድሩ ግን እጅግ በርካታ ጠቃሚ ልምዶችን እንዳገኘ እና የነበሩበትን ችግሮችም የተመለከተበት እንደነበር ይገልጻል፡፡

ወደ ኬንያ የተጓዘው ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ኢሳያስ ታፈሰ፡ " ወደዚህ ውድድር ከመምጣታችን በፊት ማከናወን የነበሩንን በርካታ ስራዎች አለመስራታችን በደምብ ተመልክተንበታል፡ በተለይ በሀገር ውስጥ የምናከናውነው አመታዊው የኮፓ ውድድር በደምብ ያልሰራንበት እንደነበር እና ከዚህ ስንመለስ ግን የቀጣዩ ውድድር ላይ ከመጀመሪያው አንስቶ አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ በተገቢው የእድሜ ክልል የሚገኙ እና ብቃቱ ያላቸው ልጆችን ለይተን ለማብቃት እንሰራለን፡፡

በኬንያ ጥሩ ቡድን ይዘው ከቀረቡ ሀገራትም መልካም ተሞክሯቸውን ለመውሰድ ሞክረናል" ብለዋል፡፡

በዚህ ውድድር በጣም በትንሽ እድሜያቸው ከተሳተፉት ታዳጊዎች መካከል አንዱ የሆነው የ13 አመቱ ኢትዮጵያዊ ኦባንግ ማክ በበኩሉ " ወደ ፊት እንደ ኡሞድ ኡኩሪ አይነት ጥሩ ተጫዋች የመሆን ህልም አለኝ፡ በዚህ ውድድር በመሳተፌ እና ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውጭ ተጉዤ በመጫወቴ ትልቅ ደስታ ተሰምቶኛል፡ የበለጠ በእግር ኳሱ እንድገፋም አነሳስቶኛል" ሲል አስተያዬቱን ሰጥቷል፡፡

በዚህ ውድድር ታዳጊዎቹ በእግር ኳስ ውደድሮች ብቻ ሳይሆን በባህል ልውውጥ እና በታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት ፕሮግራሞች ላይ እየተሳተፉ መቆየታቸው ይህ አህጉር አቀፍ ውድድር ይዞት የተነሳውን አፍሪካውያን ታዳጊዎችን ስፖርትን ምክንያት በማድረግ የማቀራረብ ተልዕኮ ያሳካበትም እንደነበርም የካምፓኒው የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ ብራንድ ማኔጀር የሆኑት ወ/ሪት ትዕግስት ጌቱ ገልጸዋል፡፡

እንደ ወ/ት ትዕግስት ገለጻ ከሆነ "ይህ በአይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ያካሄድነው እና የተሳተፍንበት ውድድር በመሆኑ ተሳታፊዎቹ ልጆች በብዙ መንገድ ጥቅም እንዳገኙበት እናምናለን፡፡

እንደ ኮካ ኮላ ኢትዮጵያ ደግሞ በምናከናውናቸው የሀገር ውስጥ ውድድሮች ላይ ማስተካከል ያሉብንን ነገሮች ከሌሎች ተሳታፊ ሀገራት በብዙ የተማርንበት በመሆኑ፡ ወደ ፊት ሀገራቸውን ወክለው መጫወት የሚችሉ ተጫዋቾችን የሚያፈራ ውድድር ለማድረግ ጥረታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ብለዋል፡፡

ውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ እና እንደ ኢትዮጵያ አይነት ቡድኖች ደግሞ በአጭር የጥሪ እና የዝግጅት ጊዜ እንደመሳተፋቸው መጠን፡ የተወሰኑ ክፍተቶች እንደነበሩ በግልጽ ይታዩ ነበር፡፡ በተለይም አንዳንድ ተሳተፊ ሀገራት በውድድሩ ከተቀመጠው የእድሜ ገደብ በላይ የሆኑ የሚመስሉ ተጫዋቾችን ማምጣታቸው እና በጠባብ የቡድን ስብስብ ለተከታታይ አምስት ቀናት ያለ እረፍት ልጆቹ እንዲጫወቱ መደረጋቸው በቀጣዮቹ ውድድሮች ላይ መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

በኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም – ታህሳስ 06/2011 ዓ.ምበኬንያ አስተናጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ በተከናወነው እና አዘጋጇ ኬንያ ናይጀሪያን መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አቻ ከተጠናቀ....

በኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም - ታህሳስ 02/2011 ዓ.ም በኮፓ ኮካ ኮላ የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ ቀን መርሀግብር ኢትዮጵያ ከ ቦትስዋና ከቀኑ 10:30 ያከናወኑት ጨዋታ ያለግብ በአቻ ውጤት ...
11/12/2018

በኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም - ታህሳስ 02/2011 ዓ.ም

በኮፓ ኮካ ኮላ የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ ቀን መርሀግብር ኢትዮጵያ ከ ቦትስዋና ከቀኑ 10:30 ያከናወኑት ጨዋታ ያለግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ የኢትዮጵያ ታዳጊዎች ቡድን ትላንት በአስተናጋጇ ኬንያ አሰደንጋጭ ሽንፈት ካስተናገደበት እንቅስቃሴው በእጅጉ ተሻሽሎ በቀረበት ጨዋታ ፡ ጥሩ የሚባል ፉክክር ማድረግ ቢችልም ወደ ሩብ ፍጻሜው የማለፍ እድሉን የሚያሰፋበትን ወሳኝ ድል ግን ማስመዝገብ ሳይችል ቀርቷል፡፡

