Goolgule/ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Goolgule/ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ኢትዮጵያን በተመለከተ ዜና፤ የዜና ትንተናዎችና ወቅታዊ ጉዳ? If Ethiopia is going to change, information will be integral to it.

ስለ እኛ!

ህዝብ “የነጻ” ሚዲያ ረሃብ አለበት፡፡ ፖለቲከኞችም ከድጋፍና ከሙገሳ ባለፈ መልኩ ግልጽ የሕዝብ ትችትና የባለሙያ አስተያየት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በሁሉም አቅጣጫ ግን ክፍተት አለ – ይህ ክፍተት ደግሞ የመረጃ አፈና በሚካሄድባት ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ነጻነት አለበት በሚባልበት የውጪው ዓለምም በተደጋጋሚ ሲከሰት ይስተዋላል፡፡ ይህንን ክፍተት መሙላት ባይቻልም የበኩላችንን ማበርከት እንዳለብን በማመናችን በተለያዩ አገራት የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ለመመስረት ወሰንን፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ ዕውቀት ኃይል ነው፤ መረጃ ደግሞ አንዱ የዕውቀት መሠረት ነው፡፡ በመሆኑም ጎልጉል የዜና ማሰራጫ ወይ

ም የመረጃ ማስተላለፊያ ስራ መጀመሩን ይፋ ያደረገበት ዕለት የህዝብ ልሳን መሆናችንን አወጅን ማለት ነው። የህዝብ ንብረት ሆንን ማለት ነው። ሕዝብ ኃይል እንዲኖረው የምናገኘውን መረጃ ያለ መድልዖ ለሕዝብ ማሳወቅ አለብን ማለት ነው – ይህ ነው የሕዝብ ንብረት መሆን ማለት፡፡ ስለዚህ በህዝብ ንብረት ላይ የማዘዝ ስልጣን የለንም፡፡ ጎልጉልን አብረን እንምራው፡፡ አጀንዳችን ህዝብ ነውና ሁሉም በነጻነት ይሳተፍበት፡፡ በአመለካከት ነጻነት መከበር ላይ ካለን እምነት በመነሳት የተለያየ ሃሳቦች ላይ ገደብ አናደርግም።

“ከጎሰኝነት ይልቅ ለሰብአዊነት ቅድሚያ መስጠት” የሚለው ታላቅና ሁሉን ዓቀፍ የሆነው መርህ ስለሚገዛን ድረገጻችን በዚህ ዙሪያ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ይህ ማለት ግን በድረገጻችን የሚጻፈው ሁሉ የአንድን ድርጅት ወይም ተቋም ሃሳብ ያንጸባርቃል ማለት እንዳልሆነ ይታወቅልን ዘንድ እንወዳለን፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® የሕዝብ ነው!

በተጨማሪም ለፖለቲካና ለማህበራዊ ጉዳዮች፣ ለአንገብጋቢ ቀውሶች ትኩረት በመስጠት መተዛዘን እንዲሰፍን፣ የፖለቲካውና የፖለቲከኞች አለመጣጣም፣ የህዝብን እምነትና ፍላጎት አለመረዳት፣ አገራችንና ህዝቧን ለከፋ ችግር የዳረገበትን ዋና ጠባሳ በማሳየት ሁላችንንም ነጻ የሚያወጣንን መረጃ ለሕዝባችን በማስተላለፍ መረጃን ኃይል ወደሆነው እውቀት በማስተላለፍ የበኩላችንን እንሰራለን። ማንኛውንም ዓይነት አስተያየትና በጨዋነት እናስተናግዳለን። ጽሁፎቻችንም እንደአስፈላጊነቱ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ይቀርባሉ፡፡ እኛ ይህን እንመስላለን።

About Us

We are a group of Ethiopian professionals, who seek to provide a diverse, balanced and expansive source of important news, opinions, studies and analyses on issues mostly pertinent to Ethiopia. We believe the public seeks a “free” media where a broad spectrum of contributors are able to offer varied information, ideas and opinions, whether or not one agrees with them. We hold that the public will benefit from diverse views that bring new light to an issue, a region, a group or a viewpoint and will invite such contributions. In a pluralistic society, we should be aware of the needs, challenges and perspectives of others; even when it challenges our own critical analysis of facts, opinions, assumptions and conclusions. In Ethiopia, opposing viewpoints are not tolerated, unflattering truth is hidden and critical analysis of actions, ideas or policies can bring punitive actions. Even in the Diaspora, where the potential for media freedom exists; censorship, competition, exclusion, isolation and sectarianism—ethnic, political, regional, religious and other—often limit what is available to the public. It has created a significant gap in our information coverage; coverage we urgently need in order to sharpen our perspectives, to bridge our major rifts and to create a new, stronger and healthier Ethiopia. Though it is hard to fill such a huge gap easily, it is our intention to contribute our part to uncovering what is concealed, to reminding ourselves of what has been wrongly overlooked and to piercing the darkness of “informational starvation” with new light—“goolgule (ጎልጉል)” – the Amharic word for investigation, exposure or the revelation of something necessary for change. Our approach will affirm the inclusive and universal principles of “humanity before ethnicity” Our intent is to be the voice of and for the public—not only endorsing one’s own preferences—but also being open to publishing opinions with which we may disagree. We believe the people should be able to judge for themselves rather than blocking public access to information. We will give due consideration to social, legal, economic, political and other pertinent issues that are seriously affecting our highly diverse society, both here in the Diaspora and back at home. However, it should be noted that the news, views, opinions, etc that are posted on “goolgule” are not presented to promote principles of a certain organization or institution. Goolgule: the Amharic Internet Newspaper will be presented mainly in Amharic but, as deemed necessary, we will share information in English as well.

