
23/01/2025
የ25 ሰዎች ሕይወት አለፈ😥
በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ25 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው ከኩርባ ከተማ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ በመገልበጡ መድረሱን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ሃላፊ ም/ኢንስፔክተር ጌታቸው አራጌ ተናግረዋል፡፡
በደረሰው አደጋም ለሕልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ 14 ሰዎች ላይ ከባድ እና 15 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በደላንታና ደሴ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተከታተሉ እንደሚገኙ መጥቀሳቸውንም የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