በጨዋታው የማገባደጃ ደቂቃዎች ላይ ቦትስዋናዎች በፈጠሩት ጫና ምክንያት ያደረጓቸው ተከታታይ የማግባት ሙከራዎች በእለቱ ድንቅ ሆኖ በዋለው ግብ ጠባቂው አቤል ያንግ አማካኝነት ከሽፎባቸዋል፡፡

የቡድኑ አሰልጣኝ አናንያ ዘለቀ " ከትላንትናው ጨዋታ መጠነኛ የተጫዋቾች እንዲሁም የቦታ ለውጦችን አድርገን መግባታችን እና ለማሸነፍ የነበረን ከፍተኛ ፍላጎት ዛሬ ጥሩ እንድንንቀሳቀስ አስችሎናል" ሲል አስተያዬቱን ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ቡድን ወደ ሩብ ፍጻሜው ለማለፍ ነገ ጠዋት 4:00 ላይ በሚደረገው ጨዋታ ኬንያ ቦትስዋናን በ11 የግብ ልዩነት ማሸነፍ ይኖርባታል፡፡ ውድድሩ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ የተሸጋገረ ሲሆን ዛምቢያ እና ደቡብ አፍሪካን ተከትለው ወደ ሩብ ፍጻሜ የሚያልፉ ቡድኖችን ለመለየት የሚደረጉ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች በነገው እለት ይከናወናሉ፡፡

✍ የውድድሩ የእስካሁን የጨዋታ ውጤቶች እና ቀጣይ መርሀግብር ጥቆማ፡፡

✍ ሰኞ ታህሳስ 01
- ኬንያ 11-1 ኢትዮጵያ
- ዛምቢያ 2-1 ናይጀሪያ
- ማላዊ 1-2 ዩጋንዳ
- ደቡብ አፍሪካ 10-0 አንጎላ
- ኬንያ 2-0 ዚምባብዌ (የልጃገረዶች )

✍ ማክሰኞ ታህሳስ 02
- ታንዛኒያ 0-0 ደቡብ አፍሪካ
- ማላዊ 0-2 ሞዛምቢክ
- ዛምቢያ 0-0 ዚምባቡዌ
- ኢትዮጵያ 0-0 ቦትስዋና

✍ ረቡዕ ታህሳስ 03

- ኬንያ ከ ቦትስዋና ጠዋት 4:00
- ናይጀሪያ ከ ሞዛምቢክ 5:30
- ዩጋንዳ ከ ሞዛምቢክ 9:00
- አንጎላ ከ ታንዛኒያ 10:30

ውድድሩ ሀሙስ እለት የሩብ ፍጻሜ፡ አርብ የግማሽ ፍጻሜ እንዲሁም ቅዳሜ ደግሞ የደረጃ እና የፍጻሜ ጨዋታዎችን በማከናወን ይጠናቀቃል፡፡

በኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም – ታህሳስ 02/2011 ዓ.ም በኮፓ ኮካ ኮላ የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ ቀን መርሀግብር ኢትዮጵያ ከ ቦትስዋና ከቀኑ 10:30 ያከናወኑት ጨዋታ ያለግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋ.....

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ታህሳስ 2/2011 ዓ. ም. በተለያዩ ምክንያቶች ለብሔራዊ አትሌቶች ጥቅም የማይሰጡ የአዲዳስ ምርቶችን ለአንጋፋ አትሌቶች በስጦታ አበረከተ፤ በአዲስ አበባ...
11/12/2018

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ታህሳስ 2/2011 ዓ. ም. በተለያዩ ምክንያቶች ለብሔራዊ አትሌቶች ጥቅም የማይሰጡ የአዲዳስ ምርቶችን ለአንጋፋ አትሌቶች በስጦታ አበረከተ፤

በአዲስ አበባ ስቴድዮም የአትሌቲክስ ማሟሟቂያ ትንሿ ሜዳ ውስጥ ባከናወነው በዚህ የስጦታ ሂደት ላይ ከ68 በላይ ለሚሆኑ አንጋፋና ስመ ጥር ነባር አትሌቶች የተሟላ የስፖርት ትጥቅ ዛሬ አከፋፍሏል፡፡

በተከፋፈለው የስፖርት ትጥቅ ዝርዝር ውስጥ ሙሉ ቱታ፣ ኮፍያ፣ ቲ-ሸርት፣ ሻንጣ፣ ጃኬት፣ ሹራብ፣ ስኒከር ጫማና መሰል የስፖርት አልባሳት ተካትተዋል፡፡ አንጋፋ አትሌቶቹም ለተደረገላቸው የስፖርት ትጥቅ ስጦታና ፌዴሬሽኑ አስታውሶ እንዲህ ያለ ነገር በማድረጉ የተሰማቸው ደስታ ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ታህሳስ 2/2011 ዓ. ም. በተለያዩ ምክንያቶች ለብሔራዊ አትሌቶች ጥቅም የማይሰጡ የአዲዳስ ምርቶችን ለአንጋፋ አትሌቶች በስጦታ አበረከተ፤ በአዲስ አበ....

Address

Addis Ababa
ADDIS

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Liyu Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Liyu Sport:

Share

Category