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ በፊት ለማርያም ተሰጥተዋት የነበሩት “የመድኃኒዓለም ረዳት” (Co-Redemptrix) እና “ሴት አማላጅ” (እናት አማላጅ) (Mediatrix) የሚሉት ስሞች ለ...
15/12/2025

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ በፊት ለማርያም ተሰጥተዋት የነበሩት “የመድኃኒዓለም ረዳት” (Co-Redemptrix) እና “ሴት አማላጅ” (እናት አማላጅ) (Mediatrix) የሚሉት ስሞች ለማርያም እንዳይውሉ ውሳኔ አስተላለፈች። ውሳኔው በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ሊመሠረት ለታቀደው ኅብረት ድጋፍ ሰጪ እንደሆነም ተነግሮለታል።

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን የአስተምህሮና ሥነ-ስርዓት የሚመራው “በጳጳሳዊ ምክር ቤት የእምነት አስተምህሮ ጽ/ቤት” (Dicastery for the Doctrine of the Faith (DDF)) በኅዳር ወር መጀመሪያ “የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝብ እናት” (Mater Populi Fidelis) በሚል ርዕስ ስለ ማርያም ሰፊ ማብራሪያ ይፋ አድርጓል።

* ውሳኔው ለአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት መንገድ ጠራጊ ነው ተብሏል የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ በፊት ለማርያም ተሰጥተዋት የነበሩት “የመድኃኒዓለም ረዳት” (Co-Redemptrix) እና “ሴት አ....

ነጭ ሽብርም ሆነ ቀይ ሽብር በቀለም መጠሪያቸው ካልተለያዩ በቀር ሁለቱም ሽብር ናቸው። መስከረም 21 ቀን 1969 ዓ.ም. አዲስ አበባ ሞርጌጅ ህንጻ ውስጥ ትሠራ የነበረችውን ባለቤታቸውን መኪ...
13/12/2025

ነጭ ሽብርም ሆነ ቀይ ሽብር በቀለም መጠሪያቸው ካልተለያዩ በቀር ሁለቱም ሽብር ናቸው። መስከረም 21 ቀን 1969 ዓ.ም. አዲስ አበባ ሞርጌጅ ህንጻ ውስጥ ትሠራ የነበረችውን ባለቤታቸውን መኪናቸው ውስጥ ሆነው በመጠባበቅ ላይ እያሉ አድብተው ይጠብቁ በነበሩ የኢሕአፓ ነፍሰ ገዳዮች በቅርብ ርቀት በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸው ያለውፈው በወቅቱ በሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት የጊዜያዊ ጉዳዮች ሰብሳቢ የነበሩት ዶ/ር ፍቅሬ መርዕድ ነጭ ሽብር ከበላቸው ዜጎች አንዱና ነጭ ሽብር ራሱን ያስተዋወቀበት ኦፕሬሽኑ ነው። ….

* የተዘነጋው የኢህአፓ ነጭ ሽብርና የወቅቱ ኢህአፓ አካሄድ ነጭ ሽብርም ሆነ ቀይ ሽብር በቀለም መጠሪያቸው ካልተለያዩ በቀር ሁለቱም ሽብር ናቸው። መስከረም 21 ቀን 1969 ዓ.ም. አዲስ አበባ ሞ...

