14/07/2025
Ethiopian Coders Initiative
በአረብ ኢምሬትስ ስፖንሰርነት በኢትዮጵያ የተጀመረ ኢንሼቲቭ ነው:: የኢትዮጵያ ወጣቶች (ግማሽ ያህሉ ሴቶች) የዲጂታል ክህሎት አዳብረው በዲጂታል ኢኮኖሚው ውስጥ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ማድረግን ያለመ ነበር:: ይህ “5 ሚሊዮን ኢትዮጵያን ኮደርስ ኢንሼቲቭ” (5 Million Ethiopian Coders Initiative) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አካል የሆነ ሰፊ ፕሮግራም ነው።
#ፕሮጀክቱ:-
* ፕሮግራሚንግ (Programming)
* አንድሮይድ ልማት (Android Development)
* የዳታ ሳይንስ (Data Science) እና
* አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence) መሰረታዊ ስልጠናዎችን የሚያካትት ነው።
---
ይህ ፕሮጀክት ሲጀመር በሶስት ዓመታት ውስጥ (እስከ 2026) አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ማሰልጠንን ያለመ ነበር።
ይሁንና ፕሮግራሙ በበይነመረብ (Online) መሰጠቱ (ኢንተርኔት የማግኘት ችግር)፣ በነጻ የሚሰጥ ስልጠናን የመናቅ አባዜ (ጥቅሙን በአግባቡ ባለመረዳት)፣ ስልጠናው የሚሰጠው በእንግሊዝኛ ቋንቋ መሆኑ . . . በሚጠበቀውና በሚፈለገው ሁኔታ እየተሳካ አይደለም::
የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ስልጠናውን ለመውሰድ የተመዘገቡ ዜጎች ቁጥር 800,000 በላይ ሲሆን በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቀው ሰርተፊኬት የወሰዱት ሰዎች ብዛት 270,000 በላይ ነው::
በዚህ አፈጻጸም መሰረት የታቀደለት ወጣቶች የዲጂታል ዕውቀት ታጥቀው በቴክኖሎጂ ዘርፍ ሥራ የመፍጠር፣ ችግር ፈቺ የመሆን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የማድረግ ዓላማ የሚሳካ አይመስልም::
---
ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ መንግስት በቀጥታ ባያስገድድ እንኳን #ሰርተፊኬቱ በመንግስት ስራዎች፣ እድገት፣ ሹመት . . . እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚወስድበት ጊዜ ሩቅ ላይሆን ይችላል። ስልጠናውን መውሰድ የሚችል ሰው ሁሉ መጀመር ብቻ ሳይሆን በአግባቡ ተከታትሎ በማጠናቀቅም #ሰርተፊኬቱን ቢይዝ ይመከራል።🙌