21/03/2026
“ብርቱዋ ገበሬ በፈተና ላይ ናት›— የበረከት ገበሬዋ ወቅታዊ የጤና ሁኔታ መረጃ
አዲስ አበባ — መጋቢት 12 ፣ 2018 ዓ.ም ለብዙዎች የጥንካሬ ተምሳሌትና የሥራ ወዳድነት ተምሳሌት የሆነችው በረከት ገበሬዋ፣ በአሁኑ ወቅት በፅኑ ታማ በሕክምና ላይ እንደምትገኝ ታውቋል። "ወደ ሥራዋ ለምን አልተመለሰችም?" በሚል ከደጋፊዎቿ ለቀረቡ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሆን መረጃ ከቅርብ ምንጮች ለማግኘት ተችሏል።
በረከት ገበሬዋ በእስር ላይ በነበረችበት ወቅት በገጠማት የጤና መታወክ ምክንያት በፖሊስ ሆስፒታል ተኝታ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ በቂ የሕክምና እርዳታ ባለማግኘቷ በጤናዋ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል።
እንደ ምንጮቻችን ገለጻ፣ የበረከት ሕመም ከደም መረጋት (Blood Clotting) ጋር የተያያዘ ሲሆን ለህይወቷም አስጊ ነው ተብሏል::
ከእስር ከተፈታች በኋላ በተለያዩ የመንግሥት እና የግል ሆስፒታሎች የሕክምና ክትትል ስታደርግ ቆይታለች።
ይሁን እንጂ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ጤንነቷ በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ በአሁኑ ሰዓት በጦር ኃይሎች ሪፈራል ሆስፒታል ተኝታ በልዩ ባለሙያዎች ጥብቅ ክትትል እየተደረገላት ይገኛል።
የጤና ባለሙያዎቹ የሚያደርጉት ጥረት ተሳክቶ፣ በቅርቡ ሙሉ ጤንነቷ ተመልሶ ከሆስፒታል አልጋ እንድትነሳ ልባዊ ጸሎታችን ነው።
በረከት ገበሬዋ ለብዙ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የሥራ ክብርን ያስተማረች የቁምነገር ተምሳሌት ናት።
ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ በድል ተወጥታ፣ ፈጣሪ ሙሉ ጤንነቷን እንዲመልስላትና ዳግም ወደ የምትወደው የእርሻ ሥራዋ እንድትመለስ ከልብ እንመኛለን።
ፈጣሪ ምሕረቱን ይላክልሽ 🙏
ጉርሻ page