የመረጃ ጦርነት ወጥመድ፡ ሃገርንና መንግሥትን ለጥቃት ያጋለጠው የጌታቸው ረዳ የአልጀዚራ “ፊት ለፊት” ፕሮግራም ሲፈተሽ................................................
04/12/2025

የመረጃ ጦርነት ወጥመድ፡ ሃገርንና መንግሥትን ለጥቃት ያጋለጠው የጌታቸው ረዳ የአልጀዚራ “ፊት ለፊት” ፕሮግራም ሲፈተሽ....................................................................
ዓላማው ግልጽ ነው። አስታጥቀው፣ አደራጅተው፣ ሴራ አዋቅረው ያሰማሩትን ኃይል መርዳት ነው፤ ለቅጥረኞቻቸው ሽፋን በመስጠት ሲያፈራርሷቸው እንዳየናቸው አገራት ሊያፈርሱን ነው። ቀደም ሲል ከነጀሌዋቻቸው በአልጃዚራ በኩል ኢትዮጵያ ላይ ሲተፉ የነበሩ በመክሸፋቸው በሌሎች ተወክለው ስለማየታችን የጋዜጠኛነት ካባ ለብሳ ስለ ሞራል ያነሳችው የአማራ፣ የአፋር፣ የኦሮሞ እና ሌሎች ዜጎች ላይ የተፈጸመውና እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ ደንታ የማይሰጣት “ሞራለ ሙሉዋ” የአዲስ ስታንዳርዷ ጸዳለና “ነጩ ትህነግ” የሚባለው ሼትል ከፊት ሲታዩ ድግሱ ፍንትው ብሎ የሚታይ ይሆናል። ከዚያም በላይ አክቲቪስት ሆኖ ተተርጉሞ የተሰጠውን የጌታቸውንና የጠቅላይ ሚኒስትርን አብይ ልጥፎች እያነበነበ ሲወራጭ የነበረው ዲቃላ እንግሊዛዊ ማህዲ መካከል የገባው ጌታቸው ረዳ ይህን ድግስ አያውቀውም ሊባል አይችልም። ለሁሉም ትምህርትና ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የዘወትር አምደናችን የሚከተለውን ልከውልናል።

በአለባቸው ጉብሳ

እንደ መግቢያ

አዲስ ሪፖርተር ዒላማቸውን ኢትዮጵያ ላይ ያደረጉ በውጭ ሃገር መንግስታት ባለቤትነት፣ ጥቅምና መተዳደሪያ ህግ የሚተዳደሩ እንደ (ቢቢሲ፣ ዶቼቬሌ፣ ቪኦኤ እና ሌሎች) የመሳሰሉ የመገናኛ አውታሮች ሚና አስመልክቶ ሰፊ ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል።

እነዚሁ መገናኛዎች ቀለብ ሰፋሪዎቻቸው የሃገራቸውን ብሔራዊ ጂኦስትራቴጂክ ግብ ለማሳካት እንደ አንድ ብሔራዊ የተፅዕኖ መሳሪያ የሚጠቀሙባቸው መሆናቸውን በመግለፅ በቀረበው ጽሁፍ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ርዕዮተ ዓለምና እሴቶችን ለማስረፅ፣ እምነትና አመለካከት ላይ የሚፈልጉትን ዓይነት ተፅዕኖ ለመፍጠር እና የጠላት ሃገርን ሰላማዊ አስተዳደርን ለማወክ ጥቅም ላይ ሲውሉ እንደነበር ከዚህ በፊት በዝርዝር አቅርቦ እንደነበር አይዘነጋም።

እነዚህ መገናኛ ብዙሃን የሃገራቸውን በተለይ ሶቪየት ኅብረት፣ የአሜሪካና የእንግሊዝ ስትራቴጂክ ግባቸውን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማስከበር ባደረጉት ፉክክር ርዕዮተ ዓለም በማስረፅ፣ በመንግሥትና በህዝብ መካከል መተማመን እንዳይኖር፣ የሕዝቦች እርስ በርስ ግንኙነት በጥርጣሬና በጥላቻ የተሞላ እንዲሆን እና የሃገር ምሶሶ የሆኑት የፀጥታና ደህንነት፣ የመከላከያ፣ የፍትህ አስተዳደርና ሌሎች የመንግሥት ተቋማት በሕዝብ ዘንድ እምነት እንዳይጣልባቸው በማድረግ ህዝባዊ አመፅ በመቀስቀስና ለሽምቅ ተዋጊዎች ወታደራዊ ፕሮፓጋንዳ ድጋፍ በመስጠት የቀዳማዊ ኃይለሥላሴና የደርግን መንግሥትን ለመጣል ያደረጉትን አስተዋጽዖ አይተናል።

ባለሁለት ስለቱ አሁናዊ የመረጃ ጦርነ

https://www.goolgule.com/jawar-the-sme-in-strike-calls-for-another-one/
17/11/2025

https://www.goolgule.com/jawar-the-sme-in-strike-calls-for-another-one/

አሁን ላይ ጃዋር የፖለቲካ ምሕዋሩን ስቶ የሚሄድበትን መንገድ የማያውቅ ሆኗል። በዚህ ኪሣራ ውስጥ ተስፋ ሰጪ ሆኖ ያገኘው የሥራ ማቆም አድማ መጥራት ነው። እስካሁን ያልተሳኩ የሥራ ማቆ.....

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goolgule/ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Goolgule/ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ:

Share