Tofa arada

Tofa arada Digital army and propaganda for prosperity party

15/06/2025
15/06/2025
07/05/2025
25/02/2025
03/02/2025

በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተመረጡ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት

1. ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ
2. አቶ አደም ፋራህ
3. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
4. አቶ ሽመልስ አብዲሳ
5. አቶ ከፍያለው ተፈራ
6. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
7. አቶ አወሉ አብዲ
8. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
9. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
10. አቶ ሳዳት ነሻ
11. ዶ/ር ተሾመ አዱኛ
12. ዶ/ር እዮብ ተካልኝ
13. አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ
14. አቶ አህመድ ሽዴ
15. ወ/ሮ ሀሊሞ ሀሰን
16. አቶ መላኩ አለበል
17. አቶ አረጋ ከበደ
18. አቶ ጃንጥራር አባይ
19. ዶ/ር አብዱ ሁሴን
20. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
21. አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጣው
22. ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ አድማሱ
23. አቶ ጥላሁን ወልዴ
24. ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ
25. ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ
26. ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ
27. ዶ/ር እንደሻው ጣሰው
28. ወ/ሮ ሙፊሪሃት ካሚል
29. ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ
30. ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ
31. አቶ ማስረሻ በላቸው
32. ሀጂ አወል አርባ
33. አቶ መሀመድ ሁሴን አሊሳ
34. አቶ መሀመድ አህመድ አሊ
35. አቶ ኦርዲን በድሪ
36. ወ/ሮ አሚና አብዱከሪም
37. ዶ/ር ፍፁም አሰፋ
38. አቶ ደስታ ሌዳሞ
39. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
40.አቶ አሻድሊ ሀሰን
41. አቶ ጌታሁን አብዲሳ
42. ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ
43. ዶ/ር ጋልዋክ ሮን
44. ዶ/ር አብርሃም በላይ
45. አቶ ታዜር ገ/ሔር

01/01/2025

የአፍሪካውያን ኩራት የብልጽግና ተምሳሌት ከተማ ፦
አዲስ አበባ!!

አዲስ አበባ ታሪካዊት ፣ የአለም ሶስተኛዋ የዲፕሎማሲ ከተማ ፣ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ ድንቅ ውብ ከተማችን ነች።

አዲስ አበባ በየጊዜው የተለያዩ ኩነቶችን ታስተናግዳለች። እንግዶቿን በክብር ተቀብላ በፍቅር አስተናግዳ በሰላም ትመልሳለች።

ዘንድሮም እንደተለመደው ከተማችን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባሄን ለማስተናገድ ሽር ጉዷን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች።

የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚካሄደው አዲስ አበባችን እጅግ ውብ በሆነችበትና ባማረችበት ጊዜ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች የቆየ የእንግዳ አቀባበል እሴትና የፀጥታ ኃይሎቻችን ቁርጠኛ የሰላም ዘብነት ሲታከልበት ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ሐሴትን በእንግዶቻችን ላይ ይጨምራል። አዲስ አበባ እጅግ አምራለች! አፍሪካዊት የነፃነት እመቤትነቷም በግልፅ እየታየ ይገኛል።

አዲስ አበባ ከተማ ሁለንተናዊ ሰላምና ፀጥታዋን ከዳር እስከዳር በመጠበቅ እንግዶቿን በኢትዮጵያዊያን ጨዋነት በክብርና በፍቅር ለመቀበል እጆቿን ዘርግታ በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች!!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ ቤት

07/08/2024

ነባራዊ ሁኔታውን በጥልቀት በመመርመር ፣ ዘላቂ ዕድገታችንን ለማረጋገጥ የተደረገው ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ግቡን እንዲመታ የድርሻችንን እንወጣ !

