
13/04/2025
ምክር ቤቱ የፈረሰው የመስጅድ አጥር ወደ ቦታው እንዲመለስ እንዲሁም የታሰሩት እንዲፈቱ አሳሰበ
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ የሚገኘውን ተባረክ (ጀርመን) መስጅድ ዙሪያ የሚገኘውን አጥር ጨለማን ተገን በማድረግ ትላንት ምሽት ያፈረሱት አካላትን ድርጊታቸውን በማውገዝ ፣ የመስጅድ አጥር ወደ ነበረበት እንዲመለስ እና ያለምንም ጥፋት ከመስጅድ የታሰሩት ሰዎች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ አሳሰበ።