
15/06/2025
#አልደበራችሁም?
👉 ፊፋ አጋልጦ ሰጣቸው ባየር ሙኒክ ከዕረፍት በፊት ብቻ 6ለ0 እየመራቸው ነበር።
👉 በፎቶው ከላይ የምትመለከቱት የኦክላንድ ሲቲው ካፒቴን ዋና ስራው በሱፐር ማርኬት ውስጥ የሽያጭ ሰራተኛ ነው። ትንሿን አህጉር ወክለው ከኒውዝላንድ የመጡት የኦክላንድ ሲቲ ክለብ ተጫዋቾች ለእግር ኳስ አማተር ናቸው በሳምንት ለትራንስፖርት ወጪ የሚሆን $90 ብቻ የሚያገኙ ናቸው አስቡት ለሃሪ ኬን ብቻ በሳምንት ሙኒክ $503,484 ይከፍላል።
👉 የቡድኑ ስብስብ አስገራሚ ነው አስተማሪ ፣ የፋብሪካ ሰራተኛ ፣ የብረታ ብረት ባለሙያ ፣ የሳምሰንግ ሾፕ ውስጥ ተቀጣሪ ፣ የኮካ ኮላ የሽያጭ ማናጀር እና ቀለም ቀቢ ሁላ ተሰብስበው ያለ ምንም ቋሚ ደሞዝ ፍላጉት ያሰባሰባቸው ናቸው
👉 ጨዋታው አያልቅም እንዴ እያሉ የነበሩት እና ጨዋታው እንደተጀመረ እግራቸው መዛል የጀመረው አማተሮቹ በመጨረሻም በሙኒክ 10ለ0 ተሸንፈው ወጥተዋል። በአለም የክለቦች ውድድር ታሪክም በሰፊ ውጤት የተሸነፈ ክለብ በመሆን አዲስ ሪከርድ ሆኗል
👉 የአለም የክለቦች ዋንጫ የማይመጣጠኑ ክለቦችን እያፎካከረ ስለሆነ ገና ብዙ አስቂኝ እና ፍፁም ደባሪ ግጥሚያዎችንም ልናይበት እንችላለን።
እግር ኳስ/The Beautiful Game