ፓርቲያችን በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ባለብዙ ወገን የኢኮኖሚ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ በተለይም ምርትና ምርታማነት በእጅጉ እንዲጨምር ታሪካዊ ውሳኔዎችን እያሳለፈ መጥቷል።

በተደራራቢ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች የማይበገር ፣ ስንዴን ኤክስፖርት ወደ ማድረግ ጭምር መሸጋገር የተቻለው ዘመኑን በዋጁ የፓርቲያችን ፖሊሲዎች ጥራት እና በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመጣው የመንግስት የመፈፀም አቅም ነው፡፡

ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋጥ በምናደርገው ርብርብ የዜጎቻችን ህይወት እየተሻሻለ ሲሄድ መንግስት በኢኮኖሚው ላይ እጁን እያሳጠረ እንደሚሄድና በአንፃሩ ደግሞ የግሉ ዘርፍ የአንበሳውን ሚና እንዲጫዎት ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጠሩ ፓርቲያችን በኢኮኖሚ ፕሮግራሙ አመላክቷል።

ተራማጅ የሆኑ እሳቤዎች ባለቤት የሆነው ፓርቲያችን ተለዋዋጭ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ ሁኔታዎችን ቀድሞ በመረዳት ትናንትን ከዛሬ ፣ ዛሬን ደግሞ ከነገ እያስተሳሰረ ጠንካራ ሀገር ለመፍጠር ይተጋል እንጅ በጅምር ስኬቶች አይረካም ፤ በጊዜያዊ ተግዳሮቶችም ያነገበውን ራዕይ ዕውን ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም።

በየዘርፉ ውስብስብ ዕዳዎችን የተረከብን ትውልዶች እንደመሆናችን ያለፈውን በማከም የሚገጥመንን ችግር ቀድመን በመከላከል እንዲሁም ለስኬታችን መስፈንጠሪያ በማድረግ ከድል ላይ ድል ማስመዝገብ የህልውናችን ዋስትና ነው።

አንዳንዶች በቅርቡ በሀገራችን የተደረገው ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ሳይታሰብበት ድንገት የተደረገ አድርገው ተረድተውታል ወይም ተርጉመውታል።

ትርፍና ኪሳራው ተለይቶ ከዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ግባችን አንፃር በዘርፉ ምሁራን በጥልቀት ተጠንቶ ፣ የተለያዩ ሂደቶች አልፎ የመጣ እንጅ ድንገተኛ አለመሆኑን የፓርቲያችን አቅጣጣዎች እና ከውሳኔው ቀደም ብለው የነበሩ ምክክሮችን ማስታወስ ይበጃል።

ሰው ተኮር ፕሮግራሞችን በስፋትና በጥራት እየተገበረ የሚገኘው መንግስታችን የህዝባችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርስን የኑሮ ጫና ለማቃለል አበረታች ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል ፤ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ለአብነትም በከተማችን ዘርፈ ብዙ ትርጉም ያለው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ተቋማዊ ለማድረግ የተከናወኑ አበረታች ስራዎች ፣ የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላትን በማስፋፋት ፣ የሴፍቲኔት ፕሮግራምን በዘላቂነት ህይወትን በሚያሻሽል አሰራር እንዲደገፍ እየተደረገ ያለው ጥረት ፣ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ፣ በትራንስፖርት እና በመሳሰሉት የሚደረጉ በቢሊዮን ብር የሚቆጠሩ ድጎማዎች ዋነኛ ዓላማ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ጉዟችን ሂደቱም ጭምር ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ እንዲሄድ ፓርቲያችን እና መንግስታችን ያላቸውን ፅኑ አቋም አመላካች ነው::

ሰሞኑን የተደረገውን ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ተከትሎም በህዝባችን ላይ ሊፈጠር የሚችልን የኑሮ ጫና ለማቃለል መንግስት ተጨማሪ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ይጠበቃል።

አጋጣሚዎችን ሁሉ በህዝብ ላይ ተረማምደው ያልተገባ ጥቅም ለማጋበስ የሚሞክሩ ስግብግብ ግለሰቦችን ደግሞ በህግ እና በአሰራር ተጠያቂ የማድረጉ ተግባር እንደሚጠናከር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሰሞኑን መግለፃቸው አይዘነጋም ።

ዘላቂ ዕድገታችንን ለማረጋገጥ የተደረገው ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ በታለመለት መልኩ ግቡን እንዲመታ በተለይም የንግድ ስርዓታችንን በማዘመን ፣ ብልሹ አሰራሮችን ፈጥኖ የማረም ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በህገ -ወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ህዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ ለዘላቂ ጥቅሙ እና ለመብቱ መረጋገጥ የድርሻውን እንዲወጣ ለማድረግም በትኩረት ይሰራል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ /ቤት


Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tofa arada posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share