EthioXpress

EthioXpress "Your go-to source for Ethiopian news and entertainment. Stay updated, informed, and entertained with
(1)

03/04/2024
04/02/2024
09/01/2024
09/01/2024

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ በአሥመራ በነበራቸው የኹለት ቀናት ጉብኝት ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር በኹለትዮሽ፣ በቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር አስታውቋል።

ኹለቱ መሪዎች በኹለትዮሽና በጋራ የትብብር መስኮች ላይ ሰፋ ባለ ቀጠናዊ የትብብር ማዕቀፍ ለመስራት መስማማታቸውን የገለጠው ሚንስቴሩ፣ በትግዕስትና በቀና መንፈስ በመጓዝና "ከተንኳሽ አጀንዳዎች በመራቅ" ቀጠናዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ መስማማታቸውን ጠቅሷል።

ኤርትራ ከሱማሊያ ጋር ባላት የኹለትዮሽ ግንኙነትና በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ በቅርቡ ዝርዝር መግለጫ እንደምታወጣም ሚንስቴሩ ገልጧል።(ዋዜማ)

 #አስደማሚ
08/12/2023

#አስደማሚ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሶማሊያ የነበረውን ሚና  መልሶ ለመቃኘት እያሰበ ነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሶማሊያ የነበረውን ሚና  መልሶ ለመቃኘት እያሰበ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ...
11/11/2023

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሶማሊያ የነበረውን ሚና መልሶ ለመቃኘት እያሰበ
ነው

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሶማሊያ የነበረውን ሚና መልሶ ለመቃኘት እያሰበ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለፁ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ በተለይም በቀጠናው ለበርካታ ዓመታት በሰላም ማስከበርና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ጉልህ አስታዋፅኦ ስታበረክት መቆየቷ ይታወቃል። የመከላከያ ሰራዊቱም በብቃትና ዲሲፕሊን አለም አቀፍ እውቅና ያተረፈና ምስጉን ነው።

ሆኖም በሶማሊያ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስርና ከዚያ ባለተናነሰ ቁጥር ደሞ በተናጠል ሽብርተኝነትን በመዋጋት ጎረቤት ሶማሊያን በመርዳት እንዲሁም ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረውን አደጋ በመመከት ላይ ተጠምዶ ቆይቷል ።

በዚህም ከፍተኛ የቁስና የሰው ሃይል ዋጋ ተከፍሏል። በተለይም በተናጠል የምታካሄደውን የፀረሽብር ዘመቻ ያለምንም ድጋፍ በራሷ አቅም ሸፍና ቆይታለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህንን ፖሊሲ እንደገና በመፈተሽ የሠራዊት ሃይሏን በመሰብሰብ በአጎራባች አካባቢዎች ላይ ብቻ ያተኮረ የፀረሽብር ስራ ለመስራት እየታሰበ መሆኑን ለመከላከያ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ።

በሞቃድሾ መንግስት አከባቢ በቂ ለውጥ መምጣት አለመቻሉ መቋጫው በማይታወቅ ሁኔታ መስዋዕትነት እየከፈሉ ከመቀጠል ሌሎች አማራጮችን ማሰብ እንደሚገባ አንዳንድ አካላት በማሳሰብ ላይ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል።



በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመሩን " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ዘግቧል።እንደ ዘገባው ከሆነ ባለፉት  ሳምንታ...
08/11/2023

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመሩን " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ባለፉት ሳምንታት የፌደራል መንግሥት እና የኦሮሚያ ክልል መንግስሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች እንዲሁም ሁለት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ተሳታፊ የሆኑበት ውጤታማ የተባለ የፖለቲካ ውይይቱ ተካሂዷል።

ውይይቱ ውጤታማ ስለነበር እና በዚህም ምክንያት የፌደራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች የተሳተፉበት ውይይት ትላንት ጥቅምት 27/2016 ዓ/ም በታንዛኒያ ዳሬሰላም መጀመሩን ተነግሯል።

08/11/2023

መከላከያ ማረን

አንጋጦ መትፋት መልሶ ከአፍ እዲሉ መከላከያን ወግቼ በህዝብ የተመረጠን መንግስት እገለብጣለሁ የሚለው ጃውሳው ቡድን አሁን መዋቅሩ ሁሉ ፈራርሶ የሚበላው እስኪያጣ ድረስ ከማህበረሰቡ እየተገለለ ይገኛል።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን አደራጅቶ መከላከያን ለመውጋት የሞከረው ጃውሳው ቡድን አሁን ላይ ብትንትኑ መውጣቱ ተረጋግጧል ግማሹ ከድቷል ግማሹ እጅ ሰጥቷል የቀረው ተደምስሷል።

እንኳን አንድ የመንደር ሽፍታ ይቅር እና ማንኛውም የተደራጀ ሓይል መከላከያን ሊያሸንፍ አይችልም።



02/11/2023
የዘንዶ ቆዳ በመያዝና ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተም ወንጀል የተጠረጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ክስ ተመሰረተየዘንዶ ቆዳ እና የተፈጥሮ ማዕድን በመያዝ እንዲሁም ሀሰተኛ የውጭ ሀገራ...
02/11/2023

የዘንዶ ቆዳ በመያዝና ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተም ወንጀል የተጠረጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ክስ ተመሰረተ

የዘንዶ ቆዳ እና የተፈጥሮ ማዕድን በመያዝ እንዲሁም ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተም ወንጀል የተጠረጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ክስ ተመሰረተ።

ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ልደታ ምድብ 14ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ሲሆን÷የፍትሕ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ተደራራቢ ክሶችን አቅርቦባቸዋል።

ክስ የቀረበባቸው ተከሳሾችም 1ኛ አቦየም መኮምቢሊ ጂ፣ 2ኛ ርሆቦት ሮሄ ፣ 3ኛ ዳውድ ሲዲኪእና ኪምቢ ኪምቢ ጆን ይባላሉ።

በተከሳሾቹ ላይ የቀረበው አንደኛው ክስ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና አንቀጽ 356 ላይ የተደነገገውን ድንጋጌ ተላልፈዋል በሚል ነው።

ተከሳሾቹ ተከራይተው በሚኖሩበት በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ቦታው ቦሌ አዲስ ት/ቤት አካባቢ ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በፀጥታ አካላት በተደረገ ክትትል በጋራ በመሆን ሀሰተኛ ገንዘብ ለመስራት የሚያገለግሉ መሳሪያዎች፣ የተለያዩ ኬሚካሎች እና ሀሰተኛ ገንዘብ መስሪያ ወረቀቶችን በመጠቀም ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች አመሳስለው በመስራት ላይ እያሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው በክሱ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ዐቃቤ ሕግ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተሳታፊ በመሆን ሀሰተኛ ገንዘብ የመስራት ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

በ2ኛው ክስ ላይ ደግሞ ተከሳሾቹ አንድ የብር ማተሚያ ማሽን ፣ ሀሰተኛ ገንዘብ ለመስራት የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ኬሚካሎች ፣ በዶላር ቅርፅ የተቆረጠ 55 ወረቀት፣ ጥቁር በዶላር ቅርፅ የተቆረጠ 27 ወረቀት፣ የሀሰት ገንዘብ ማዘጋጃ ኦሬንጅ ወረቀት እና ሌሎች 109 ወረቀት እንዲሁም22 የዶላር ማሸጊያ ፕላስቲክና ዶላር ለማተም የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ተከሳሾቹ በጋራ ሲጠቀሙባቸው መገኘታቸው ተጠቅሷል፡፡

በዚህም ዐቃቤ ሕግ ሀሰተኛ ነገሮችን ለመስራት የሚያገለግሉ መስሪያ እና መሳሪያዎች መያዝ ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ተከሳሾቹ በጋራ በመሆን ምንም አይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው 71 ነጥብ 15 ግራም የሚመዝን ካኦሊናይት የተፈጥሮ ማዕድን በመኖሪያ ቤት ውስጥ ይዘው የተገኙ መሆኑን የጠቀሰው ዐቃቤ ሕግ÷ ፈቃድ ሳይኖረው የተፈጥሮ ማዕድን መያዝ እና የአዋጁን ድንጋጌዎች መተላለፍ ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል በሁሉም ተከሳሾች ላይ በተደረገው ማጣራት የፀና የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሀገር ውስጥ ሲኖሩ የተያዙ መሆናቸው በክሱ ተገልጾ÷ የፀና የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖር በሀገር ውስጥ የመኖር ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።

በተጨማሪም ፈቃድ ሳይኖራቸው የዱር እንስሳት ቆዳ ማለትም የዘንዶ ቆዳ ይዘው የተገኙ በመሆኑ በፈፀሙት ምንም አይነት ፈቃድ ሳይኖር የዱር እንስሳት ውጤቶች ይዞ መገኘት ወንጀል ክስ ተከሰዋል።

በተጨማሪም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች በተጠቀሰው ተከራይተው ይኖሩበት በነበረው መኖሪያቸው ውስጥ አጠቃላይ 2 ሺህ 705 ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር የተገኘ በመሆኑ÷ ሀሰተኛ ገንዘብ ይዞ የመገኘት ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።

አራተኛ ተከሳሽ በአራተኛ ክስ ላይ ብቻ የተጠቀሰ ሲሆን÷ ቀሪዎቹ ግን በሁሉም ክሶች ላይ መካተታቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህ መልኩ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው ተደራራቢ ክሶች በችሎት እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን÷ ተከሳሾቹ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል።

ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ላይ የቀረበው ተደራራቢ ክስ መሆኑን እና የተፈጸመው ወንጀል የሀገር ኢኮኖሚን የሚጓዳ ተግባር መሆኑን ጠቅሶ÷ የዋስትና ጥያቄያቸውን በመቃወም ተከራክሯል።

በተጨማሪም ተከሳሾቹ ቋሚ አድራሻና የፀና የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በመሆኑ በዋስ ቢወጡ የዋስትና ግዴታቸውን አክብረው ላይቀርቡ ይችላሉ በማለት የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ ጠይቋል።

የግራ ቀኙን ክርክር የተከታተለው ችሎቱ መርምሮ ዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠት ለፊታችን ጥቅምት 26 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Address

Adds Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioXpress posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share